You are here:መነሻ ገፅ»milkta»news admin - Sendek NewsPaper
news admin

news admin

 

የፕሬስ ነፃነት ማለት ሃሳብን በተለያየ የመገናኛ ብዙሃን ማለትም በኤለሌክትሮኒክስ እና የህትመት ሚዲያዎች የመግለፅ መብት ማለት ሲሆን ይህ መብት መረጃን ጠይቆ የማግኘት እና ይህን መረጃ በተፈለገው መንገድ የማሰራጨት መብትንም ያጠቃልላል። በአብዛኛው ይህን መብት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ውጪ የመተግበር ፍላጎት ቢኖርም ለተለያዩ ዓላማዎች ሲባል ይህ ነፃነት ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ጥበቃዎች እየተበጁለት የሚተገበር ነው።


የፕሬስ እና ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብትን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያለውን ታሪክ ስንመለከት በሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ተሻሽሎ የወጣው የ1948ቱ ህገ መንግስት ይህን መብት ከማረጋገጥ አኳያ ፈር ቀዳጅ የነበረ ሲሆን በዚህ ህገ መንግስት አንቀፅ 41 ስር «በመላው የንጉሰ ነገስት ግዛት ውስጥ በህግ መሰረት የንግግር እና የጋዜጣ ነፃነት የተፈቀደ ነው።» በሚል ተደንግጓል። በተመሳሳይ የኤርትራ ህገ መንግስት በአንቀፅ 12/d/ ስር ሃሳብን በነፃ የመግለጽ መብት በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ መሆኑን እና የፌዴራል መንግስት ይህን መብት የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል።


የንጉሱ ሥርዓት ካበቃ በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው የደርግ መንግስት በአብዛኛው የስልጣን ዘመኑን የፕሬስ ነፃነትን የሚያስከብር የህግ ሥርዓት ያልዘረጋ ሲሆን ሆኖም መስከረም 1/1980ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አዋጅ በአንቀፅ 47/1/ ስር ኢትዮጵያውያን የንግግር፣ የፅሁፍ፣ የመሰብሰብ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።


ከላይ የተገለፀው ለፕሬስ ነፃነት የተሰጡ ህጋዊ ከለላዎች ባለፉት ሥርዓቶች ምን ይመስሉ እንደነበር ሲሆን በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ የነበረውን ተጨባጭ ታሪካዊ ዳራን ስንመለከት አጀማመሩ ከህትመት ሚዲያው ጋር የሚገናኝ ሲሆን ከቀዳሚዎቹ የህትመት ውጤቶች መሀከል በአፄ ምኒልክ ዘመን ይሰራጭ የነበረው አእምሮ እና ጎህ ጋዜጣዎች ተጠቃሽ ናቸው። በተለይ በአፄ ሃይለስላሴ ዘመን በቁጥር በርከት ያሉ ጋዜጣዎች ይታተሙ የነበረ ሲሆን ከነዚህም መካከል የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ሰንደቅ ዓላማችን፣ ህብረት፣ አዲስ ዘመን እና ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ የሚጠቀሱ ናቸው። በነዚህ ሁለት ነገስታት ወቅት ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦችን የሚያመሳስላቸው ነገር የህትመቶቹ ይዘት ሲሆን ይህም በአብዛኛው የዘውዱን ሥርዓት የሚያሞካሹ መሆናቸው ነበር።


የንጉሳዊ ሥርዓት በሀገሪቱ ካበቃ በኋላ ወደ ስልጣን የወጣው የደርግ መንግስት ቀደም ብለው ሲታተሙ የነበሩ የህትመት ውጤቶችን በመዝጋት እና በመውረስ በምትካቸው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እና ሰርቶ አደር የተባሉ ጋዜጦች ታትመው ለስርጭት እንዲቀርቡ አደረገ። በዚህ ሥርዓት ምንም አይነት የግል ፕሬስ ያልነበረ ሲሆን በመንግስት ታትመው የሚወጡ የህትመት ውጤቶች በሙሉ የቅድመ ምርመራ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።
የብሮድካስት አገልግሎትን በተመለከተ የመጀመሪያው ሬዲዮ ጣቢያ የተቋቋመው በ1941 ዓ.ም አካባቢ ከጣሊያን ካምፓኒ ጋር በተደረገ ስምምነት ሲሆን ይህ የሬዲዮ ጣቢያ በጣሊያን ወረራ ወቅት ተቋርጦ በ1949 ዓ.ም አካባቢ በድጋሚ የኢትዮጵያ ሬዲዮ በሶስት ጣቢያዎች እና በስድስት ቋንቋዎች ስራውን ጀምሯል።በኢትዮጵያ የቴሌቭዥን አገልግሎት በ1960ዎቹ መጀመሪያ ተጀምሯል።


የደርግ ሥርዓት ካበቃ በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው የሽግግር መንግስቱ ያወጣው የኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተር በክፍል 1 አንቀፅ (1) (ሀ) ስር የእምነት እና ሃሳብን የመግልፅ መብቶች የተረጋገጡ ሲሆን ከዚህ በኋላ በ1987 ዓ.ም የፀደቀው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ለፕሬስ ነፃነት የተሻለ ሰፋ ያለ ሽፋን በመስጠቱ በርካታ የግል የህትመት ውጤቶች ወደ ኢንዱስትሪው ሊገቡ ችለዋል።


በዚህ ጽሁፍ በአሁኑ ወቅት የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት፣ የሀገሪቱ የህግ አካል የሆኑት ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና እነዚህን መሰረት አድርገው የወጡ አዋጆች ፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ የሚያትቱትን እንመለከታለን።

 

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት


በህገ መንግስቱ አንቀፅ 29 ስር ሃሳብን የመግለፅ እና የፕሬስ ነፃነት የተረጋጠ ሲሆን ይህ አንቀፅ በዝርዝር ማንኛውም ሰው ሃሳብን በነጻነት የመያዝ እና የመግለፅ መብት እንዳለው፣ የፕሬስና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በነጻነት እንዲሁም የስነ ጥበብ ፈጠራ ነፃነት የተረጋገጠ መሆኑ፣ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑ፣ ሁሉም ሰው የህዝብ ጥቅምን የሚመለከት መረጃ የማግኘት እድል የተሰጠው መሆኑ እና የመሳሰሉት በህገ መንግስቱ ውስጥ ተካተው የሚገኙ መብቶች የፕሬስ እና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቶችን በተሻለ ያረጋገጡ ናቸው። በተጨማሪም ማንም ሰው በማናቸውም ዘዴ ሃሳብን በነፃነት የመሰብሰብ እና የማሰራጨት መብት ተረጋግጦለታል።


ሌላው ከፕሬስ ነፃነት ጋር በተያያዘ የተሰጠው ህገ መንግስታዊ መብት የህዝብ ጥቅምን የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብት ሲሆን በተጨማሪም ለነፃው ፕሬስ መረጋገጥ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ ተከልክሏል። ከእነዚህ መብቶች ጋር በተያያዘ ህገ መንግስቱ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሃሳቦች እና አመለካከቶች በነጻ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነትና የተለያዩ አስያየቶችን የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የህግ ጥበቃ እንደሚደረግለት በመደንገግ በሀገሪቱ የተሻለ የፕሬስ ነፃነት ይሰፍን ዘንድ የህግ ከለላ ለፕሬስ አካሉ መስጠት እንደሚገባ አስቀምጧል።


ሆኖም እነዚህ መብቶች ያለገደብ የሚተገበሩ አይደሉም። ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 29/6/ ስር የፕሬስ ነፃነት እና ሃሳብን መግለፅ በመብትነትም ሆነ በነፃነት በማረጋገጥ በኩል ገደብ ሊጣልባቸው የሚችልባቸውን ሁኔታዎች አስቀምጧል። ሃሳብን በነፃነት በመግለፅ በኩል የሚኖር ህገ መንግስታዊ ገደብ በዋናነት የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል በሚወጡ ህጎች መሰረት ሊፈፀሙ የሚችሉ ናቸው።


በተጨማሪም በዚሁ አንቀፅ ስር የጦርነት ቅስቀሳዎችን እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በህግ ሊከለከሉ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ይህን በማጠናከር ህገ መንግስቱ የፕሬስ አካሉም ሆነ ማንኛውም ዜጋ ከላይ በተረዘሩት መብቶች አጠቃቀም ረገድ የሚጣሉ ህጋዊ ገደቦችን ጥሶ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን በአንቀፅ 29/7/ ስር ይገልፃል።


በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች የኢፌዴሪ ህገ መንግስት የፕሬስ እና ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን በተመለከተ እንዲሁም በእነዚህ መብቶች ላይ ሊጣሉ የሚችሉ ገደቦችን በተመለከተ በአንቀፅ 29 ስር በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው ከፕሬስ ነፃነት እና መገናኛ ብዙሃን ጋር በተያያዘ የተሰጡ መብቶችን ሲተገብር እነዚህን ህገ መንግስታዊ ገደቦች ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ እና በሀገሪቱ መብቶቹን ለማስፈፀም የሚወጡ ህጎችም ሆነ መመሪያዎች የህገ መንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎች የተከተሉ መሆን እንዳለባቸው መረዳት ይቻላል።

ዓለም አቀፍ ስምምነቶች


ኢትዮጵያ ዋንኞቹን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ዓለም አቀፍ ሰነዶችን ያፀደቀች ከመሆኑም በላይ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9/4/ ስር እነዚህን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ የህግ አካል መሆናቸው ተደንግጓል። በተጨማሪም በአንቀፅ 13/2/ ስር በህገ መንግስቱ የተዘረዘሩት መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም እንዳለበት በመደንገግ እውቅና ሰጥታለች። እነዚህ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ስለ ፕሬስ ነፃነት የሚያትቱትን እንደሚከተለው እንመለከታለን።

የሰብአዊ መብቶች ሁሉ አቀፍ መግለጫ


ይህ መግለጫ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሀገሮች ላይ ተፈፃሚነት ያለው የሰብአዊ መብት መግለጫ ሲሆን በአንቀፅ 19 ስር «ማንም ሰው አስተያየት የመስጠት ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት እና መብት አለው። ይህ መብት እንያንዳንዱ ሰው ያለምንም ተፅህኖ አስተያየት እንዲኖረውና እና ጠረፍ ሳይወሰነው በማናቸውም ዓይነት መሳሪያ መረጃዎችን ወይም አሳቦችን የመፈለግ የመቀበልና የማስተላለፍ ነፃነትን ይጨምራል» በማለት ሰዎች ነፃ የሆነ ሃሳብን የመግለፅ እና የማስተላለፍ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።

የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን


ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች መሀከል አንዱ ሲሆን የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ አንቀፅ 19 የሚከተለውን ይደነግጋል፣ ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሱን አስተያየት ሊኖረው መብት አለው፣ ማንኛውም ሰው ሃሳቡን የመግለፅ ነፃነት አለው፣ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 ስር የተደነገጉ መብቶች ያጠቃቀም ሁኔታ ልዩ ግዴታዎችን እና ሃላፊነቶችን አብሮ ይዟል። በዚህም ምክንያት የተወሰኑ ገደቦች ሊደረጉበት ይችላል። ይሁን እንጂ ገደቦቹ በህግ በተደነገጉ እና የሌሎች መብቶችንና ክብርን ለማስጠበቅ፣ የብሔራዊ ፀጥታን፣ የህዝብን ደህንነት ወይም ጤናን ወይም ሥነምግባርን ለማስከበር መሆን አለባቸው። ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው ከፕሬስ እና መገናኛ ብዙሃን ነፃነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው መብቶች ማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ፣ መረጃን ያለምንም የድንበር ገደብ የመፈለግ፣ የማግኘትና የማስተላለፍ መብቶች ለሁሉም ስው የተሰጡ ቢሆንም እነዚህ መብቶች ግን ፍፁማዊ እና ያለምንም ገደብ ሊተገበሩ የሚችሉ አለመሆናቸውን ይልቁንም በህግ በተደነነገ ጊዜ የሌሎችን መብት ለማስጠበቅ እና ብሔራዊ ፀጥታን፣ የህዝብ ደህንነት፣ ጤናን ወይም ስነ ምግባርን ለማስከበር መንግስታት በህግ ይህን መብት ሊገድቡ እንደሚችሉ በዚህ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ላይ የተቀመጠ ነው።

 

የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች መብቶች ቻርተር


የሰዎች ሃሳብን በነፃ የመግለፅ እና የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ ይህ ቻርተር በአንቀፅ 9 ስር የሚከተለውን አስፍሯል። ማንኛውም ሰው መረጃ የማግኘት መብት አለው፤ ማንኛውም ሰው ህግን ተከትሎ ሃሳቡን የመግለፅና የማሰራጨት መብት አለው ይላል። በዚህም መሰረት ሁሉም ሰው መረጃ የማግኘት፣ ሃሳቡን የመግለፅ እና የማሰራጨት መብት እንዳለው ሲደነግግ ነገር ግን ይህን መብት ለማስፈፀም የሚወጡ ህጎችን መሰረት በማድረግ ሊተገበር የሚገባ መሆኑን ይገልፃል። በአጠቃላይ ከላይ እንደተመለከተው ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው እና የሀገሪቱ የህግ አካል የሆኑ በእነዚህ ዓለምአቀፍ ስምምነቶች ውስጥ የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ የተደነገጉ መብት እና ግዴታዎች በሀገሪቱም ተፈፃሚነት አላቸው። በመሆኑም የፕሬስ ነፃነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት እነዚህ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከፍተኛ ሚና ስለሚኖራቸው ታሳቢ ሊደረጉ ይገባል።


የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነጻነትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 590/2000


ይህ አዋጅ መነሻ ካደረጋቸው በርካታ መሰረታዊ ዓላማዎች መካከል በዜጎች መካከል የሚደረገውን ነጻ የሃሳብ እና የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን የአሰራር ነጻነት ላይ መሰናክል የነበሩ መዋቅራዊ ችግሮችን ማስወገድ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ ታላቅ ሚና መጫወት የሚችል ራሱን በከፍተኛ ስነምግባር እና የሙያ ብቃት ያነጸ ዘርፈ ብዙ የመገናኛ ብዙሃን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ መታመኑ በዋናነት ይገኝበታል። በተጨማሪም በአዋጁ መግቢያ ላይ ይህ አዋጅ የወጣው የወጣቶችን ደህንነት የሰውን ክብርና መልካም ስም፣ ብሄራዊ ደህንነትን፣ የህዝብን ሰላምና ጸጥታን እንዲሁም ሌሎች ተነጻጻሪ መብቶችና ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ሲባል በግልጽ በሚደነገጉ ህጎች ብቻ ሃሳብን በነጻ የመግለጽና በመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ላይ ገደቦች እንዲጣሉ የሚያዘውን ህገመንግስታዊ መርህ በማረጋገጥ መሆኑን ተገልጿል።


በዚህ አዋጅ የመገናኛ ብዙሃን ማለት በየጊዜው የሚወጡ የህትመትና ብሮድካስቶችን የሚያካትት የህትመት ስራ እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶታል። ይህ አዋጅ በአብዛኛው ፕሬሱ መረጃን ጠይቆ የማግኘትና ይህ መረጃ ወይም ሃሳብን የመግለጽ መብት እንዴት እንደሚተገበር የሚያተት ነው።


በቅድሚያ አንቀጽ 4 የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት የሚያብራራ ሲሆን በዚህም የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑ፤ በመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ላይ ገደቦች የሚጣሉት ህገመንግስቱን መሰረት በማድረግ በሚወጡ ህጎች ብቻ መሆኑን እና ማንኛውም የመንግስት አካል የመገናኛ ብዙሃን ማህበራዊ ተግባራቸውን ለመወጣት፤ ዜና ወይም መረጃን የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ፤ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ወይም ትችት የማቅረብ፤ የተለያዩ ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም የህዝብን አስተያየት በመቅረጽ ሂደት የመሳተፍ መብታቸውን ማክበር እንዳለበት ይደነግጋል።


                                                                                                                            (በሰላማዊት ተሰማ ከፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ)

 

የህወሓት/ ኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 35 ቀናት ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ስትራቴጂካዊ አመራር ክልላዊና ሃገራዊ ተልእኮውን ከመወጣት አንፃር ያለበት ቁመና ለማየት የሚያስችል ስር ነቀል ግምገማ አካሂዷል። ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ከመገንባት፤ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ መዋቅራዊ ለውጥ ከማረጋገጥ፣ የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከመመለስ አንፃር ያሉበት መሠረታዊ ክፍተቶችንና አዲስቷን ፌዴራላዊት ዴሞክሰራሲያዊት ኢትዮጵያ ከመገንባት አኳያ የተጋረጡ አሳሳቢ አዝማሚያዎች በጥልቀት ገምግሟል። ይህን መሰረት አድርጎ ባደረገው ሂስና ግለሂስ ተከትሎ የእርምት እርምጃ በመውሰድና የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ተጠናቋል።


እንደሚታወቀው ሁሉ ህወሓት የትጥቅ ትግል ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በየደረሰበት የትግል ምእራፍ ውስጥ ሁሉ የሚገጥሙትን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች በስከነ ሳይነሳዊ ኣመራርና በኣባላቱና በህዝብ የተማላ ተሳትፎ በአስተማማኝ እየመከተ ለድል የበቃ ድርጅት ነው። የህዝብን ፀረ-ጭቆና፣ ፀረ ኃላቀርነትና ፀረ-ድህነት ትግል ለስኬት ለማብቃት የሚያስችሉ የጠራ መስመር፣ መስመሩን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ስትራተጂዎችና ስልቶችን እየቀየሰ ከኣንድ የትግል ምዕራፍ ወደ ሌላው የትግል ምዕራፍ ለመሸጋገር የቻለበት ምስጢር ግልፅ ነው። ህዝባዊ ወገንተኝነቱ አስተማማኝ የሆነ፣ ፈተናዎች በገጠሙት ቁጥር ራሱን በሚገባ እየፈተሸና ወቅቱ የሚጠብቀውን ፤ ማንኛውንም የእርምት እርምጃ እየወሰደ ጥንካሬዎቹን የሚያጎለብት ድክመቶቹ ያለምህረት በማስወገድ በመስዋእትነት የደመቀ ታሪክ መስራት የቻለ ኣመራር ባለቤት በመሆኑ ነው።


ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ከእህትና አጋር ድርጅቶችና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን በከፈሉት እጅግ ከባድ መስዋእትነት አዲሱቷን ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ችለዋል። በአገራችን ታሪክ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የህዳሴ ምዕራፍ ከፍቷል።


ይሁንና በትጥቅ ትግልም ወቅት ሆነ በልማትና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንቅስቃሴያዎችን እጅግ የሚያኮራ ተግባራትን የፈፀመ ድርጅት ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ከችግር ኣዙሪት መውጣት አቅቶት የሚንገዳገዱበትና ለህዝብ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ላይ ሰፊ ድክመት እያሳየ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥረዋል። በተለይም ካለፉት ጥቂት ኣመታት ወዲህ ስትራቴጂካዊ ኣመራሩ እየተዳከመ ተልእኮውን ለመወጣት የሚያስችል ቁመና፣ ኣመለካከትና ኣደረጃጀቱ በየጊዜው እየተሸረሸረ፣ ህዝባዊነቱ እየቀነሰ፣ የህዝብን ችግር በማያወለዳ መልኩ ሳይፈታ በትንንሽ ድሎች የሚረካ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት የመፍትሔ አካል ከመሆን ይልቅ የችግር ምንጭ መሆን የጀመረበት ሁኔታ በስፋት መታየት ከጀመረ ውሎ ኣድራል። ይህንን ቁመና ይዞ መስመሩንና የመለስን ለጋሲ ማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ እንደሌለ በግልፅ አይቷል።


ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ማእከላዊ ኮሚቴው ከገባባት ኣዙሪት ለመውጣት ያለው ብቸኛ አማራጭ በድርጅት የቆየ ሳይነሳዊ የትግል ባህልና ታሪክ መሰረት በቁጭት ተነሳስቶ ጥልቀት ያለው የአመራር ግምገማ ማድረግ ብቻ እንደሆነ በማመን በኣፅንኦት መክራል። ያጋጠሙትን ፈተናዎች በጥሞና መርምሮ ድርጅቱን በማያዳግም ሁኔታ ወደ ትክክለኛው መስመሩና ህዝባዊ ወገንተኝነቱ ለመመለስ በሚያስችለው መልኩ ራሱን በጥልቀት ፈትሿል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስደረጉ ከነበሩት የይስሙላ ግምገማዎች በዓይነቱና መልኩ በተለየ ችግሮቹን በሚገባ ለመለየት ያስቻሉት መተጋገል አካሂዷል።


ወደ ግምገማ ሲገባ አሁን በስራ ላይ ያለውና ተተኪው አመራር በጋራ ትኩረት ሰጥቶ ያየው ጉዳይ ከገባበት የአመራር አዙሪት ውስጥ ለመውጣት በተለመደው መንገድ መሄድ በፍፁም የማይዋጣ መሆኑን በመገንዘብ ከተለመደው ግምገማ ለመውጣት ያስችላል ተብሎ የታመነበትና ስፋትና ጥልቀት ያለው ክርክር የጋበዘ የድርጅቱን ኣጠቃላይ ሁኔታና የኣመራሩን ድክመት በሚገባ የፈተሻ ሰነድ ለኣመራሩ ቀርቦ ሰፊ ውይይትና ክርክር ተደርጎበታል።


በዚህ መድረክ በቀረበዉ ሰነድ ላይ ተመስርቶ በተደረገ ጥልቅ ዉይይት የህዝባችንና የመላው አባላችንን ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመመለስ ያልተቻለው በዋናነት ስትራቴጂክ አመራሩ ከገባበት አዙሪት ውስጥ መውጣት አቅቶት ሲዳክር በመቆየቱ መሆኑን የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አረጋግጧል።


አመራሩ የሃሳብና የተግባር አንድነት የጎደለው፣ ፀረ ዴሞክራቴክ ተግባርና አስተሳሰብ ውስጥ በስፋት የተነከረ፣ በተልዕኮ ዙርያ በመተጋገልና በመርህ ላይ የተመሰረተ አመራር የማይሰጥ፣ ህዝብንና አላማን ከማስቀደም ይልቅ የራሱን ክብርንና ጥቅም የሚያስቀድም መሆኑ ታይቷል። ለህዝብ ያለው ወገንተኝነት እየተሸረሸረ፣ ከኣገልጋይነት ይልቅ ራሱን እንደ ተገልጋይ እየቆጠረ፤ መዋቅራዊ ለውጥ በሚያመጡ ስኬታማ የህዝብ ዙርያ መለስ እንቅስቃሴ ከመጠመድ ይልቅ በተደማሪ ለውጦች የሚረካና በውሸት ሪፖርት ራሱን መሸለም የሚቃጣው አመራር እየሆነ በአጠቃላይ ራሱን ወደ ጥገኛ ገዢ መደብ የመሸጋገር አዝማሚያ የተጠናወተው መሆኑን በትክክል አስቀምጧል።


ይህ የስትራተጂካዊ አመራር ድክመት በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግቦቻችን አፈፃፀም ላይ እጅግ ከባድ ተፅእኖዎች ፈጥረዋል። በህዝብ ዙርያ መለስ ተሳትፎና በጠራ መስመር ማስመዝገብ የጀመርናቸውን በርካታ ለውጦች ማስቀጠል ያልተቻለበት አንዳንዴም ወደሃላ መመለስ የጀመሩበት ሁኔታ እንደነበረ በጥልቀት ታይታል። ሁሉንም የልማት ሃይሎች በተደራጀ መልኩ በመምራት ረገድ የነበረውን ሰፊ ክፍተትንም ኣይቷል። ወጣቶች ፣ ምሁራን፣ ሴቶችና ሌሎችም የሞያ የማሕበራትና መሰል ኣደረጃጀቶች የለውጥ ባለቤት ሆነው የሚውጡበትን ዕድል በማምከን ድርጅቱን በቀጣይነት የሚመራ ብቁ ሃይል እንዳይፈጠር እንቅፋት የሆነ ኣመራር መሆኑንም በሚገባ ተረድቷል። ህዝቡ በድርጅቱ ላይ የነበረዉን እምነት እንዲሸረሸርም ትልቅ አስተዋፅኦ ኣድርጓል።


በአመራሩ ዘንድ የታየው ድክመት በህዝብ ዘንድ ካስከተለው ከፍተኛ የአመኔታ መሸርሸር ችግር በተጨማሪ በከተማም በገጠርም በጀመርናቸው ትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ ሰራዎቻችን ለአደጋ ያጋለጠ እንደነበረ ማእከላዊ ኮሚቴው ገምግሟል። በገጠርም በከተማም የቀረፅናቸው ፖሊስዎችና የቀየስናቸው ስትራተጅዎች ትክክለኝነት ላይ የሚያጠራጥር ነገር ባይኖርም ኣፈፃፀማችን የደረሰበት ደረጃ ባቀድነው ልክ ኣስተማማኝ መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ በህዝባችን ዘንድ ተገቢ ጥርጣሬ እንዲያድርበት ማድረጉም በትክክል ለይቷል። በገጠር የእርሻ ትራንስፎርሜሽን፣ በከተማ የኣነስተኛና ጥቃቅን ልማት፣ የከተሞች እድገት፣ የወጣቶች እና ሴቶች ስራ ፈጠራ እንዲሁም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት ባቀድነዉ ልክ ላለመመዝገቡ የስትራተጂክ አመራሩ ድክመት ዋናውን ድርሻ እንደሚወስድ ገምግሟል።

 

የችግሩን ጥልቀትና የኣመራሩን ሁኔታ በስፋት ከገመገመ በኃላ ማእከላይ ኮሚቴው ለተፈጠረው የአመራር ችግር ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት በማመን ቀጥሎ ያከናወነው በመላው የማእከላይ ኮሚቴው ኣባላት የሚደረግ የሰላ ሂስና ግለሂስ ነው። ለተፈጠረው ችግር ማእከላዊ ኮሚቴው በኣጠቃላይ ተጠያቂ ቢሆንም የችግሩ የከፋ መገለጫ የህወሓት ስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ እንደ ኣካልም ሆነ እንደ ግለሰብ ኣመራሩ መሆኑን በመውሰድ ጥልቅ የሂስና ግለ ሂስ መድረክ ኣካናውኗል። የሂስና ግለሂስ መድረኩ አላማ በግለሰብ ኣመራር አባላት ላይ ያተኮረ ሳይሆን ድርጅቱ ካለዉ ስትራተጂካዊ ፖለቲካዊ ተልእኮ አንፃር እያንዳንዱ አመራር ሃላፊነቱን የተወጣበትን ደረጃ እና ልክ በትክክል ለመገንዘብ እና አስፈላጊዉን የእርምት እርምጃ ለመዉሰድ ያለመ ነበር። ሂደቱም በግልፅነት ፣ በሙሉ ተሳትፎና በቁጭት መንፈስ የተከናወነ ሲሆን በመጨረሻም መላዉ አመራር ዘንድ በተደረሰበት ድምዳሜ ዙርያ የጋራ መግባባት የተያዘበት ሁኔታ ተፈጥራል።


ማእከላይ ኮሚቴዉ የሂስና ግለሂስ ሂደቱን ካከናወነ በኃላ በድርጅቱ ስትራቴጂክ አመራር ዘንድ በስፋት ይስተዋል የነበረዉን የሃሳብና የተግባር አንድነት ችግር ስር ነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት የሚያስችል መግባባት ላይ የተደረሰበት የአመራር ሽግሽግ በማድረግ የተሃድሶው ስትራቴጂክ አመራር ተጠናክሮ የወጣበት የተመቻቸ ሁኔታ ፈጥሯል።

 

የተከበራችሁ የድርጅታችን አባላት፣ አርሶ አደሮችና የከተማ ነዋሪዎች:-
ህወሓት የትግራይ ህዝብ የትግል ውጤት እና መሪ ድርጅት ነው። ጥንካረው ለህዝቡ ካለው ታማኝነትና ወገንተኝነት የሚመነጭ ነው። ህወሓት ፈተናዎች ባጋጠሙት ቁጥር ከህዝብና አባላቱ ጋር በመሆን ችግሩን እየፈታ ለበርካታ አስርት ዓመታ ዘልቋል። ባለፉት ዓመታት ጥያቄዎችህን በመፍታት ረገድ የህወሓት አመራር ከፍተኛ ድክመት አሳይቶም ጭምር በትዕግስት እና በተስፋ መጠበቃችሁ ድርጅቱ ይገነዘባል። ማእከላይ ኮሚቴው ችግሩን በሚገባ ተረድቶ የናንተን ጥያቄዎችንና ፍላጎቶች ለመፍታት፣ በህዝብ ዘንድ በብዙ መልኩ ተሸርሽሮ የነበረውን አመኔታ ለማሳደስ የሚተጋ፣ በሃገር ኣቀፍ ደረጃ ሊኖረን የሚገባውን ገንቢ ሚና ለማስቀጠል ዝግጅነቱ፣ ተኣማኒነቱና ፅናቱ ያለው፤ ስኬቶቻችንን ለማስቀጠል የቆረጠና ቀጣዩን ጉባኤ ኣሳታፊ በሆነ መልኩ ለማከናወን የሚያስችል ስራዎችን የሚሰራ ኣመራር እንደሚሆን ኣንጠራጠርም። አመራሩ በጊዜ የለም መንፈስ ከመላው አበላችንና ህዝባችን ጋር በሚደርገው ጥልቅ ውይይት ያስቀመጣቸው ኣቅጣጫዎች በበለጠ ለማበልፀግ የሚያስችል ስራ የሚሰራ ይሆናል።


የጉባኤ ዝግጅታችን መላው አባላችን፣ ምሁራን፣ ወጣቶች ፣ ሴቶችና ቡዙሃን ማሕበራትን በነፃነት ባሳተፈ መልኩ እንዲካሄድና በተመረጡ የህዝብ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ ለማካሄድ የሚያስችል ዙርያ መለሽ ዝግጅት የሚደረግ ይሆናል። እንደተለመደው ሁሉ አሁንም ከጎናችን ቁማቹህ ለጥቅማቹህ መረጋጥ እንድትታገሉ ድርጅታቹ ህወሓት ጥሪውን ያቀርባል።

የተከበራችሁ የክልላችን ምሁራንና ልማታዊ ባለሃብቶች:-


የህወሓት/ ኢህአዴግ አመራር በሚፈለገው ደረጃ የተመቻቸ ሁኔታ ባለመፈጠሩ ምክንያት በክልላችሁና በሃገራችሁ ጉዳይ ላይ በሚገባው ደረጃ ያላሳተፍናችሁ መሆኑን ተገንዝቧል በመሆኑም ጥያቄያችሁን ለመመለስ የራሳችሁን የተሟላ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ህወሓት/ኢህአዴግ ምሁሩና ባለሃብቱ በመሰላችሁ አደረጃጀት ውስጥ ሁናችሁ ተዋናይ የምትሆንበት ተቋማዊ መሰረት በማስቀመጥ ከልቡ የሚሰራ ይሆናል። በጥናትና ምርምርም ሆነ በልማት የክልላችንም ሆነ የሃገራችን ልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ባለቤት የምትሆኑበት ሁኔታ ይመቻቻል።

የተከበራችሁ የክልላችን ወጣቶችና ሴቶች:-


በክልላችን ልማትም ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላችሁ ተሳትፎ ለሃገራችን ዕድገትና ህዳሴ መረጋገጥ ወሳኝ ነው። ከምንም በላይ የተጠቃሚነትና የተሳታፊነት ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ ድርጅታችሁ ህወሓት/ኢህአዴግ ቃል ይገባል፤ እናንተን በፅሞና ለማዳመጥና ለማታገል የሚያስችሉ መድረኮችንም ያመቻቻል።

ዉድ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች:-


በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙርያ ህዝባችን ለከፍተኛ ምሬት የዳረጉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በኣመራሩ ድክመት የተፈጠሩ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅታችን ህወሓት/ ኢህአዴግ በአገር ደረጃ በሚደረጉ የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎቻችን በማሳካት ረገድ ሲጫወት በመጣው ሚና ላይ ኣሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩንም በሚገነባ ይገነዘባል። የአመራር ድክመት በህወሓት ውስጥም ሆነ በክልላችን በሚደረጉ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጥረቶች ላይ ጉዳት ከማድረሱ በተጨማሪ በእህትና በአጋር ድርጅቶች መካከል ለበርካታ ኣስርት ኣመታት የነበረውን በመርህ እና በትግል ላይ የተመሰረተ ውህደት፣ ለዙርያ መለሽ ስኬት ያበቃን የአመለካከትና የተግባር ኣንድነት በየጊዜው እየተሸረሸረ እንዲመጣና በጋራ ዓለማ ዙርያ በአንድ ልብና መንፈስ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በንትርክና በጥርጣሬ መተያየት ያጠላበት እንዲሆን በማድረግ በኩል የራሱን ኣሉታዊ ኣስተዋፅኦ እንደደረገ በትክክል ኣስቀምጣል።

 

ሁሉንም አቅሞቻችን፣ የህዝባችንን ፍትሓዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ የጠሩ ፖሊሲዎቻችን ሲኬታማ ኣፈፃፀም ላይ ከማድረግ ይልቅ የፌዴራል ስርዓት ጠላቶች ባጠመዱልን ወጥመድ ውስጥ ገብተን የሃገራችንን ኢትዮጵያ ህልውና ፈተና ላይ እንዲወድቅ በማድረግ ረገድ በህወሓት ኣመራር ዘንድ የታየው ድክመት የማይናቅ ሚና እንደነበረው በግልፅ ይረዳል። የፈዴራል ስርዓቱን ለመናድ ከውስጥም ከውጭም የተሰባሰቡ ጥገኛ ሃይሎችን በጋራ የመመከት ኣቅማችን እየተመናመነ በተመሳሳይ ፕሮግራምና ልማታዊ መስመር ዙርያ የተሰለፉ ሃይሎች የጋራ ትግላቸዉ መደነቃቀፍ የጀመረበት ሁኔታ ተፈጥራል። በኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶች ውስጥ ለሚታዩ ችግሮች ዋነኛው ተጠያቂነት ለየድርጅቱ ኣመራር የሚተው ቢሆንም በህወሓት ኣመራር ውስጥ ይታዩ የነበሩ ኣዝማሚያዎች ለብዙ ኣስርተ ዓመታት በእሳት ጭምር ተፈትኖ የመጣውንና ለሃገራችን ኢትዮጵያ ልማትና ዴሞክራሲ እውን መሆን ምክንያት የሆነው አብዬታዊና ዲሞክራሲያዊ አንድነት በመሸርሸር ረገድ የማይናቅ ድርሻ እንዳነበረው ማእከላዊ ኮሚቴው ባደረገው ግምግማ ኣረጋግጧል።


ህወሓት ከእህት እና አጋር ድርጅቶች ያለውን ግንኝነት በመርህና በመተጋገል ላይ በመመስረት የሚታደስበት የነበሩ የርስ በርስ መጠራጠሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ኣቅጣጫዎችን የሚከተል ይሆናል።

ዉድ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች፣ ላብአደሮች፣ ልማታዊ ባለሃብቶች:-


ህወሓትና የትግራይ ህዘብ ከሌሎች እህትና ኣጋር ድርጅቶች እንዲሁም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን ለእኩልነትና ለፍትሓዊ ተጠቃሚነት የከፈሉት እጅግ ከፍተኛ መስዋዕትነት ሳይበቃውና ተከታታይ ገዢዎች ያሲረፉበት ቁስል በወጉ ሳያገግም ለሌላ የተቀናጀ ጥቃት የሚጋለጥበት ሁኔታ ከመፍጠር ኣንፃር የህወሓት ኣመራር ውስጥ የታየው ድክመት የማይናቅ ኣስተዋፅኦ ኣድርጓል።


አሁንም ቢሆን ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ያመጣቸዉን ትሩፋቶች ጠብቆ የተሻለ ብልፅግና የሰፈነባት እና ህዳሴዋ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ዉስጥ ድርሻዉን ኣጠናክሮ ይቀጥላል። ከዉጭም ከዉስጥም የሚቃጡብንን አፍራሽ ጥቃቶች ለመመከት ከመላዉ የሃገራችን ህዝቦች ጋር በቅርበት ይሰራል። በአሁኑ ሰአት በየአካባቢዉ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትና የህዝቦች የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የልማት ጥያቄ በተገቢዉ መንገድ ለመመለስ በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ ድርሻዉን ለማበርከት ዝግጅነቱን ይገልፃል። ህወሓት/ኢህኣዴግ የጋራ ሃገራችንን በሆነችው ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የተጫወተውን ገንቢ ሚና ኣጠናክሮ ለመወጣት የሚያስችለውን ኣቅጣጫዎች ከህዝቦች ጋር በመመካከር የሚያከናውን ይሆናል። ዲሞክራሲያዊ አንድነታችሁን አጠናክራችሁ አፍራሽ አጀንዳዎቻችውን ለማሳካት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚዳክሩ ጠላቶችን በጋራ እንድንመክት ጥሪውን ያቀርባል።


የህወሓት ማ/ኮሚቴ
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማእታት
ህዳር 21/2010 ዓ.ም
...
የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና ማዕከላዊ ኮሚቴ በጥልቀት ሲያካሂድ የቆየውን የሂስና ግለ ሂስ መድረክ እና የድርጅቱን ቁልፍ አመራር መልሶ ማደራጀት ዛሬ አጠናቋል።
የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአዲስ መልኩ የተደራጀ ሲሆን በዚህም መሰረት:-


1. ጓድ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)
2. ጓዲት ፈትለወርቅ ገ/እግዛብሄር
3. ጓድ ኣለም ገ/ዋህድ
4. ጓድ ኣስመላሽ ወ/ስላሴ
5. ጓድ ጌታቸው ረዳ
6. ጓድ ኣዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር)
7. ጓዲት ኬርያ ኢብራሂም
8. ጓድ ኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር)
9. ጓድ ጌታቸው ኣሰፋ የህወኃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነዋል።
ጓድ ደብረፂዮን የህወሓት ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡ ሲሆን ጓዲት ፈትለወርቅ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።¾

 

“ያለፍኩበት” ለንባብ በቃ

Wednesday, 06 December 2017 13:04

“ያለፍኩበት” ለንባብ በቃ

 

በዶ/ር ፍሰሃ አስፋው የተዘጋጀው “ያለፍኩበት” የተሰኘው መጽሀፍ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ለንባብ በቅቷል። 267 ገፆች ያሉት መፅሐፍ የፀሐፊውን ግለ ታሪክ፣ የኢትዮጵያ አርበኞች በኮንጎ ዘመቻ የፈፀሙትን ተግባር፣ በአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ላይ የተነሳውን ጥያቄ ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም እንዴት እንደቀለበሱት፣ በ1997 ዓ.ም ስለተካሄደው ምርጫ እና አሁን ያለውን መንግሥት የአስተዳደር ሥርዓት በስፋት የሚዳስስ ነው። በከላር ማተሚያ ቤት ታትሞ ለገበያ የቀረበው መፅሐፍ 81 ብር ለመሸጫ የተቆረጠለት ዋጋ ነው።

 

በይርጋ አበበ

 

በኢትዮጵያ ጀግኖች አባቶችና እናቶች ተጋድሎ ላይ ያተኮረው የሽለላ እና የአገር ፍቅር ገላጭ ሙዚቃ ለገበያ የቀረበው ባሳፍነው ሳምንት መጀመሪያ ነው።

በሙዚቃ ሥራው የዜማ ደራሲ እና የሙዚቃ አቀናባሪውን የኔው አካሉን ጨምሮ በርካታ እውቅ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በፋሽስት ጣሊያን ወረራ የህይወትና አካል መስዋዕት ለከፈሉት አባት እና እናት አርበኞች መታሰቢየ የተዘጋጀው ይኸው የሙዚቃ አልበም፤ በተለይ ለሰማዕቱ አርበኛ “ስምኦን አደፍር”ስ መታሰቢያ ውሏል። አልበሙን ጎልድ ሊፍ የሙዚቃ ማዕከል አሳትሞ አከፋፍሎታል።

 

አርአያ ጌታቸው


«የግብፅ የውሃ ድርሻ የማይሻር ነው። እንደ ግብፅ ፕሬዚዳንት የማረጋግጥላችሁም ግብፅ የናይል ስጦታ፤ ናይልም የግብፅ ስጦታ መሆኑንና ይሄንን ለማስከበርም ሁሉም ዓይነት አማራጭ እንዳለን ነው» ፕሬዚዳንት ሙርሲ እ.ኤ.አ. ጁን 2013 የተናገሩት፡፡


«ለእኛ ውሃ የልማት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የህይወት እና የሞት ጉዳይ ነው፡፡ ሀገራዊ ደህንነታችንን የማስጠበቅ አቅሙ አለን፡፡ ለእኛ ውሃ የብሔራዊ ደህንነት ጥያቄ ነው፡፡ አራት ነጥብ። የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ›› ፕሬዚዳንት አልሲሲ እአአ በ2017 የተናገሩት፡፡


«ማንም ተናገረ ወይም አስፈራራን ብለን የምናቋርጠው ፕሮጀክትና የምንጀምረው ጦርነት የለም» ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ፡፡


«ለድርድር የሚቀርብ ግንባታ ስላልጀመርን የህዳሴን ግድብ ለድርድር አናቀርበውም» ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፡፡


«ፍትሐዊ ያልሆኑ ውሎችን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ተከታታይ መንግሥታት አልተቀበሏቸውም። ይኸም መንግሥት አይቀበልም።» የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እነዚህን ሁለት ተቃራኒ ሃሳቦች ልብ ብለን ስንመዝናቸው ብዙ የሚነግሩን ሃቅ አላቸው።


ግብፃዊያን የናይል ወንዝን የራሳቸውና የራሳቸው ብቸኛ ሀብት አድርገው ይቆጥራሉ። ይሄንን የተሳሳተ ስግብግብ አቋማቸውን ለማስከበር ደግሞ ዛሬም ድረስ በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ መሆናቸውን ንግግሮቹ ያሳብቃሉ። በተቃራኒው ኢትዮጵያ ምንም እንኳን እስከ 85 በመቶ የሚሆነው የወንዙ ውሃ ከግዛቷ የሚመነጭ ቢሆንም የጋራ ሀብት ነው በሚል መርህ እየተጓዘች የግብፅን ዛቻ ወደ ጎን ትታ በጋራ ለመልማት እንደምትሥራ ነው።


የናይልን ወንዝ በተመለከተ እንደ ግብፅ በተዛነፈ አቋም ላይ እንቁም ከተባለ የወንዙ ብቸኛ ባለቤት ወንዙ የሚመነጭባቸው አገራት ናቸው። ይህ ማለት ናይልን ናይል ያሰኙት ወንዞች የሚመነጩባቸው አገራት ሁሉ የወንዛቸው ብቸኛ ባለቤቶች ናቸው። በዚህ ስሌት ከሄድን ግብፅ ብቸኛ ሀብቷ የሚሆነው ከአገራቱ ተርፎ የሚፈሰው ውሃ ብቻ ይሆናል። የሚተርፍ ካለ ማለት ነው። ስለሆነም ስለ ብቸኛ የሀብቱ ባለቤትነት ማውራትና ይገባኛል ማለት በተገላቢጦሹ የዚህ ዓይነት እውነት እንዳለው ግብፅና ግብፃዊያን ሊያውቁት ይገባ ነበር። እንደ አለመታደል ግን ግብፃዊያን ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብና ውል ለመውጣት ዝግጁ አይደሉም።


እኛ ግን ኢትዮጵያዊያን ነን፤ ነፃና ኩሩ አገር። ነፃ አገር መሆናችን ለቅኝ ግዛት ውልና አስተሳሰብ ቦታ እንዳይኖረን አድርጎናል። እንድንጠየፈውም ጭምር። ለዚህ ነው ግብፅ ዛሬም ድረስ እንደ ሞኝ ዘፈን እየደጋገመች የምታዜመውን የ1959ኙን የቅኝ ግዛት ዘመን ውል አናውቀውም፤ አንቀበለውም ማለታችን። ይሄ ደግሞ አገራችን ቀደም ብለው ያስተዳደሩት መንግሥታት ያልተቀበሉት፤ አሁን አገራችንን እያስተዳደረ ያለው መንግሥትም ያልተቀበለው ወደፊትም የሚመጣው መንግሥት የማይቀበለው ነው። ምክንያቱም ይሄንን ውል መቀበል ኢትዮጵያዊነትን መክዳት ነው። ይሄንን ውል መቀበል ቅኝ መገዛትም ነው። ስለሆነም የግብፅን የቅኝ ግዛት ውል እዚያው ለራሷ ስንል እንሞግታለን። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያ ነን፤ ነፃና ኩሩ ህዝብ። የቅኝ ግዛት ውል ይተግበርልኝ የሚል አገርና መንግሥት ካለ በቅኝ ግዛት ስር መተዳደር መብቱ ስለሆነ እዚያው በጸበሉ ከማለት ውጪ አማራጭ የለንም።


እንደ እኛ ግን ግብፃዊያን ማወቅ ያለባቸው መሬት ላይ ያለውን እውነታ ነው። መሬት ላይ ያለው እውነታ የናይል ወንዝ የእነሱ ብቸኛ ሀብት አለመሆኑ ነው። የናይል ወንዝ የ10 አገራት ሀብት ድምር ውጤት ነው። እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ እናንተ ተራቡ፤ እኛ ብቻ እንብላ ማለት የህግም የሞራልም ተቀባይነት አይኖረውም። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን ግብፃዊያን አሁን እያሉ ያሉት ይሄንን ነው። እናንተ ረሀብንና ድህነትን ለምዳችሁታልና እዚያው ቆዩ፤ እኛ ወደፊት ሊርበን ስለሚችል ወንዙን ተውልን። ይሄ ራስን ማሞኘት ነው። አፍሪካዊያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ድህነትን አምርረው መታገልና ማሸነፍ ጀምረዋል። ለዚያም ነው የተስፋዪቱ ምድር፤ አፍሪካ እየነቃች ነው እየተባለ የሚጻፈውና የሚነገረው። መንቃቱ አጠገብ ያለን ሀብት ከመጠቀም ይጀምራል። ይሄ ደግሞ ውሃንም ይጨምራ። የወንዝ ውሃን።


ግብፃዊያን የቅኝ ግዛት ውል ከግምት ውስጥ ይግባልን ከሚለው መከራከሪያቸው ጀርባ ያለው መከራከሪያቸው «እናንተ ሌላ የውሃ አማራጭ አላችሁ፤ እኛ ብቸኛ ሀብታችን እሱ ነው፤ ኢኮኖሚያችንም የግብርና ጥገኛ ነው፤ ግብፅ የናይል ስጦታ ናትና ተውሉን» የሚል ነው። እውነታው ግን ይሄ አይደለም። ይሄ የእነሱ የኖረና ያረጀ አስተሳሰብ ነው። በነገራችን ላይ ለዘመናት እንደዚህ በሚል ቅኝት ውስጥ ስላሉ ብዙዎችን የተፋሰሱን አገራት አሞኝተውና አሳምነው ኖረዋል። እውነታው ግን የግብፅ ኢኮኖሚ እንደሚባለው በግብርና ላይ ጥገኛ አለመሆኑ ነው።


መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከግብፅ ኢኮኖሚ እስከ 49 በመቶ የሚሆን ድርሻ ያለው የአገልግሎቱ ዘርፍ ነው። ኢንዱስትሪ የ13 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን የ8 በመቶ ድርሻ አላቸው። የፋኦ መረጃ የሚገልጸው እ.ኤ.አ. በ2010 የግብፅ ግብርና ለዓመታዊ የአገሪቷ ምርት የነበረው ድርሻ 13 ነጥብ 7 በመቶ ብቻ ነው። ከዚህ ዓመት በኋላ ያለውን የተደራጀ መረጃ ማግኘት ስላልቻልኩ መጠቀም አልተቻለኝም። ከተገኘው መረጃ መገንዘብ የሚቻለው ግን የአገሪቷ ኢኮኖሚ ከግብርና እየተላቀቀ መምጣቱን ነው። ስለሆነም ግብፅ የናይል ስጦታ ናት የሚለው አስተሳሰብ ፉርሽ ነው።


እንዲያውም አንድ አንድ መረጃዎች የሚገልጹት የአገሪቷ ኢኮኖሚ ዋነኛ ዋልታዎች ሬሚታንስ፣ ቱሪዝምና ስዊዝ ካናል መሆናቸውን ነው። ይህ የሚነግረን ግብፅ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያገኘች ያለውና ኢኮኖሚዋን እየደጎመች የምትገኘው እርሷ እንደምትለው በናይል ወንዝ ላይ በተመሰረተው የግብርናው ዘርፍ አለመሆኑን ነው። ይልቁንም ከቱሪዝም እና ከስዊዝ ካናል መተላለፊያ የምትሰበስበው ገንዘብ ላቅ ያለ ሆኖ ይታያል። እ.ኤ.አ. በ2016 ያለው መረጃ የሚያሳየው ግብፅ ከስዊዝ ካናል ብቻ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታገኝ፤ ከቱሪዝም ደግሞ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ወደካዝናዋ ጨምራለች። በተቃራኒው ግብርናዋ የቸራት ገንዘብ ይሄን አያክልም።


የጠቃቀስኳቸው እውነታዎች ሁሉ እውነት መሆናቸው ይቅርና በግብፅ በኖረ ፕሮፖጋንዳ ብናምን እንኳን፤ ግብፅ «ወንዙ የደህንነቴ ጉዳይ ነው፤ ውሃው ከቀነሰ እጠፋለሁ» የምትለው እውነት እንደምትለው የውሃ ችግር ኖሮባት አይደለም። ያማ ቢሆን ኖሮ ውሃውን በአግባቡ በተጠቀመችበት ነበር። በአሁኑ ወቅት ግብፅ በግዛቷ ውስጥ የምታካሂደው የውኃ አጠቃቀም ከህግ እና ከሥርዓት ውጪ የሚፈፀም ነው። ከዚህም በላይ የናይል ወንዝን ተፈጥሯዊ የጉዞ መስመር በማስቀየር(out of basin transfer) በረሃ ሳይቀር እያለማችና እየተጠቀመች እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው።


ከዚህም ባሻገር ግብርናዋ ውሃ አባካኝ እንጂ ቆጣቢ አለመሆኑም ይታወቃል። ስለሆነም እንደምትለው የውሃ ችግር ያለባት አገር ብትሆን ኖሮ አትንኩብኝ ከማለት ይልቅ እጇ ላይ ያለውን ውሃ በአግባቡ መጠቀም በተገባት ነበር።


መረጃዎች የሚነግሩን ግብፅ በአስዋን ግድብ አማካኝነት በያዘችው ውሃ በትነትና በስርገት እስከ 10 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እያባከነች ስለመሆኗ በጥናት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። የምታመርታቸው አብዛኛዎቹ የግብርና ምርቶችም ውሃን በብዛት የሚጠቀሙና አጠቃቀሙም እንደ ጠብታ ውሃ መስኖ ላሉ ቴክኖሎጂዎችን ባዳ የሆነ ነው። የግብፅ የውሃ አጠቃቀም ይሄ ሁሉ ገበና ባለበት ሁኔታ በፕሮፖጋንዳ ብቻ ውሃ ከቀነሰ አበቃልኝ ማለት ትዝብት ላይ ይጥላል። ተቀባይነትም የለውም።


ስለፍትሐዊነት ማውራት ካለብን ግብፅ ስለሚገባት የውሃ ድርሻ ብቻ ሳይሆን የናይልን ወንዝ ጥቅም ላይ የምታውልበት መንገድም ምን ያህል ከብክነት የፀዳና ፍትሐዊ ነው የሚለው መታየት አለበት። የአገራቱን የውኃ አጠቃቀም ሥርዓት በውል ተፈትሾ ባልታየበት ሁኔታ የህዳሴውን ግድብ ብቻ በተናጠል ወስዶ ስለፍትሐዊነት ማውራት ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ማለት ነው። እኛ ግን እንደ አገር የምንከተለው መርህ ፍትሐዊነትን ያገናዘበ ነው። የውሃው ባለቤት እኛ ነን፤ ብቻችንን እንጠቀምበት አላልንም። አባይ የደህንነታችን፣ የሞት ሸረት ጉዳያችን ነውም አላልንም፤ አንልምም። ምክንያቱም እኛ ተካፍሎ በመብላት የምናምን፤ ባርነት አምርረን የምንጠላ፣ በወዳጅነት የምናምን ህዝብና አገር ነንና።


ለመሆኑ የአባይ ወንዝ በተገላቢጦሽ ከግብፅ የሚመነጭ ቢሆን ኖሮ ግብፆች ውሃውን አሁን እኛ በጋራ እንጠቀምበት እያልን በፈቀድነው ልክ እንድንጠቀምበት ይፈቅዱልን ነበር? በጭራሽ። ለድርድርም እንደማይቀመጡ አሳምረን እናውቃለን። ምክንያቱም ግብፆች ሁሉም ይገባኛል የሚሉ፣ አፈር የገባውን ቅኝ ግዛት ቆፍረው አውጥተው የዚያ ዘመን ውል ይተግበርልን የሚሉ ራስ ወዳድ ናቸውና። ሀብታችን በእጃችን ላይ ሆኖ እንኳን እያሉን ያለውን የምናውቀው እኛው ነን።


በግሌ የምለው ግብፅ ዛሬም ድረስ በቅኝ ግዛት ውስጥ መሆኗን ነው። ምክንያቱም የቅኝ ግዛት ዘመን ውል ተግባራዊ ይደረግልኝ ማለት ከዚህ ሌላ ስያሜ ሊያሰጠው አይችልምና ነው። ግብፅን በተለያዩ ጊዜያት ያስተዳደሩት መሪዎቿም ይሄ እንደማያስኬድ እያወቁ እውነታውን ለህዝባቸው ነግረው ማስረዳት ሲገባቸው ዛሬም ድረስ ውሃው የደህንነታችን ጉዳይ ነው፤ ማንም አይነካውም እመኑኝ እያሉ በየአደባባዩ ይምላሉ። ለመሆኑ ግብፃዊያን እንዳይራቡ ኢትዮጵያዊያን ስንት ዓመት ይራቡ? ስንት አመትስ በድህነት ይማቅቁ? ይሄ ተቀባይነት የሌላው ንጽጽር ነው። ማንም መራብ የለበትም። ግብፅም፤ ኢትዮጵያም፤ የተፋሰሱ ሁሉም አገራት። ማንም። አራት ነጥብ።


ወንዛችን የተፈጥሮ ሀብታችን ነው። ነጩ ነዳጃችን፤ ከድህነት መውጫ አንዱ መንገዳችን። ስለሆነም ባሻን ጊዜ የምንጠቀምበት ባሻን ጊዜ ደግሞ የምንተወው እኛ ራሳችን እንጂ ማንም ሊሆን አይችልም። ማንም ስላስፈራራን ፕሮጀክቶቻችንን አንተውም፤ ማንም ስለማይረዳንም ገንዘብ አጥሮን ሥራውን አናቆምም። ምክንያቱም ተከዜንና ጣና በለስን ገንብተን የጨረስነው በግብፅ እየተመረቅን፤ በዓለም አገራትም እየተረዳን አይደለም። እየተዛተብን በራሳችን አንጡራ ሀብት ነው። አሁንም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለማንም ዕርዳታና በማንም ዛቻ ሳንዘናጋ ከዳር እናደርሰዋለን።


ግድቡ የእኛ ቀይ መስመራችን ነው። መንግሥትና ህዝብ ዳግም በምርጫ ውል ያሠሩት መንግሥት ግድቡን ከዳር እንደሚያደርስ ቃል ስለገባ ነው። ይሄንን ቃል አለመጠበቅ ዋጋው ምን እንደሆነ መንግሥት አሳምሮ ያውቃል ብዬ አምናለሁ። ይህ ግድብ የምንወዳት አገራችን ብሄራዊ ምልክቷ ነው፤ ሰንደቅ ዓላማዋም ጭምር። የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው የህግ ታራሚዎች ሳይቀር እያዋጡ የሚገነቡትን ይሄንን ምልክትና ሰንደቅ የሆነ ፕሮጀክት ማስተጓጎል አገራችንን እንደ መውረር ይቆጠራል። ለወረራ የምንሰጠው ምላሽ ደግሞ ምን እንደሆነ ታሪካችን ይናገራል። ስለሆነም ላንጨርስ የጀመርነው ግድብ የለም፤ አይኖርምም። ወዳጅ አገር ግብፅና ግብፃዊያን ፈቅደው ከገቡበት ቅኝ ግዛት ፈጥነው ይውጡ። ምርጫው ግን የእነሱ ነው። በዚህ አቋማቸው ከቀጠሉ ግን የተፋሰሱ አገራት በተናጠል ወንዛቸውን ማልማታቸው አይቀርም። ያኔ ግብፃዊያን የማይወጡበት ችግር ውስጥ መግባታቸው የግድ ይሆናል ማለት ነው። አሁንም ግን ምርጫው በእጃቸው ነው!

ከ11ዱ የሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ

የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ድርድር ለሰላማዊ ትግል ቀዳሚ መሳሪያ ነው!!

አማራጭ የህዝብ ድምጾች የሚሰሙበት መድረክ እንዲመቻች ለማድረግና ህዝብ ስልጣን ባለቤት እንዲሆን የሚያስችል የህግ ማእቀፍ መኖር የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት አሁን እየታዬ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት በማርገብ በቂምና በጥላቻ የተሞላው የአገሪቱ ፖለቲካ ተቀርፎ በምትኩ መቻቻልና መልካም ፉክክር ያለበት የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር ማስቻል ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ስለዚህ እኛ    11ዱ የሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ከወረቀት ባለፈ ለስልጡን የፖለቲካ ስርዓት ግንባታ ሒደት መሰረት ለመጣልና ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋትና ሰብአዊ መብት እንዲከበር ማድረግ ቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት ይታመናል።

የፖለቲካ ድርድር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ለማሳለጥ ጠቃሚ መሳሪያ በመሆኑ ድርድሩ በአግባቡ እንዲካሄድ የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ድጋፍ የሚጠይቅ ታላቅ ተግባር ነው። ከገዥው ፖርቲ ኢህአዴግ ጋር የጀመርነው ድርድር የሃገራችንን ውስብስብ የፖለቲካ ችግር ለመፍታት ያስችላል ብለን በማሰብ ለአለፉት 11 ወራት የድርድር መተዳደሪያ ደንብን ከማዘጋጀትና ማፅደቅ ጀመሮ 12 የድርድር አጀንዳዎች በጋራ በመለየት በቀዳሚዎቹ ሶስት የምርጫ ህጎች አጀንዳዎች ላይ ድርድር አድርገናል።

በመጀመሪያው አጀንዳ ማለትም በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ 573/2000 ላይ የነበረን የድርድር ሁኔታ አሁን በምንገኝበት ስብስብ ደረጃ ሳይሆን ፓርቲዎች በተናጠልና በተወሰነ ምልኩም ቢሆን በቡድን የተደራደርን ቢሆንም በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በርካታ የድርድር ሃሳቦች ቀርበዋል። ይሁን እንጂ በወቅቱ ተደራዳሪ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቁጥር 16 ስንሆን የነበረን የድርድር ሁኔታ በተናጠል በመሆኑና እርስ በርስ ተናበን ገዢውን ፓርቲ መገዳደር ባለመቻሉ ከድርድር ይልቅ ውይይት በሚመስል መልክ የተጠናቀቀ አጀንዳ ነበር። በዚህ ሁኔታም ቢሆን በአዋጁ ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ያሰፋሉ የተባሉና የመድብለ ፓርቲ ስርአቱን ያጠናክራሉ ያልናቸውን ድንጋጌዎች እንዲሻሻሉ ተደራድረናል።  በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቀረቡት የድርድር ሃሳቦች ውስጥ ሰፊ ክርክር ተደርጎባቸው ስምምነት ካልደረሰባቸው ማሻሻያዎች ውስጥ  ለፖለቲካ ፓርቲዎች የዳኝነት ችሎት አሰያየምና በዋናነት የአቃቤ ህግና የፕሬዝዳንቱን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት መታገድ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ።

ይሁን እንጂ በመጀመሪያው የድርድር አጀንዳ የነበረውን ሂደት በመገምገም ከተደራዳሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አስራ አንዳችን የድርድር ሃሳቦቻችንን በጋራ በማደራጀት ከሁለተኛው አጀንዳ ማለትም ከምርጫ ህጉ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ጀምሮ ጠንክረን እየተደራደርን እነገኛለን። እኛ የ11 ዱ ሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁንም በኢትዮጵያ ምርጫዎች በተሟላ ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆኑ ነጻና ሚዛናዊ ምርጫዎች እንዲካሄዱ ወሳኝ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ብለን እናምናለን። በአገራችን የዜሮ ድምር ፖለቲካን በማስወገድ በፖለቲካ ኃይሎች መግባባትና ትብብር ላይ የተመሰረተ የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሥርዓትን ለመፍጠር የበለጠ ወደ ሚያግዝ አማራጭ ከመቀየር አንስቶ የህግ ማእቀፉን በማሻሻል ለነጻና ሚዛናዊ ምርጫ እንቅፋት ሆነው የሚገኙ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ሁኔታዎች መሻሻል እንዳለባቸው አጠንክረን ተደራድረናል። በድርደሩም ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክረን እየሰራን ነው።

ሁለተኛው አጀንዳ የተሻሻለው የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ሲሆን በ2002 እና በ2007 ዓ.ም በተደረጉት የምርጫ ሂደቶች ከታዩት ጉድለቶች አንጻር በኢትዮጵያ በቀጣይነት የሚደረጉ ምርጫዎች የበለጠ ዴሞክራሲያዊና ነጻና ሚዛናዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የምርጫ ህግ፣ የምርጫ ስነ-ምግባር ኮዱንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምዝገባ አዋጅን ማጣጣም አስፈላጊ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በመረዳት በምርጫ ህጉ ላይ መደረግ አለባቸው ብለን ያመንባቸውን የማሻሻያ ሀሳቦች በማቅረብና በመደራደር ከአለም አቀፍ የምርጫ ህግ መስፈርት፤ የተባበሩት መንግስታትንና የአፍሪቃ ህብረትን የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የሰብአዊ መብት አከባበር ድንጋጌዎች ስምምነት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማድረግ ተደራድረናል።

በዚህም መሰረት የምርጫ አመራር አካል አደረጃጀት የአለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና ሞዴሎችን በማቀረብ ከኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም የድርድር ሀሳብ አቅርበናል። ሆኖም ግን ገዥው ፓርቲ የምርጫ አመራር አካል ባለበት ሁኔታ እንዲቆይ በመፈለጉ እኛ 11 ዱ ሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ባለመስማማት ድርድሩ የተሟላ ሳይሆን ቀርቶ የምርጫ አዋጅ 532/99 በከፊል ተቋርጧል። በድርድር መርህ መሰረት የተቋረጠው ድርድር እንደገና ማየት የሚቻለበት አግባብ በገዢው ፓርቲ በኩል እንደሚኖር የተገለፀ በመሆኑ ድርድሩ ከእኛ ጋር ስለሚቀጥልበት ሁኔታ እየተነጋገርን እንገኛለን።

ነገር ግን የምርጫ ስርዓቱን በተመለከተ አሁን የምንከተለውን የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ስርአት ወደ ተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት እንዲቀየር የመደራደሪያ ሐሳብ አቅርበን ነበር። የአሰራር ሂደቱንና ህጉን ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የመድበለ ፓርቲ ስርአት ግንባታውን የሚያጠናክርና የተሳትፎ ፖለቲካ እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የሌሎች አገሮችንም ተሞክሮ ግምት ውስጥ በማስገባት ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦችን ከአለም አቀፍ ተሞክሮዎች ጋር በማገናዝብ ለመደራደር ችለናል።የነበረውን የምርጫ ስርዓት በምርጫ አብዛኛው ሕዝብ የመረጠው ሳይሆን አብላጫ ድምጽ ያገኘው ብቻ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚወስድና በፖለቲካ ኃይሎች መካከል መቻቻልንና መግባባትን እያሳደጉ ከመጓዝ አንጻር አብላጫውን ድምጽ ላገኘው ፓርቲ የሚያጎናጽፈው የላቀ መብት የሌሎች ፓርቲዎችን ተሳታፊነት ስለሚያሳንስ በኛ በኩል ይህ የጠቅላይነት ባህሪ ያለው የምርጫ ስርዓት ቀርቶ ተመጣጣኝ ውክልና ስርዓት እንዲሆን ተደራድረናል።

በአገራችን የተጀመረው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሄድ አሁን ካለበት አንድ ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የበላይነትና ቁጥጥር ወደ ሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች ትብብር ወደ ተመሰረተበት ደረጃ ማሸጋገር የግድ ይላል። ሥርዓቱ በሁሉም ፖለቲካዊ ኃይሎች ተሳትፎና ትብብር ላይ የተመሰረተ ከማድረግ ባሻገር በምርጫ ሂደት የሕዝባችን ተሳትፎ ተጽዕኖ ያለው እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን፣ እኛ 11 ዱ የሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ አሁን በሥራ ላይ ያለው የአገራችን የምርጫ ሥርዓትን በመቀየር በአገር ግንባታ ሂደት በተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ሊኖር የሚገባውን ትብብር የሚያጎለብትና ለኢትዮጵያ ዴሞክርሲ ዕድገት አስተዋጽዖ የሚያደርግ የምርጫ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የአብላጫ ድምጽ ስርዓትን ወደ ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት (mixed parallel electoral system) ለመቀየር ከገዥው ፓርቲ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰናል።

ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርአት በኛ በ11 ዱ ተደራዳሪ ፓርቲዎች በኩል የባከኑ ድምጾች በመቶኛ ስሌት ለተመጣጣኝ ውክልና እና ለአብላጫ ድምጽ ይሁን የሚለው ቀመር ላይ ለበርካታ የድርድር መድረኮች ከተደራደርን በኋላ  ለተመጣጣኝ ውክልና 20% ለአብላጫ ድምጽ 80% የውክልና ድምጽ አሰራር እንዲኖር በመስማማት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ አሁን ካለው ተጨማሪ 110 ወንበሮችን በማካተት ወደ 660 መቀመጫዎች እንዲያድግ ስምምነት ላይ ተደርሱዋል። በእኛ እምነት ይህ የባከኑ ድምጾች ወደ ፓርላማ ወንበር እንዲቀየሩ ማደረግ የፖለቲካ ተሳትፎን በመጠኑም ቢሆን እንደሚያሻሽል እናምናለን።

በሦስተኛ ደረጃ የተደራደርንበት አጀንዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 662/2002  ሲሆን እኛ 11ዱ የሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በአዋጁ ውስጥ የተካተቱ የህግ ድንጋጌዎችን ከህገመንግስቱና ከአለምአቀፍ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር በማነጻጸር የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተሳትፎን ይገድባሉ ብለን ያልናቸውን አንቀጾች እና መጨመር አለባቸው ያልናቸውን ሐሳቦች ከነማሻሻያቸው ለይተን በማቀረብ ተደራድረናል። በአዋጁ ውስጥ ከተካተቱት አንቀጾች ውስጥ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ የሚገድቡና ጥንካሬያቸውንም የሚፈታተኑ ናቸው ያልናቸውን 10 አንቀጾች እንዲሻሻሉ፣ 4 አንቀጾች እንዲሰረዙ፣ 2 አንቀጾች እንዲጨመሩ በማቀረብ ሁሉንም በሚባል ደረጃ ገዥው ፓርቲ ተስማምቷል። ነገር ግን የጋራ ምክር ቤት ተቋማዊ ይዘትና ክትትል ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ የሚደራጁትን የጋራ ምክር ቤቶች የምርጫ ኮሚሽን እንዲያቋቁማቸውና እንዲከታተላቸው ሐሳብ አቅርበን ገዥው ፓርቲ አልተስማማም። ነገር ግን የጋራ ምክር ቤቶች በተዋረድ ባሉት ምክር ቤቶች  ስር እንዲሆኑ በቀረበው የመደራደሪያ ሐሳብ በመጽናቱ ከስምምነት ላይ አልተደረሰም።

 

እኛ 11ዱ የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች፡-

1.       እየተደመረ የሚቀጥል ዘላቂ ለውጥን በተቻለ ፍጥነት ማረጋገጥ ከሚያስችሉ አማራጮች መካከል አንደኛው ለአገራችን ዲሞክራሲ መጎልበት ገንቢ የሆኑ ሀሳቦችን በመተማመን ደረጃ በደረጃ ተቋማዊ እየሆኑ እንዲያድጉ የሚያስችሉ ስምምነቶችን መፍጠር ነው ብለን ስለምናምን ገንቢ ሀሳቦችንና ስምምነቶችን መፍጠርያ የሆኑ ውይይቶቸንና ድርድሮችን ማድረግ እንደ ወሳኝ የትግል ስልት አድርገን ድርድሩን ወደፊት ማስቀጠል፣

2.       የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን ያለው የአገራችን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አንጻር አስፈላጊ በሆኑ የሀገር ጉዳዮችና በአገር ግንባታ ሂደት በተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ሊኖር የሚገባውን ትብብር ለማምጣት፣ ገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት እየተቆጣጠረው እንዳይሄድ የሚያስችል ፖለቲካዊ ተፅእኖ በመፍጠር፣ ለብሔራዊ መግባባት፣ ፖለቲካዊ መቻቻልና አንድነት እንቅፋት የሆኑ ህጎችና ፖሊሲዎችን በማሻሻል ህዝቡ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማጎልበት በቁርጠኝነት እየታገልን የህዝቡን ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ለለውጥ እንሰራለን።

3.       በአገራችን የተጀመረው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሄድ አሁን ካለበት የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ቁጥጥር ተላቆ በሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር የሚመሰረትበት ምእራፍ ማሸጋገር የግድ ስለሚጠይቅ፣ መቻቻልና መግባባት እየሰፈነና እየሰረጸ ቀስ በቀስ አገራችን ከዜሮ ድምር ፖለቲካ እንድትላቀቅ  ማስቻል ነው። የፖለቲካ ሥርዓቱን በሁሉም ፖለቲካዊ ኃይሎች ተሳትፎና ትብብር ላይ የተመሰረተ ከማድረግ ባሻገር ዜጎች በምርጫ የሚፈልጉትን ወደስልጣን ለማምጣት የማይፈልጉትን ለማውረድ የሚችሉበትን ስርአት በማምጣት የዜጎችን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተሳትፎ ጠንካራ እንዲሆን ለማድረግ በትጋትና በቁርጠኝነት እንሰራለን።

4.       በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የመገናኛ ብዙሃንና ፀሃፊዎች የማተካ ሚና አላቸው። በመሆኑም የድረድሩን ሂደት በቅርብ በመከታተል ለህዝቡ መረጃ ተደራሽ በማድረግ የህዝቡን ተሳትፎ ከፍ እንዲልና በፖለቲካው ወሳኝ ሚናውን እንዲጫወት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

5.       ድርድር የሃሳብ ትግልን ማእከል ያደረገ የህዝብን ፍላጎት በመወከል የሚደረግ የፖለቲከኞች ሰላማዊ መድረክ ነው። አሁን ከገዢው ፓርቲ ጋር እያደረግን ያለው ድርድር በህዝብ ጥያቄና ተፅእኖ እንጂ በፓርቲዎች የልየነት አጀንዳ ተፅእኖ የተፈጠረ ክስተት አይደለም።በመሆኑም በተለይ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚታየው ተገቢ ያልሆነ የጥላቻና የፍረጃ ፓሮፓጋንዳ የአንድ ፓርቲ አገዛዝን ከማራዘም በስተቀር የፈየደው ነገር ስለሌለ በመካከላችን ተከባብረን የውድድር ሜዳውን በማስተካከል ሁላችንም በህዝብ ድምፅ ለመዳኘት ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል።

6.       በመጨረሻም ከዚህ ድርድር የሀገሪቱ ህዝቦች በፖለቲካው ምህዳር መጥበብ ምክንያት ያጡትን የተሳትፎ መብት ለማግኘት ያስችላል ብለን ስለምናምን፣ የፖሊተካ ፓርቲዎችን፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮችንና በአጠቃላይ የዜጎችን የተለያዩ አስተሳሰቦች ወደመድረክ ሊያመጣ ይችላል ብለን ስለምናስብ የድርድሩን ሂደት የባለድረሻ አካላት ድጋፍ እንዳይለየን በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናስተላለፋለን።

የ 11ዱ የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ

1.       የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ደርጅት (መኢአድ)

2.       የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(መኢዴፓ)

3.       ቅንጅት ለአንድነትና ለፍትህ (ቅንጅት)

4.       የኢትዮጵያውያን ዴሞክረሳያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)

5.       አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ (አንድነት)

6.       የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ(አብአፓ)

7.       የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ህብረት(ኢድህ)

8.       የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ(ኢዴአን)

9.       አዲስ ትውልድ ፓርቲ(አትፓ)

10.     የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አሰዴፓ)

11.የወለኔ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርተ(ወህዴፓ)

ህዳር 2010

አዲስ አበባ¾

“እውነተኛ፤ የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት ያሳየው

ደርግ ነው”

ዶ/ር ፍሰሃ አስፋው

በይርጋ አበበ

አርብ 29/03/2010 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። በየዓመቱ የሚከበረው ይህ ቀን (በዓል) መሠረቱ በ1987 ዓ.ም የወጣው የአገሪቱ ህገ-መንግሥት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትን ያመጣ በመሆኑ እንደሆነም አገሪቱን የሚገዛት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደጋግመው ይናገሩ።

መንግሥት “የማንነት ጥያቄ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተፈቷል፤ ህገ መንግሥቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችን ተቻችለው እንዲኖሩ ያስቻለ የቃል ኪዳን ሰነድ ነው” ሲል ይገልጻል። ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የማንነት ጥያቄዎች እና ዘርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች ሲፈጠሩ እያየን ነው።

ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ ሕገ-መንግሥቱ እና የፌዴራል ሥርዓቱ የሚጫወቱት ሚና ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ቅድሚያ የሚሰጠው ነጥብ ነው። ህገ-መንግስቱ በሚረቀቅበት ወቅት ኢህአዴግን ወክለው የአርቃቂ ኮሚሽኑ አባል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና በደርግ መንግሥት የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲትዩት አባል ሆነው የወቅቱን ህገ መንግሥት ካረቀቁት መካከል አንዱ የነበሩት ዶ/ር ፍሰሃ አስፋው ላነሳነው ጥያቄ መልስ የሰጡ ምሁራን ናቸው። (ዶ/ር ነጋሶ ጉዳዳ ቀደም ብሎ ለሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ politics of Federalism እና ለናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ኢንስቲትዩት Constitution for a multinational Democratic state nation the case of Ethiopia በሚሉ ርዕሶች ያወጧቸውን ሰነዶች እንደሳቸው መረዳት እንድንጠቀም በፈቀዱልን መሠረት ነው ለዚህ ጽሁፍ የተጠቀምንበት)።

 

የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር በሕገ -መንግሥቱ

በ1987 ዓ.ም የፀደቀው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ አንድ “የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚል ስም ይጠራል” ሲል ይደነግጋል። የፌዴራሉ መንግሥት አባል ክልሎችን ሲጠቅስም ስምንት የብሔር ክልሎች፤ ትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሀረር፣ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ መሆኑን በአንቀጽ 47 ደንግጓል።

ዶ/ር ፍሰሃ ፌዴራሊዝም አወቃቀሩን ላይ ያላቸውን ልዩነት ሲገልፁ “ቋንቋን መሠረት ያደረገ መሆኑ በህዝቦች መካከል መለያየትንና መጠራጠርን ያሰፍናል” ሲሉ ይሞግታሉ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው ለሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ በቀረቡት የጥናት ፅሁፍ ላይ የፌዴራሊዝሙን ጠቀሜታ ገልጸዋል። ዶ/ር ነጋሶ ሀሳባቸውን ሲያጠናክሩም ከ1983 ዓ.ም በፊት በነበረው የአገዛዝ ሥርዓት ማህበራዊ ፍትህ እጦት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ እና የፖለቲካ ቁጣ (ጥያቄ) ተነስተው ነበር። እነዚህ ጥያቄዎችና ኢፍትሃዊነቶች ደግሞ በሀይማኖት፣ በባህል እና በቋንቋ ላይ ያተኮሩ ነበር። በዚህ የተነሳም በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች አመፆችና ተቃውሞዎች ተነሱ። በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች የኤርትራ የነፃነት ግንባር (ሻዕቢያ)፣ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ህወሓት)፣ የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራቲክ ንቅናቄ (ኦህዴን) ጨምሮ ሌሎች የታጠቁ ሀይሎች እንደነበሩ በፅሁፋቸው አስፍረዋል። ዶ/ር ነጋሶ አያይዘውም፤ ኢህአዴግ ሥልጣን በተረከበበት ወቅት የነበረውን አካባቢያዊ ፖለቲካ ጠቅሰው ባቀረቡት ጽሁፍ “በሱዳን የነበረው የምሥራቅ አፍሪካ ጦርነት እና የሶማሊያ አለመረጋጋት በህንድ ውቅያኖስ ሰሜን ምስራቃዊ ቀጠና እና በቀይ ባህር ዙሪያ አደጋ ያንዣበበ ነበር” ብለዋል። ኢህአዴግ ምንም እንኳን ወታደራዊውን መንግሥት በጠበመንጃ አፈሙዝ አሸንፎ የአራት ኪሎውን ቤተመንግሥት ቢቆጣጠርም፣ ይህ ግን ብቻውን ለሰላም ማረጋገጫ ዋስትና እንዳልነበረ ዶ/ር ነጋሶ ተናግረዋል። ለዚህም ሲባል የሰላም ጉባኤ (ኮንፈረንስ) መዘጋጀቱን ያወሱት የቀድሞ የኢፊዲሪ ፕሬዝዳንት፤ ሆኖም ግን ኢህአፓ፣ መኢሶን እና ኢሰፓ በጉባኤው እንዳይሳተፉ መደረጋቸውንም አውስተዋል።

 

ሕገ-መንግሥት እና ሂደቱ

የኢህአዴግ መንግሥት በ1987 ዓ፣ም ህዳር 29 ቀን ያጸደቀውን ህገ-መንግሥት “ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተስማምተውና ተቻችለው እንዲኖሩ ያስቻለ የቃል ኪዳን ሰነድ” ሲል ይገልጸዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ይህን ነፃነታቸውንና እኩልነታቸውን ያረጋገጠላቸውን ሕገ- መንግሥት የወጣበትን ቀን ለማሰብ በየዓመቱ እየተገናኙ የብሔር፣ ብሔረሰቦች ቀን ያከብራሉ። በአሉም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት ይከበራል።

ዶ/ር ፍሰሃ አስፋው ግን ከላይ የሰፈረውን የብሄር ብሄረሰቦችን በዓል ምክንያት አይቀበሉትም። የስነ-ሰብ ምሁሩ ለምን እንደ ማይቀበሉት ሃሳባቸውን ሲያስቀምጡ “ህገ- መንግሥቱ ህዝብ ሳይወያይበት የፀደቀ ነው” ይላሉ።

ዶ/ር ፍሰሃ አክለውም “ለምሳሌ እኛ ያረቀቅነውና ያፀደቅነው ህገ-መንግሥት (በደርግ ጊዜ የወጣውን የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት) ረቂቁ ከታወጀ በኋላ በ16 ቋንቋ ተተርጉሞ ህዝብ ውይይት እንዲያደርግበት አቅርበን ህዝቡ ተወያይቶ ተስማምቶ ነው ያጸደቀው። ኢህአዴግ ያወጣው ህገ-መንግሥት ግን ህዝብ ያልተወያየበት ስለሆነ ነው ህዝቡ ሊቀበለው ያልቻለው” ብለዋል።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው በኢህአዴግ የሥልጣን ዘመን የወጣው የኢትዮጵያ ህገ- መንግሥት “ህዝቡ አልተወያየበትም” የሚለው ገለፃ ትክክል መሆኑን ይስማማሉ። “እኔ እስከማውቀው ድረስ አርቃቂ ኮሚሽኑ ረቂቁን ለህገ-መንግሥት ጉባኤ ከላከ በኋላ ለህዝብ ውይይት አልቀረበም” ሲሉ ተናግረዋል። ረቂቁ ከመውጣቱ በፊት ግን 73 ጥያቄዎችን ለ23ሺህ ቀበሌዎች ነዋሪ ህዝብ ቀርቦ ህዝብ እንደተወያየበትና የህዝብ አስተያየትን ባማከለ መልኩ የህገ-መንግሥት ምሁራን (experts) ሃሳባቸውን አክለውበት እንደወጣ ዶ/ር ነጋሶ ይናገራሉ።

በአንፃሩ የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት ደግሞ መግቢው ላይ ባሰፈረው ሀሳብ ላይ “የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች” በራሳቸው ፈቃድ እና በነፃነት ባካሄዱት ውይይት የፀደቀ ህገ-መንግሥት መሆኑን ይገልፃል።

 

የብሔሮች ብሔረሰቦች መብት በሕገ-መንግሥቱ እና በተግባር

የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት በአንቀጽ ስምንት ቁጥር አንድ ላይ “የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው” ይላል። “ይህ ህገ-መንግሥም የሉአላዊነታቸው መገለጫ ነው” በማለት ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሰጣል።

ዶ/ር ፍሰሃ አስፋው ደግሞ በብሔር ብሔረሰቦች መብት መከበርና እኩልነት መጎናጸፍ ላይ ቅሬታ ባይኖራቸውም የሚያነሱት ጥያቄ ግን አለ። ዶክተሩ ሲናገሩ “ታሪክን በታሪክነቱ ማስቀመጥ ጥሩ ነው። ብሔረሰቦች በዘውዱ ጊዜ በቋንቋህ አትጠቀም፤ ባህልህን አታሳድግ የሚል አልነበረም። በደርግ ጊዜ ግን ከዚህ የተለየ ነው። የብሔረሰቦችን እኩልነት በይፋ ያወጣው የደርግ መንግሥት ነው። የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲትዩት አቋቁሞ፤ ጥናት አስጠንቶና በ16 ቋንቋ አስተርጉሞ ህገ መንግሥት ያስፀደቀና እውነተኛ የሆነ የብሄረሰብ እኩልነት ያሳየው ደርግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፍሰሃ አክለውም የኢህአዴግ መንግሥት በብሄሮች እኩልነት ላይ ያለውን አቋም የሚገልፁት “ለፖለቲካ ትርፍ እንጂ ከልብ የመነጨ አይደለም። የብሄረሰብ እኩልነት ማለት በቀጠሮ እየተገናኙ ጭፈራ መጨፈር አይደለም። ትክክለኛ የብሔረሰብ እኩልነት የሚባለው የኢኮኖሚ እኩልነት፣ የፖለቲካ እና የልማት እኩል ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት እንዲሁም የአስተዳደር እኩልነት ሲፈጠር ብቻ ነው” ይላሉ። በእሳቸው እምነትም እውነተኛ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት “አልተከበረም!”። በአሁኑ ወቅት አገሪቱ የምትከተለው ፌዴራሊዝም ለክልሎች የሚሰጠው ሥልጣን ውስን ነው። ከላይ የወረደን መመሪያ እንጂ ክልሎች በራሳቸው ፈቃድና እቅድ የሚሰሩት የለም” ሲሉ የፌዴራል መንግሥት የፖለቲካ ጡንቻ ከክልሎች የገዘፈ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢፌዴሪን ህገ-መንግሥት ካረቀቁት 29 ሰዎች አንዱ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምንም እንኳን ከህገ-መንግሥቱ አንቀጾች መካከል በተወሰኑት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ቢገልጹም “የብሔር ብሔረሰቦችን መብት” እውቅና መስጠት መቻሉን ይናገራሉ። እንደ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምልከታ የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት ለብሔር ብሔሰቦች የሰጠው መብት ተገቢ ቢሆንም “እስከመገንጠል” በሚለው ክፍል ላይ ግን ልዩነት አላቸው። ብሄራዊ ቋንቋን፣ የመሬት ባለቤትነትን፣ ሰንደቅ ዓላማ እና አንቀፅ 39 ላይ ያለው እስከመገንጠል የሚሉ የህገ-መንግሥቱ አንቀፆች ያኔም ሆነ አሁን አጨቃጫቂ እንደሆኑ ተናግረዋል። በብሔር ብሄረሰቦች እኩልነት ላይ ሳይሆን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር ላይ ልዩነት እንዳላቸው የገለፁት ዶ/ር ነጋሶ “በዓሉ ላይ ልዩነት አለኝ። ምክንያቱም ህዳር 29 ህገ-መንግሥት የፀደቀበት እንጂ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አይደለም” ሲሉ ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል።

በአገሪቱ በርከት ያሉ አካባቢዎች ዘርንና ብሄርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች እየታዩ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ 12ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ከነገ በስቲያ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ይከበራል። በህገ-መንግሥቱ እና በፌዴራል ስርዓቱ አወቃቀሩ ላይ ልዩነት ያላቸው ወገኖች ለወቅታዊ የአገሪቱ ችግር ምንጭ አድርገው የሚያቀርቡት ህገ-መንግሥቱን እና የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀሩን ሲሆን፤ ከዚህ ጎን የተሰለፉ ወገኖች ደግሞ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የዶላር ኮንትሮባንድ እና የጫት ንግድን በላይነት ለመውሰድ የሚደረግ ጤናማ ያልሆነ የኪራይ ሰብሳቢ ባለሥልጣናት ሥራ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።

  

እኛና ግብጽ

Wednesday, 06 December 2017 13:16


ዳደ ደስታ

 

1) ግብጽ ምናችን ናት?


በአገር ደረጃ እምንፈራው ጠላት ምን ዓይነት ነው? መጀመርያ ‘ማነው?’ ወደሚለው እንሂድ። “ጠላት” እሚባለው ነገር “ሁኔታ” ሊሆን አይችልም፣ በምክንያትና ውጤት የሚገለጽ “ኃይል” እንጂ። ትልቁ ጉዳይህን ወይም ዓላማህን ከማደናቀፍ እስከ ማኮላሸት፣ ህልውናህንም ከመፈታተን እስከማክተም የሚሄድ ውጥኑን ለማሳካት አቅዶ እሚንቀሳቀስ ኃይል ነው። ድህነት “ሁኔታ” ነው። ስትራተጂ ነድፎ፣ ለያንዳንዱ እንቅስቃሴ መልስ እየሰጠ፣ ለማሸነፍና ላለማሸነፍ የሞት ሽረቱን እሚፍጨረጨር ኃይል አይደለም። ስለዚህ ድህነት የሁኔታዎች ውጤት እንጂ ጠላት አይደለም።


ታዲያ ለምን ‘ቀንደኛ ጠላታችን ድህነት ነው’ እንላለን? ለጠላት ተጋላጭ ስለሚያደርገን ነው፣ ሲባል ሰምቻለሁ። ይህ ግን አሳማኝ አይሆንም። እንዲያውም የተሳከረ ቅደም ተከተል ነው፣ ምክንያቱም ከድህነቱ በፊትም ቢሆን ጠላት እሚባል ነገር ነበረና ነው። ጠላት ለመባል እሚበቃው እንደ ድህነት ያለ ዓይነት ግኡዝ ነገር ሳይሆን ተጋፊ አጀንዳ ይዞ እሚንቀሳቀስ ህያው አካል (active organism) መሆን አለበት።


በሌላ በኩል ጠላትነት መጀመርያና መጨረሻ ያለው የእንቅስቃሴዎች ፍሰት ነው። ይህ ማለት ታድያ፣ ልክ እንደ ወዳጅነት፣ ጠላትነትም ነጠላ ክስተት አለያም ዘላለማዊ እርግምት አይደለም። የአንድ ወቅት ጠላትነት ወደ ወዳጅነት ሊቀየር ይችላል። ይህ ሽግግር እውን ይሆን ዘንድ እንደ ዓላማ መያዝም አለበት። ወዳጅነት ወደ ጠላትነት ቢንሸራተት ግን አንድም ክፉ ዕድል፣ አለያም ከዚህ ሁኔታ ሊጠቀም አቅዶ የሰራ ኃይል ስላለ ብቻ ነው። ለአቶ ድህነት፣ ወዳጅነትም ጠላትነትም ጉዳዩ አይደለም።


ወደ ምድረ ግብጽ ቁልቁል ከሚፈሰው የናይል ወራጅ ውሃ 85%ቱ ከኢትዮጵያ ነው ይባላል። ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ሽቅብ ከሚፈሱት ክፋቶች 85%ቱ ከግብጽ ሳይሆኑ አይቀሩም። ብዙዎቹ ውጭ-ወለድ የኢትዮጵያ ችግሮች ምንጫቸው ቢጠና ግብጽ ከመሆን አይዘልም። ለምሳሌ የአፍሪካ ቀንድ ለብዙ ዘመናት እርጋታና ሰላም የራቀው ቀጠና ሆኖ መዝለቁ። የኢትዮጵያ በዓላትና የማይሰራባቸው ቀናት መብዛታቸው ራሱ የግብጽ ተንኮል ነው በማለት አስረጅ ጠቅሰው እሚከራከሩ ምሁራን አሉ። በግብጾችም ቢሆን አይፈረድም። እርግጥ ዘላቂ አገራዊ ጥቅም ዋስትና እሚያገኘው ከወዳጅነትና ከፍትህ ነው። ‹ልክ ናቸው አይደሉም›ን ትተን ግን ኢትዮጵያን አቆርቁዞና ቀስፎ መያዝ ዋነኛ የህልውናቸው ዋስትና አድርገው ስለቆጠሩት በዚያ አቅጣጫ በሙሉ አቅማቸው ቢረባረቡ እሚገርም አይሆንም። የግብጽ ጥፍሮችን ከአንገታችን ማላቀቅ ደግሞ ለኛ የህልውናና የሞት ሽረት ጉዳይ ይሆናል።

 

2) የሆነው ይህ ነው፤ ሁሌም የግብጽ አሸናፊነት - ሁሌም የኢትዮጵያ ተሸናፊነት


ከግብጾች ጋር የቆየ ታሪክ አለን። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለት የሚታወቁ ጦርነቶች ገጥመናል። ሁለቱንም ጊዜ ድል አድርገናል። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከህልፈታቸው አንድ ዓመት ገደማ ቀደም ብለው ለአንድ የውጭ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ “ግብጾች ድርድርን ትተው ጦርነት የመረጡ እንደሆነ ውጤቱ የነሱ ሽንፈት ሆኖ ያበቃል” የሚል አስተያየት ሰንዝረው ነበር። አክለውም፣ “ግብጾች የጦርነቱን አማራጭ ከዚህ በፊት ደጋግመው ሞክረውታል። በህይወት ተርፎ የጦርነት ዉሎው ለመተረክ የበቃ ወሬ ነጋሪ ግን አልነበረም” ሲሉ ተናገሩ። ይህ ምናልባት ወታደርና ትጥቅ በማሰለፍ የተደረጉትን ፍልሚያዎች ብቻ ስንቆጥርና ስናስታውስ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በሁለቱ አገሮች መካከል በአባይ ጉዳይ ላይ በይፋ ያልተነገረና መታኮስን ያልጨመረ ስውር ጦርነት ሁለቴ ብቻ ሳይሆን ሁሌ እንደተካሄደ ነው። አባርቶም አያውቅም።


በዚያ ስውርና ያላቋረጠ ጦርነት ግን ሙሉ ለሙሉ አሸናፊዋ ግብጽ ናት። አሸናፊነቷም በግልጽ እሚታይ ነው። እሰከ ቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ ከአባይ/ናይል ውሃ አንዲት ጭልፋ ስንኳ እንዳትነካ አድርጋት ቆይታለች። ግብጽ ይህን ማድረግ የቻለችበት ዘዴና አካሄድ ኢትዮጵያ ዉስጥ ችግሮች እንዲበዙና የኢትዮጵያ መንግስታትና ህዝቦች በውስጥ ችግሮች ተተብትበው ፋታ እንዲያጡ የሚያደርጓቸው ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በማድረግ፣ ከጎረቤቶቿ ጋር ፍጥጫና ዉጥረት ዉስጥ እንድትገባ በማድረግ፣ ኢትዮጵያን የማይመለከቱ ፍርደገምድል ዉሎችና መብቶች እንደመሟገቻ ባንዲራዎች ከፍ አድርጋ በማውለብለብ፣ ዓለም አቀፍ ኃይሎችና የፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ እንዲለግሙ በማግባባት፣ የድርድር መዓዶች የግብጽ ጥቅሞች ማስጠበቂያ ይሆኑ ዘንድ ሙዝዝ ያሉ አሰልቺ ንትርኮች በማካሄድ፣ አስቀያሚ የኢንፎግራንዳ (ኢንፎርሜሽን+ፕሮፖጋንዳ) ዘመቻዎች በመክፈትና አስፈላጊ በመሰላት ጊዜ ደግሞ ኃይልን ጨምሮ “ማንኛውንም ዘዴ እጠቀማለሁ” እያለች በማስፈራራት ነው። መቼም አይሳካላትም እያልን ራሳችንን አናሞኝም።

 

3) የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ዳርቻዎችና ማዕከሎች


ይህ ጽሁፍ “ምስለ ኢትዮጵያን ከናይል ተፋሰስ አንጻር ስለመገንባት” ያወሳል። ይህም “የኢትዮጵያን ምስል እንደ አንዲት የተፋሰሱ ቀጠና ኃያል አገር” እንዲታይ ወይም እንዲቀረጽ ማድረግ ያስፈልጋል ከሚል ነጥብ ይነሳል። “ኃያል” እሚለው ቃል ከጡንቻ ጥንካሬ ይልቅ የበጎ አሳቢነት፣ የትብብር ፈላጊነት፣ የመርህ አጥባቂነትና የፍትህ ጠበቃነት ጥንካሬን ያመለክታል። የራስ አገራዊ ጥቅም ማስከበርም ሁሌ የጡንቻ ኃይል ጉዳይ አይደለም የፍትህ እንጂ። የኢትዮጵያን ምስል በዚህ መልክ እንዲቀረጽ የማድረጉ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም። አሁን ጥያቄው የዚህ ዓይነት ምልከታና ቅኝት የሚጠይቀው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ የትኩረት ስበት ቀዳሚ ማእከሎች እሚመሰረቱት “በየትኞቹ ጉዳዮችና አካባቢዎች ላይ መሆን አለበት” እሚለው ይሆናል። ይህም ቢሆን እንዲሁ በአግባቡ ለመንደርደር ይረዳ ያህል አነሳነው እንጂ ለአሻሚ ሙግት እሚዳርግ ነጥብ ሆኖ አይደለም።


ከኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዋነኞቹና ቀዳሚዎቹ፡ 1) የናይል ወንዝ፣ የናይል ተፋሰስና ተያያዥ ጉዳዮች፥ 2) የአፍሪካ ቀንድና የቀይባህር አካባቢ፣ 3) አፍሪካና የአፍሪካ ህብረት፣ 4) ልዕለ ኃያላን፣ ዓለም አቀፍ ኃይሎችና ተቋሞቻቸው ወዘተ እያለ በተዋረድ እሚፈረጁ ናቸው። ከተጨባጭ አገራዊ ጥቅምና ወደፊት ከሚኖረው የውጭ ግንኙነት ፋይዳ ብቻ ሳይሆን ከታሪክም አንጻር ሲታይ ይህ አፈራረጅ ዝንፈት የለውም።


ለናይል ተፋሰስ ከዉጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያችን አንጻር እምንሰጠው ትርጉም በኢትዮጵያ ዕይታ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚወሰን አይደለም። የናይል ዉሃ የህልውናቸው መሰረት አድረገው እሚነሱት አገሮችና ህዝቦች እሚያደርጉትና እሚያስቡትንም ታሳቢ ያደርጋል። ለምሳሌ የግብጽ እንቅስቃሴ “ናይል ህልውናችን ነው” ከሚል አጠቃላይ መአዝን ይቃኛል። ዲፕሎማሲ የአገሮችና መንግስታት እንዲሁም ከመልቲላተራል ድርጅቶች ጋር የሚኖረውን ግንኙነታዊ ክዋኔ ወይም መስተጋብር መሳርያ ነው ካልን፣ ይህ የግብጽ አስተሳሰብ እንዳለና በቀጥታ ጉዳዩ የኢትዮጵያም የህልውና ጉዳይ እንዲሆን ግድ ይላል። በናይል ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ እምትሰጠው ትኩረት ከራስዋ እሚመነጭ ብቻ ሳይሆን ግብጽ የምትሰጠው ትኩረት ነጸብራቅ ጭምርም ሊሆን የግድ ነው።


የናይል ተፋሰስ አገሮች እሚባሉት አሁን በቁጥር አስራ አንድ ናቸው። ስለዚህ ሜዳው 11 ተጨዋቾች አሉት። የተመልካቾቹ ቁጥርና የመመልከቻው ሜዳ ግን ከተጨዋቾቹና ከመጫዎቻው ሜዳ ይልቃል። ተመልካቾቹም፣ ማለትም ኳስ ከሚነጥርበት ሜዳ ዉጭ ያለው ምህዳርም ግን ችላ እሚባል አይደለም። ያም ሆኖ ጨዋታው ላይ እሚከሰተው ሁነኛ ቁምነገር ወይም ተጽዕኖ ከሜዳው የሚመነጭ ነው። የሜዳውንም ጨዋታ ቢሆን ሁሉም ተጨዋቾች በእኩል መዋጮ እሚያመርቱት አይደለም። የጎላና ወሳኝ ሚና ከጥቂቶች ነው። እያጠበብን ስንሄድ የአንበሳ ድርሻ ይዞ ጨዋታውን በበላይነት እሚቆጣጠረውን አውራ ኃይል ለይተን እናገኘዋለን። ስለዚህም ነው ለአገራችን፣ አጠቃላይ ሁኔታዎችን በምልአት፣ ልዩ ሁኔታዎችን በትኩረት እና ወሳኝ ማእከሎች ደግሞ በሙሉ ቁጥጥር መከታተል ዋነኛው የድልና የውጤት መንገድ እሚሆነው።


የናይል ተፈሰስ ህዝቦችን በተመለከተ፣ ለሁሉም እሚጠቅም፣ ነገውን የተሻለ እሚያደርግ ቁምነገር እሚሰራው ሜዳውን በምልአተ ስፋት፣ ተጨዋቾችንም በምልአተ ቁጥር ያካተተ፣ ሁሉንም ፍላጎቶችና ስጋቶች የሚመልስ ቀመርና መግባባት የመንደፍ አስፈላጊነት አያጠያይቅም። ከህግና ከሞራላዊ መነሻ አንጻር የተፋሰሱ መሬት እያንዳንዷን አባል አገር መሬት በእኩል እሚያስብ፣ አገሮቹ ራሳቸውንም በእኩልነት እሚያይ አመለካከት መያዝ ተገቢ ነው። ከተግባራዊ አሰራርና ተጨባጭ ሚና አንጻር ሲታይ ግን ሁሉም ተጨዋችና ሁሉም የሜዳው መሬት ተመሳሳይ ፋይዳ አለው ማለት አይደለም።


የተፋሰሱ ዋና ማእከል ውሃው እሚፈስበት መስመር ወይም ባንክ ነው። አውራውን ፋይዳ የተሸከሙት አገሮች ለመለየትና እነሱ ላይ ትኩረት ለማድረግም ብዙ ውሃ እሚመነጭበትና ብዙ ውሃ እሚያልፍበት በሚል ማጥበብ ይቻላል። በዚህ ቀመር ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ዋነኞቹ ባለድርሻና የስበቱ ማእከሎች ሆነው እናገኛቸዋለን። ዋናውን የጥቅም ግጭትና ፍጥጫ እሚኖረው የራስጌ መነሻ በሆነችው ኢትዮጵያና የግርጌው መጨረሻ (መዳረሻ) በሆነችው ግብጽ መካከል መሆኑ ስለሚታወቅ የጡዘቱ ዋልታዎች ኢትዮጵያና ግብጽ ናቸው። ሆኖም፣ ሱዳን መሃል ሆና የጉተታውን ሚዛን ወዲህ ወይም ወዲያ እንዲያጋድል የማድረግ ተፈጥሯዊ ስፍራ በመያዟ እንደ አንዲት ወሳኝ ተጨዋች የዚህ ትንታኔ ትኩረት አካል ትሆናለች።

አባይን የመጠቀም መብታችን

Wednesday, 06 December 2017 13:10

 

በስንታየሁ ግርማ


ምንም እንኳን አብዛኛው ግብፃውያን አባይን በተመለከተ የቀድሞ አቋማቸው እየተቀየረ ቢሆንም እንዳንዶች በድሮው የተንሸዋረረ ሀሳብ ውስጥ ይገኛሉ። ለመጥቀስ ያህል የህዳሴው ግድብ ሙሉ ስምምነት እስከሚደርስ ድረስ ግንባታው ለምን እንዳልተቋረጠ ከኢትዮጵያ መንግስት ማብራሪያ ጠይቀናል የሚለው ይገኝበታል። ከዚህ በመነሳት ከአለም አቀፍ ህግ አኳያ ወንዙን የመጠቀም መብታችን ምን ይመስላል የሚለውን ማየት ተገቢ ነው። አንዳአንድ ግብፃውያን የቀኝ ጊዜ ውሎችን በመጥቀስ ናይልን በመጠቀም አለም አቀፍ መብት ከፍተኛ ነን ይላሉ የናይል ወንዝ በተመለከተ የመጀመሪያው ስምምነት


የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1891 ነበር። በዚህ ስምምነት መሠረት ጣሊያን በአታቦራ/ተከዜ ወንዝ ላይ ግድብ ላለመስራት ከእንግሊዝ እንደተስማማች የሚያትቱ አሉ። ፕሮፌሠር አሊ አብደላ አሊ ግን ሥምምነቱ በግልፅ ቋንቋ ያልተቀመጠ ነው ይላሉ።


ሁለተኛው ስምምነት እ.ኤ.አ በ1902 በእንግሊዝ፣ በጣሊያን እና በአፄ ሚኒሊክ መካከል ተፈረመ የሚለው ነው። በዚህ ስምምነት መሠረት አፄ ሚኒሊክ የአባይን ወንዝ ላለማስቆም እንዳይፈስ ለማድረግ (Arrest) እንደተስማሙ የሚያስቀምጡ አሉ። በሌላ በኩል ስምምነት በወቅቱ በእንግሊዝ መንግስት የዘውድ ም/ቤት ስላልፀደቀ ተቀባይነት የለውም የሚሉ አሉ። የእንግሊዘኛው እና የአማርኛው ፍቺዎች የተለያዩ በመሆናቸው ኢትዮጵያ እንዳላፀደቀችው ፕሮፌሠር አሊ ይናገራሉ። የ1929 እና የ1959 ስምምነት ለታሪካዊ መብት ማነኛዎቹ መነሻዎች ናቸው ይላሉ። በእነዚህ ስምምነቶች መሠረት፡-


· ግብፅ ሱዳን አንድ ጠብታ ውሃ ሳያስቀሩ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ተከፋፍለውታል።
· ሌላ ይገባኛል የሚል ሀገር ከመጣ ከሁለቱ ሀገራት እኩል እንዲቀንስ ተስማምተዋል።
· ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ የሚሠራ ግድብ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት አጎናፅፏታል።

· በሌሎች ሀገሮች በወንዝ ላይ የሚሠራ ስራዎችን ለመከታተል የሚያስችል የቴክኒክ ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል አለ። የተጠቀሱትን ሀሳቦች ከአለም አቀፍ ህግ እና ተቀባይነት አለው መርህ አንፃር ማየቱ ተገቢ ነው።


በመጀመሪያ ደረጃ ግብፅ እና ሱዳን በ1929/በ1959 እኩል ተጠቃሚ ናቸው ብሎ መውሰድ ተገቢ አይደለም በ1929 ስምምነት ግብፅ ሱዳንን አላማከረችም ምክንያቱም በወቅቱ ሱዳን የግብፅ አንድ የግዛት አካል ተደርጋ ስለምትወሰድ ነበር።


በ1959 ስምምነት ደግሞ የሱዳን የውሃ ባለሙያዎች አስተያየት ግምት ውስጥ ሲያስገባ የሱዳን ባለስልጣናት ግብፅን በመፍራት እንዲፈርሙት ፕሮፌሰር አሊ ታሪክን በመጥቀስ ይከራከራሉ። ከሁሉም በላይ በስምምነቱ የታችኛው የተፋሰስ ሀገራት በተለይም 86% የውሃ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ ሀሳቧ አልተካተተም የስምምነቱም አካል አይደለችም። አንድ ስምምነት ተቀባይነት ያለው አለም አቀፍ ህግ ሊሆን የሚችለው ስምምነቱን በፈረሙት እና ባፀደቁት አካላት መካካል ብቻ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያም ሆነች ለሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት በሁለቱ ስምምነቶች የመገዛት ግዴታ የለባቸውም።


ድንበር ተሸጋሪ ወንዞችን በተመለከተ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ተቀባይነት ያለው መርህ የእኩል ተጠቃሚነት እና ከፍተኛ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች ናቸው። በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት የ1929 እና የ1959 ስምምነት ከ11 የተፋሰሱ ሀገራት ዘጠኙን ያገላል በመሆኑ እና ከላይ የተጠቀሱትን መርሆዎች የሚጥስ በመሆኑ በአለም አቀፍ ፍ/ቤት ቢሄድ ተቀባይነት አይኖረውም። ስምምነቶቹ በይዞታቸው የእኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሳይሆኑ የሚያገሉ (Discriminatory) በመሆናቸው በአለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት የላቸውም። ለነገሩ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ለመላክም ኢትዮጵያ መስማማት ይኖርባታል። እ.ኤ.አ. ሜይ 21 1997 የተመድ ለመጓጓዣነት የማይውሉ ድንበር ተሸጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም በወጣው ኮንቬሽን መሠረት ሁሉም የተፋሰሱ ሀገርት ወንዙን በሚጠቀሙበት ጊዜ የዕኩል (ፍትሀዊ) (ሚዛናዊ) አጠቃም መርህን በዋነኝነት መከተል እንዳለባቸው ያስቀምጣል። እኩል የመጠቀም መብት መርህ በተመለከተ አንዳንዶች ለሁሉም ሀገራት
እኩል ማከፋፈል ነው በማለት ይተረጉሙታል። ይህ ግን በአብዛኛው ተቀባይነት የለውም በኮኔቬክሽኑ መሠረት የእኩል (ፍትሃዊ) (ሚዛናዊ) መርህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚይዝ ነው (በአንቀፅ 6 መሠረት)


1. የጆኦግራፊ፣ የሃይድሮ ግራፊክ፣ የሃይድሮ ሎጅክ፣ የአርኪዮሎጂክ እና ሌሎች የተፈጥሮ ሁኔታ መመዘኛዎች
2. በተፋሰሱ የሚገኙ ሀገራት ያለው የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች
3. አንድ ሀገር ውሃውን ሲጠቀም በሌላኛው ተፋሰስ ሀገር ላይ ያለው ተፅዕኖ
4. በጥቅም ላይ ያለ እና እውቅ የውሃ አቅም
5. ውሃውን ለመጠበቅ፣ ለመከላከል፣ ለማበልፀግ ያለው ጠቀሜታ እና ለዚህ የሚውለው ወጪ
6. አማራጭ ውሃ ምንጮች


በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት ሀገራት መከፋፈል እንዳለባቸው ኮንቬሽኑ ያስቀምጣል።


በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት ያልተከፋፈለ ድንበር ተሸጋሪ ወንዝ አጠቃቀም በድርጅቱ ተቀባይነት አይኖረውም። ለእነዚህ መመዘኛዎች ቀረቤታ ያለው የቀኝ ግዛት ውሎች ሳይሆኑ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ነው። ስለዚህ ለግብፅ እና ሱዳን ዘላቂነት የሚያወጣቸው። የትብብር መዕቀፍ ስምምነት መሠረት መፈረም ነው። ለነገሩ ስምምነቱ ነፃ አባል ሀገራት 2/3ኛው ከፀደቁት አለም አቀፍ ተቀባይነት እና አስገዳጅነት ያለው ህግ ይሆናል። እስካሁን ስምምነቱ ኢትዮጵያ አጽድቃዋለች። ለመጀመሪያም ጊዜም ናይል በተመለከተ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ህግ ይሆናል።


በ1997 የተመድ ኮንቬክሽን መሠረት ከእኩል ተጠቃሚነት በተጨማሪ የከፋ ጉዳት ያለመድረስ መርህ ሌላኛው መመዘኛ ነው። የህዳሴው ግድብ በተመለከተ በግብፅ ላይ ትርጉም ያለው ጉዳት እንደማይደርስ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ አስቀምጣለች። እንደውም የግድቡ ስራ ሲጀመር ታላቁ መሪ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፍትሃዊ አጠቃቀም የሰፈነ ቢሆን ኖሮ የግድቡን ወጪ ሱዳን 20 በመቶ ግብፅ 30 በመቶ ሊሸፍኑ ይገባ ነበር ብለዋል። ባለሙያዎች እንደሚገልፁት በኢትዮጵያ የሚሠራ ግድብ ትነትን በመቀነስ ተጨማሪ ውሃ ያስገኛል። በኢትዮጵያ የሚሰራ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ የታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ከጎርፍ እና በደለል ከመሞላት ይከላከላል። የተመጠነ የውሃ ፍሠት አመቱን ሙሉ እንዲኖር ያስችላል። በተመጣጣኝ ዋጋ


የሃይል አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል ይላሉ። አንዳአንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ምክራቸውን ሲለግሱ ዘላቂው ስትራቴጂ የአባይን ወንዝ በዘላቀቂነት ለመጠቀም ውሃው የሚከማችበትን እንደ አስዋን ግድብ ከፍተኛ ትነት ካለበት ግብፅ እና ሱዳን ይልቅ ወደ ቀዝቃዛው የኢትዮጵያ ክፍል ማሸጋገር ነው ይላሉ “Will Ethiopia’s ‘grand’ new Dam Steal Nile Waters from Egypt” William Davison The Christian Science Monitor June 25,2013 ይመለከቱ።


ለነገሩማ ጉዳት ያለመድረስ ለእኩል ተጠቃሚነት ተገዢ እንደሆነ አለም አቀፍ ልምድ ያሣያል። ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍ/ቤት በዳንቡ ወንዝ አጠቃቀም ውዝግብ በተመለከተ ሀንጋሪ እና ስሎባኪያ ጉዳዩን አቅርበውለት ነበር። ፍ/ቤቱም የእኩል ተጠቃሚነት መርህ ሁለት ጊዜያት በመጥቀስ ብይን ሰጥቷል። ጉዳት ያለመድረስ መርህን ፍ/ቤቱ አልተጠቀመበትም። ይህ ማለት ደግሞ እኩል ተጠቃሚነት ቀዳሚ ጉዳት ያለመድረስ መርህ ከዛ ቀጥሎ የሚታዩ መሆኑን ያሳያል። በ3 ሀገራት የተቋቋመው የሦስትዮሽ ኮሚቴ የህዳሴው ግድብ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና በታችኛው የተፋሰስ ሀገራት የጎላ ጉዳት እንደሚያደርስ አስቀምጧል። ስለዚህ ግብፅ የ1929 እና የ1959 ስምምነት በመጥቀስ በአለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት ያለው መብት አለኝ የምትለው ስምምነቶቹ ሌሎችን የሚያገሉ እና ሚዛናዊ አጠቃቀም የሚጥሱ በመሆናቸው ተቀባይነት እንደሌላቸው መገንዘብ ይቻላል።


አንዳአንድ ግብፃውያን ሌላኛው የሚያቀርቡት የመከራከሪያ ነጥብ 55.5 ቢሊዮን ኪዪብ ሊትር ውሃ የመጠቀም ታሪካዊ መብት አለኝ። ይህም ተለምዳዊ አለም አቀፍ ህግ ሆኗል የሚል ነው። አንድ ልምድ ተቀባይነት ያለው አለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት የሚሆነው ተቃዋሚ ወገን ሳይኖር ሲቀር ነው። ይሁንና ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የመጠቀም መብት እንዳላት ለግብፅ እና ለሌሎችም በየጊዜው ከማሳወቋም በላይ ቀኝ ገዢዎች እና ግብፅ ኢትዮጵያን በማግለል የተዋወሉትን ስምምነቶች እንደማትቀበላቸው በተደጋጋሚ ለሀገራቱ እና ለአለም አቀፍ ተቋማት (ሊሊጎ ኦፍኔሽን እና ለተ.መ.ድ) በፁሁፍ መገለፃቸው ይታወቃል። በተለይ አፄ ሚኒሊክ አፄ ሃይለሥላሴ ተቋውሞዎች በፁሁፍ ሰፍረው ይገኛሉ። ስለዚህ ታሪካዊ መብት እና ልማዳዊ ህግ የሚለው ኢትዮጵያ ተቋውሟን የገለፀችበት ስለሆነ በአለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት አይኖረውም። ሲጠቃለል የአባይን ወንዝ በተመለከተ ለኤሌክትሪክም ሆነ ለሌላ አገልግሎት የሚውል አለም አቀፍ ህግ ኢትዮጵያን የሚደግፍ እንጂ የሚከላከል አይደለም የሚሻለው እውነታውን መቀበል እና በጋራ ማልማቱ ነው። 

 

በይርጋ አበበ

 

እስክስታን በጥምቀት በዓል ላይ የተለማመደው ወጣቱ መላኩ በላይ አሁን የደረሰበትን ስኬት ከማግኘቱ በፊት ረጅም እና አድካሚ አባጣ ጎርባጣ መንገዶችን አልፏል። አሁን ከበሬታን አግኝቶ ዓለም አቀፍ ዝናን ያገኘበትን የባህላዊ ውዝዋዜ (እስክስታ) ሙያዬ ብሎ ከያዘው ወደ 20 ዓመታትን አሳልፏል። በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ “አፓርታማ” ተብለው ከሚጠራው አካባቢ የሚገኘው “ፈንድቃ” የባህል ምሽት ቤት ደግሞ የመላኩ ችሎታ ነጥሮ የሚወጣበት፣ የእስክስታ እና የባህላዊ ሙዚቃ አምሮት ያለበት ታዳሚ ደግሞ አምሮቱን ‘የሚወጣበት’ ቤት ነው። የኑሮ ብዛት እና የእድሳት ማጣት ያጎሳቆላት ፈንድቃ የባህል ምሽት፤ ከውጭ ሆነው ለሚያዩዋት “እዚህ ግባ” የምትባል ባትሆንም ውስጧ ግን ስፍር ቁጥር የሌለው ቱባ ባህል እና ዘርፈ ብዙ ጥበቦችን ይዛለች። የፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት ባለቤት እና “የእስክስታው ንጉሥ” አርቲስት መላኩ በላይ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባህል የሳይንስና የትምህርት ማዕከል (ዩኔስኮ) ጋር በመተባበር እየጠፋ ያለውን የኢትዮጵያ አዝማሪዎችን ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ ብሎም ወደ ተሻለ የገቢ ምንጭነት እንዲቀይሩት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ይህን በተመለከተ ሰሞኑን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ እና ከጋዜጠኞች የተነሱ ጥያቄዎችን አቀናጅተን ለንባብ አብቅተነዋል።


ፈንድቃ ማነው? ምንስ ይሰራል?


ፈንድቃ የባህል ምሽት ወይም አዝማሪ ቤት ላለፉት 25 ዓመታት የባህል መዝናኛ አገልግሎት በመስጠት በብቸኝነት የዘለቀ አዝማሪ ቤት ነው። ይህ በአዲስ አበባ በካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘውና አገሪቱን ለመጎብኘት የሚመጡ የውጭ ሀገርና የአገር ውስጥ ቱሪስቶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ነዋሪ ለሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብና ለከተማችን ነዋሪዎች ልዩ ልዩ የባህል ውዝዋዜ እና የባህል አዝማሪ ምሽት አገልግሎት በማቅረብ የሚታወቅ አዝማሪ ቤት ሲሆን በስራውም ዓለም አቀፍ እውቅናን ለማግኘት ችሏል።


ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ፈንድቃ “ኢትዮ- ከለር” የተባለ ባንድ በማቋቋም እና በርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በተለያዩ አገራት የባህል ዝግጅቶችን በማቅረብ የሀገራችንን ባህላዊ ሙዚቃ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። ከባህላዊ ሙዚቃው ባሻገር በፈንድቃ ባህል ማዕከል ኢትዮ ከለር በሚል የሥዕል -ዓውደ ርዕይ እና የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን እንዲሁም የግጥም ዝግጅቶችን በቅታቸውን ጠብቀው እንዲቀርቡ ያደርጋል።


የአዝማሪ ሙዚቃ በኢትዮጵያ የ2000 ዓመት በላይ ታሪክ አለው። የአዝማሪ ሙዚቃ ሰዎች ሃይማታዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ በአጠቃላይ የግል አመለካከታቸውን በነፃነት የሚገልፁበት ነው። ይህም የአዝማሪዎች ሙያና የፈጠራ ችሎታቸው ለሀገር እድገትና ታሪክ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ለዚህም ይመስላል የድሮ አገር መሪዎች አዝማሪ ምን አለ?” ብለው የሚጠይቁት።


ዘርፉ ያን የመሠለ ታሪክና ክብር እንዲሁም ቁምነገር ቢኖረውም በአሁኑ ጊዜ ግን የአዝማሪ ሙዚቃ ተጫዎቾች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ለዚህም ምክንያቱ በርካታ ቢሆንም ለጥበቡ በማኅበረሰቡ የሚሰጠው ቦታ፣ የውጭ ወይም የምዕራብያዊያን ሙዚቃ ተጽዕኖ፣ ወደ ዕድገት ወይም ዘመናዊነት በሚደረገው ጉዞ አዝማሪ ቤቶች መፍረሳቸው ጥቂቶቹ ምክንያቶች ናቸው።


የዩኔስኮ ውድድርና የመላኩ ሃሳብ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳይንስ፣ የባህልና የትምህርት ድርጅት (ዩኔስኮ) በየዓመቱ ባህል እና ቅርስ ላይ ውድድሮችን ያዘጋጃል። ድርጅቱ በሚያዘጋጀው ውድድር ላይ በዓለም ላይ ያሉ ተወዳዳሪዎች “አሸንፍበታለሁ” ብለው የሚያምኑትን ሥራ “ንድፈ ሃሳብ (Proposal)” አቅርበው ይወዳደራሉ። በለስ የቀናቸው የአዱኛው አሸናፊ ሲሆኑ ያልቀናቸው ደግሞ አጃቢ ሆነው ይመለሳሉ። በ2016/17 ዓመት ድርጅቱ በዘርፉ ባወጣው ውድድር ላይ 900 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ቢሆኑም 899ኙ የኢትዮጵያዊው የእስክስታ “ጌታ” መላኩ በላይ አጃቢ ሆነው ተመልሰዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየቱን የሚሰጠው አርቲስት መላኩ “በውድድሩ አሸናፊ የሆንኩት ድርጅቱ በምን ላይ እንደምሰራ ሲጠይቀኝ በአዝማሪዎች ላይ መሥራት እንደምፈልግ ተናገርኩ። ምክንያቱም አዝማሪነት የተከበረ ሙያ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሙያው እየደከመ ነው። ባለሙያዎችም ሥራውን እየተውት መጥተዋል። ለዚህ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ተገቢውን ክብር እና ጥቅም አለማግኘት፤ እንዲሁም የዘመናዊነት ተፅዕኖ የሚሉት ይገኙበታል። እኔም ዓላማዬ ይህን የተከበረ ሙያ ወደ ቦታው መመለስ ነው” ብሏል። ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በሚፈልገው በዚህ ፕሮጀክት ምን ሊሰራ እንዳሰበ ተጠይቆ ሲመለስም ፕሮጀክቱን ዩኔስኮና አርቲስት መላኩ በላይ በጋራ የሚሰሩት ሲሆን እድሜያቸው ከ18-30 የሆኑ ወጣት የአዝማሪ ሙዚቀኞችን እና የባህል ተወዛዋዦችን ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማምጣት ልምድ ካላቸው አርቲስቶች ጋር ልምድ እንዲቀስሙ በማድረግ ኮንሰርቶችን በተለያዩ ቦታዎች እንዲያሳዩ ይደረጋል።


ወጣቶቹ ከኢትዮ- ከለር ባንድ ጋር በመሆን አራት ፌስቲቫሎችን በሁለት ዙር የሚያቀርቡ ሲሆን ይሄውም የመጀመሪያው ዙር በፈረንሳይ የባህል ማዕከል እና በጁፒተር ሆቴል ይቀርባል። ሁለተኛው ዙር ደግሞ የአደባባይ ፌስቲቫል ሲሆን በሀገራችን በታላቅ ድምቀት በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ በተመረጡ ቦታዎች ይቀርባሉ።


ይህ ዝግጅት ወጣት አዝማሪዎችን ሙያቸውን ለማሳደግና ለማሳየት እንዲሁም በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ዕድል ይፈጥርላቸዋል። በዚህም ከሚያገኙት ልምድና እውቅና በተጨማሪ ለውደፊቱ በሙያቸው ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ ይቻላል። በዚህ ዩኒስኮ ድጋፍ ባደረገበት የአዝማሪ ፌስቲቫል ላይ ፍላጎቱ ያላቸው ወጣቶች መሳተፍ ይችላሉ።


ፌስቲቫሉ በርካታ የሀገርና የውጭ ታዳሚዎችን የሚያሰባስብ ሲሆን የአዝማሪ ሙዚቃን እና ቱባውን የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ ከማስተዋወቁ ባሻገር የሀገራችን ወጣቶች ባህላዊ አርት ላይ እንዲሳቡ፣ እንዲሳተፉ እንዲሁም የአዝማሪነት ባህል እንድንኮራበትና ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚረዳ ፕሮጀክት ነው ተብሎለታል።


በሞት አፋፍ ላይ ያለው አዝማሪነት


ከኢትዮጵያ ቱባ ባህሎች አንዱ አዝማሪነት ቢሆንም አደጋ ላይ መውደቁን ቀደም ባሉት ክፍሎች አይተናል። ባለሙያዎቹ ስራውን ወደ መተው እና ልጆቻቸውን የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ የማይፈልጉ መሆናቸውን አርቲስት መላኩ ይናገራል። “ለዚህ ፕሮጀክት ወጣት እና ሥራውን ለመስራት ፍላጎት ያላቸውን አዝማሪዎች ለማግኘት ወደ ላሊበላ፣ ጎንደር አለፋ ጣቋሳ እና ባህር ዳር ሄጄ ነበር። በጉዞዬ የታዘብኩት ግን አዝማሪነት አደጋ ላይ መሆኑን ነው” ይላል። ምድር ላይ ያሉ ድምፆች ሁሉ እስክስታ ለመምታት በቂዎቹ የሆኑት ዳይሬክተር መላኩ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁ ሁለት የሲዲ ሙዚቃዎችን ቢያሳትምም፤ ለዓለም ያስተዋወቀው የአገሩ ባህል ግን አደጋ ላይ መውደቁን ይናገራል።


የኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ትግራይ እና አማራ አዝማሪዎች ተዝቆ የማያልቅ የጥበብ አውድማዎች መሆናቸውን የሚገልጸው መላኩ በላይ፤ ነገር ግን እነዚህን ተንቀሳቃሽ የቱሪስት መሥህብ እና ውድ ሃብቶች የኔ ብሎ የሚጠብቃቸው አካል ባለመኖሩ እየጠፉ እንደሆነ ተናግሯል። ለዚህ ደግሞ መፍትሄ ያለውን ሲያስቀምጥ “የአንባሳውን ድርሻ” መንግሥት መውሰድ እንዳለበት ይገልጻል። መንግሥት ባህልን የመጠበቅና የማሳደግ ሞራላዊ እና ህዝባዊ አደራ እንዳለበት አርቲስቱ ይናገራል። የአገሪቱ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከጎንህ ሆኖ እንዲሰራ ጠይቀኸው ነበር ወይ? ተብሎ ተጠይቆ ነበር። አርቲስት መላኩ ሲመልስ “የሚያሳዝን ምላሽ ነው የሰጡኝ። ቢሮክራሲያቸው ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል።


ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ለሚያዘጋጀው የአዝማሪዎች ፌስቲቫል ከመላው አገሪቱ የተመረጡ ስድስት እንስት እና ስድስት ተባዕት አዝማሪዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተው በፈንድቃ የባህል ምሽት ለአንድ ወር ስልጠና ይወስዳሉ። ሥልጠናው የሚሰጠው በሙያው አባቶችና እናቶች (አንጋፋ አዝማሪዎች) ሲሆን የሥልጠናው ትኩረት ማዕከሉ ደግሞ ወጣቶቹ ባለሙያዎች በራሳቸው እንዲተማመኑ የሚያደርግ እንደሆነ በአንድ ወቅት በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የእስክስታ ትምህርት (ኮርስ) ያስተማረው አርቲስት መላኩ ተናግሯል። አርቲስቱ አክሎም አደጋ ላይ ያለውን አዝማሪነት ማዳን የሚቻለው በዩኔስኮ ድጋፍ ወይም በውጭ አገራት ሰዎች ሳይሆን በራሳችን እንደሆነ አስምሮ ተናግሯል።

 

የፈንድቃ ቀጣይ ጉዞ


ፈንድቃ የባህል ምሽት በአርቲስት መላኩ በላይ የበላይነት መተዳደር ከጀመረ ከአስር ዓመታት በላይ ሆኖታል። አካባቢው በመልሶ ማልማት እንደሚፈለግ ሲገለፅ የቤቱ ባለንብረት በአምስት ሚሊዮን ብር ለአርቲስቱ ሸጠውለታል። የንብረቱ ባለቤት መሆን የቻለው አርቲስት መላኩም መንግሥት ለአካባቢው ይመጥናል ብሎ በደነገገው የህንጻ ደረጃ ቤቱን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ነው። 75 ሚሊዮን ብር ይፈጃል የተባለለትን ባለ ስምንት ፎቅ ህንፃ ለመገንባትም የህንጻውን ዲዛይን አሰርቷል።


አርቲስቱ ሲናገር “ቤቱን ለመገንባት አቶ ፋሲል ጊዮርጊስ የተባሉ ባለሙያ የአርክቴክቱንና የዲዛይኑን ሥራ በነፃ ሰርተውልኛል። ግንባታው ሲጠናቀቅ አገልግሎት የሚሰጠው ሙሉ በሙሉ የባህል ማዕከል ሆኖ ነው። ብዙ ሙዚቃዎቻችን ገጠር ላይ እንዲሁ የሚቀሩ ናቸው። የእኛ ባህል ማዕከል ሲገነባ ይህንን ለመታደግ የሪከርድ ስቱዲዮ ይኖረዋል” ሲል የባህል ሙዚቃዎችን በስቱዲዮ ቀርፆ በአርካይቭ ለማስቀመጥ እንደሚሰራ ተናግሯል። “ፈንድቃ ይህን የመሰለ ኃላፊነት ይዟል። ነገር ግን የመንግሥት እርዳታ ያስፈልገዋል” የሚለው አርቲስት መላኩ አያይዞም “ይህን ህንጻ ለመገንባት ወደ 75 ሚሊዮን ብር ይጠይቃል። ይህን ገንዘብ ደግሞ እኔ እስክስታ ወርጄ የማገኘው ገንዘብ ይገነባዋል ተብሎ አይገመትም። ውጭ አገር ሄጄ ሰርቼ የማመጣውን ገንዘብም ለአንጋፋ እና ወጣት ድምፃዊያንን (ለምሳሌ አርቲስት ፉንቱ ማንዶዬ) ጨምሮ ወደ 70 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንን ቀጥሬ የማሰራበት ነው” ይላል። በዚህም መሠረት ባህልን ከመጠበቅና ቱሪዝምን ከማስፋት አኳያ መንግሥት ከጎኑ እንዲሆን ጠይቋል።


ፈንድቃ የባህል ማዕከል በአሁኑ ሰዓት ከባህል ምሽት ቤቱ በተጨማሪ ለ12 ወጣት እና አንጋፋ ሰዓሊያን እንዲሁም የቅርፃ ቅርፅ ባለሙያዎች ስራቸውን እንዲያቀርቡ የምልከታ አዳራሽ (ጋላሪ) ከፍቶ ሥራዎቻቸውን በነፃ እንዲያቀርቡ እየደረገ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም በእውቅ እና አዋቂ ምሁራን መሪነት በየወሩ የፓናል ወይይት ይካሄዳል። እስካሁን ከተካሄዱ ውይይቶች መካከልም የታሪክ ተመራማሪው አቶ ስሜነህ አያሌው የመሩት what is modernity in Ethiopian context በሚል ርዕስ የተካሄደው ውይይት ይገኝበታል። “በዲንካ የባህል ሙዚቃ” እና አጠቃላይ በአርክቴክት ላይም ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው በዚሁ የፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ነው።


እውን አዝማሪነት ከተደቀነበት የሞት (የመጥፋት) አደጋ ዩኔስኮ እና መላኩ በላይ ይታደጉት ይሆን? የሚለውን ጥያቄ መልሱን ለማግኘት ጊዜ ይፈልጋል። እስካሁን ባለው ሂደት ግን አርቲስቱን የሚመለከታቸው አካላት የሚደግፉት ከሆነ የታሰበው ባህልን የመታደግ ተግባር እውን ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ሰጭ ምልክቶች ታተዋል።

Page 1 of 186

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us