የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማስፋፊያ አርባ በመቶ ደረሰ

Wednesday, 28 December 2016 13:49

 በግንባታ ላይ ያለው የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማስፋፊያ 40 በመቶ ደረሰ። በግንባታው ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡን የግንባታ ሳይቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ኃይሉ ለሙ፤ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የምድር ውስጥ ፋውንዴሽን ሥራው እንደዚሁም የሱፐር ስትራክቸሩ የኮንክሪት ስራው ተጠናቆ ግድግዳዎችን አልሙኒየምና መስታወት የማልበሱ ስራ እንደዚሁም ጣራ የማልበስና የማጠናቀቂያ (Finishing) ሥራ የሚቀር መሆኑን ገልፀውልናል። የፕሮጀክቱ ጊዜ 63 በመቶ መጠናቀቁ የተመለከተ ሲሆን አጠቃላይ ስራው ደግሞ 40 በመቶ የተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

ቀጣይ ስራዎቹ ከውጪ በፋብሪካ ተገጣጥመው የሚመጡ የግንባታ ግብዓቶችን የሚጠቀም በመሆኑ ስራውን በፍጥነት ለማከነውን ከፍተኛ እገዛ የሚኖረው መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ንጉሴ ተክሌ አመልክተዋል። የፕሮጀክቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፀጋየ ቃለ አብ በበኩላቸው፤  ነባሩ ኤርፖርት ከተቀመጠለት አቅም በላይ በዓመት እስከ 8 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግድበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀው አዲሱ የማስፈፋያ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ዓመታዊ መንገደኞችን የማስተናገድ አቅሙን በሶስት እጥፍ የሚያሳድገው መሆኑን አመልክተዋል።

 

አዲሱ የማስፈፋያ ፕሮጀክት በ345 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚከናወን ሲሆን ገንዘቡ በብድር የተገኘው ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ነው። የማማከሩን ስራ የሚሰራው የፈረንሳይ ኩባንያ ነው። ዲዛይን ያደረገው ደግሞ ሲፒጂ የተባለ የሲንጋፖር ኩባንያ ነው።

 

ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል 225 ሚሊዮን ዶላር ግንባታ በጀት ተይዞለት የነበረ ሲሆን ይሁንና ዝርዝር ጥናቱ ሲካሄድ የጠየቀው የወጪ መጠን 345 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ተገኝቷል። የማስፈፋያ ኤርፖርቱ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርገው መሆኑ ተመልክቷል። እ.ኤ.አ በጥር 2015  የተጀመረው ይህ የማስፋፊያ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እ.ኤ.አ ጥር 2018 የሚጠናቀቅ መሆኑን ኃላፊዎቹ ገልፀውልናል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
378 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 974 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us