መድረክ ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጻፈ

Wednesday, 13 January 2016 14:28

-    ለተጎዱ ወገኖች ካሳ እንዲከፈል ጠይቋል

 

ኢህአዴግ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተከሰተውን ሕዝባዊ አመጽ ጋር ተያይዞ ከተቀናቃኝ ኃይሎች ጋር እንዲመክር እንዲሁም ሠላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጎች ላይ ግድያ የፈጸሙ የጸጥታ ኃይሎች ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ ለተጎዱ ተገቢውን ካሳ እንዲከፈል መድረክ ጥያቄ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀመንበር በፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ፊርማ ለጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዳመለከተው  ኢህአዴግ ለሀገራችን ውስብስብ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሁሉ መፍትሄ እሰጣለሁ በማለት እራሱን ከማታለል እና ከመመፃደቅ ይልቅ ከመድረክ እና ሌሎች ህዝባዊ መሰረት ካላቸው ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመነጋገርና በመደራደር የፖለቲካ ምህዳሩ ነፃ፣ ፍትሀዊ እና ለሁሉም ተደራሽ በመሆን ለሀገራችን ችግሮች የጋራ መፍትሄ የሚፈለግበት ሁኔታ ለመፍጠር ፍቃደኛ መሆን ይኖርበታል ብሏል።

መድረክ በዚሁ መግለጫው የህዝቦቻችንን ጥቅሞች ማእከል ያላደረገ እና በጉዳዩ ህዝብን ያላሳተፉ፣ በልማት ስም የሚካሄዱ የመሬት ወረራዎች፣ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ጨምሮ፣ በአስቸኳይ በማስቆም የሀገሪቱ ሕገመንግስታዊ ድንጋጌዎች እንዲከበሩ ጠይቋል።

የመንግሥትንና የሕዝብ መሬት በመውረር የሚፈፀመውን ሕገመንግስታዊ ጥሰቶች በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ባካሄዱት ዜጎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉት ያልተመጣጠኑ የኃይል እርምጃዎች ባስቸኳይ ቁመው፣ እስካሁን ዜጎችን በመግደልና የአካል ጉዳት በማድረስ እርምጃ ላይ የተሳተፉት ሁሉ ለሕግ ተጠያቂነት እንዲቀርቡ፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩት የመድረክ አመራር አባላት፣ አባላትና ደጋፊዎች ሁሉ በአስቸኳ እንዲፈቱ እና የሕይወት ሆነ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ካሳ እንዲከፈል ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

በተጨማሪም “ፀረ-ሽብርተኛ” በማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትንና የፖለቲካ አቋምን የማንፀባረቅ መብትን በመፃረር የሚፈጸሙ ወከባዎችና እስራቶች ባስቸኳይ እንዲቆሙ፤ የታሰሩትም ዜጎች እንዲፈቱ እንጠይቃለን ብሏል።

መድረክ በተደጋጋሚ ለጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለፃፈው ደብዳቤ ምንም ዓይነት ምላሽ አለማግኘቱን በደብዳቤው ጠቅሷል።¾

ይምረጡ
(12 ሰዎች መርጠዋል)
1454 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1025 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us