በአስተዳደሮቹ አለመግባባት ምክንያት ነጋዴዎች ተጉላላን አሉ

Wednesday, 19 April 2017 12:22

“ሕጋዊ አሰራርን እስከተከተሉ ድረስ ልንተባበራቸው ዝግጁ ነን”

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 10 አስተዳደር

 

በምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የስራ ጊዜያችን እየባከነ ነው ሲሉ የዶሮ ማነቂያ አካባቢ ሥጋ ቤቶችና ግሮሰሪዎች ተናገሩ።

የወረዳው አስተዳደር በበኩሉ፤ ከተፈቀደላቸው በላይ ግንባታ ያካሄዱ ሥጋ ቤቶችን የማስፈረስ ስልጣንና ኃላፊነት ስላለብኝ ወደተፈቀደላቸው የግንባታ ደረጃ እንዲመጡ ደጋግሜ አስጠንቅቄያለሁ ብሏል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ዶሮ ማነቂያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በንግድ ስራ ከተሰማሩ ሥጋ ቤቶችና ግሮሰሪዎች መካከል 10 የሚሆኑት፣ የወረዳው የምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ደረጃቸውን ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡ በሚል እንዲታደሱ ማዘዙን ያስታወሱት የወረዳ 10 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮሐንስ አድማሱ፤ ከፈቃድ ውጪ ግንባታ ያከናወኑ ቤቶችን በሕግ አግባብ እንዲያስተካክሉ አድርገናል፤ አለፍ ሲልም በአስተዳደሩ መመሪያ መሰረት ሕጋዊ ግንባታ ያላከናወኑትን አፍራሽ ግብረ-ኃይል ተጠቅመን ንብረቶችን ወርሰናል ይላሉ።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት የባንቡ አጂጆ ሥጋ ቤትና ግሮሰሪ አስተዳዳሪ አቶ ሰይፈ ባንቡ እንደሚያስረዱት ደግሞ፤ በፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ መሠረት ከተፈቀደው በላይ የገነባነውን ለማፍረስ የወረዳው የግንባታ ፈቃድ ሠራተኞች ተገኝተው እንዲመለከቱ ቢጠይቁም ይህን ሳያደርጉ ቀርተው፤ ከስራ ሰዓት ውጪ በሆነ ጊዜ አፍራሽ ግብረ-ኃይል ይዞ በመምጣት ለግንባታ የተቀመጡ ንብረቶችን በመውሰድና በማፍረስ አጠቃላይ ግምቱ ከ200 እስከ 250 ሺህ ብር የሚደርስ ውድመት ደርሶብናል ይላሉ።

ይህ ውንጀላ ፍፁም ውሸት ነው የሚሉት የወረዳ 10 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዮሐንስ፤ አስተዳደሩ ከአካባቢው ነጋዴዎች ጋር ውይይት አድርጐና ተስማምቶ ወደተፈቀደው የግንባታ መጠን አብዛኞቹ ቢመጡም፤ ቀሪዎቹ ግን አናፈርስም በማለታቸው መመሪያው በሚፈቅደው መሠረት በአፍራሽ ግብረ-ኃይል እንዲፈርስ አድርገናል ብለዋል። ይህንንም በማድረጋችን አስተዳደሩ ከ40 ሺህ ብር በላይ አውጥቷል። የወረስነው ንብረትም ቢተመን ያን ያህል አይሆንም ሲሉ ተደምጠዋል።

ለግንባታ ያዘጋጀነው ንብረት ተወርሶብናል፤ አሁን ላይ መገንባት ባለመቻላችን ስራችን ተስተጓጉሏል የሚሉት የአካባቢው ሥጋ ቤቶችና ግሮሰሪዎች መፍትሄ እንፈልጋለን ይላሉ። አስተዳደሩ በበኩሉ የተወረሱ ንብረቶች በመመሪያው መሠረት አይመለስም። ከፈለጉ ደረሰኝ እናዘጋጅላቸዋለን ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የምግብና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ከዓመት በፊት በ10/04/2008 ዓ.ም በፃፈው የእግድ ማንሳት ደብዳቤ መሠረት፤ የተፈለገው እርምት በመደረጉን ጠቁሞ ድርጅቱ ወደአገልግሎት እንዲገባ ቢፈቅድም ወረዳው ግን ገና ነው ይላል። ይህንንም አለመግባባት በተመለከተ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዮሐንስ፤ “በወቅቱ በመድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር በኩል ስህተት ተፈጥሮ ነበር። አሁን ላይ ያሉት ኃላፊዎች ደግሞ ማስተካከያ አድርገዋል” ያሉ ሲሆን፤ በቀጣይ ግን ከነጋዴዎቹ ጋር በትብብር ለመስራት ሕጋዊ መንገድን ተከትለው እስኪመጡ ድረስ ችግር የለብንም ብለዋል።¾     

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
400 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 821 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us