በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዋና ከተማ የባህል ማዕከል ሊገነባ ነው

Wednesday, 19 April 2017 12:24

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባህልና ኪነ-ጥበብ ከማሳደግና ከማስተዋወቅ አንፃር ጉልህ ሚና ይጫወታል የተባለለት ግዙፍ የባህል ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ተገለፀ።

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል እና ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ለሰባተኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀውን የባህል ሳምንት አስመልክቶ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገልጿል። ይገነባል የተባለው የባህል ማዕከል ደረጃውን የጠበቀና የክልሉን ባህላዊ እሴቶች ያማከለ ነው ሲሉ የርዕሰ መስተዳደሩ ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ተናግረዋል። ለቱሪስት መስህብነትና ለባህል ጥናቶች አስፈላጊ ግብዓት ያሟላ ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ይህ የክልሉ ባህል ማዕከል በባህል ሳምንቱ ድግስ ታጅቦ የመሠረት ድንጋይ የሚጣልለት ሲሆን፤ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀ፤ እሳካሁንም የመሬት ርክክብና የህንፃ ዲዛይን ስራው በከፊል መጠናቀቁን አቶ ታምሩ ባጫ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መስተዳድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ከተለያዩ ክልልሎች የተወጣጡ የባህልና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ የባህል አምባሳደሮች በተገኙበት ከሚያዚያ 16 እስከ 21 ቀን 2009 ዓ.ም “የአብሮነት ባህላችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል በአሶሳ በተሰናዳው በዚህ የባህል ሳምንት ላይ የጥናት ወረቀቶች ይቀርባሉ፤ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ፤ የባህል ትርኢቶችና አዝናኝ ክንውኖች ይኖራሉ ሲሉ የተናገሩት ዶ/ር እልፍነሽ ኃይሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ናቸው።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ብሔረሰቦችን ባህልና ማንነት ከማስተዋወቅና ከማበልፀግ አንፃር በየዓመቱ የሚከበረው የባህል ሳምንት ከዚህ ቀደም በሀረር፣ በጉራጌና በባህርዳር ተከናውኖ እንደነበር በመግለጫው ተጠቅሷል።

በአሶሳ ከተማ በሚከናወነው የባህል ሳምንት ላይ ከተማዋ “የማንጎ ከተማ” መሆኗን ለማስተዋወቅ እንሰራለን የተባለ ሲሆን፤ በባህላዊ ምርቶች ዙሪያ የገበያ ትስስር እንደሚደረግም ሰምተናል። ክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መዳረሻ ከመሆኑ አንጻር የቱሪስት መዳረሻነቱ ጨምሯል ያሉት የአስተዳደሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ፤ ይህም ለክልሉ ባህልና ቱሪዝም ዕድገት ትልቅ እድል ነው ብለዋል። እንደክልል የቱሪዝም መስህቦችን ከማስፋት አንፃር የባህል ሳምንቱ ተመርቆ ለጎብኚዎች ክፍት የሚሆነው “የሼህ ኦጀሌ የችሎት አዳራሽ” እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በቀጣይ የመሀሙድ ባንጃውን ቤተመንግስት እድሳት ተደርጎለት ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆን የሚያስችል የጥገና ስራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

በባህል ሳምንቱ ከሚከናወኑ ፕሮግራሞች መካከል ለሀገር በቀል ዕውቀቶችን እውቅና የመስጠት እና የክልሉን የቱሪስት መስህቦች የሚያስተዋውቁ የህትመት ውጤቶችን በይፋ የማስመረቅ ስነስርዓት ይኖልም ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ባህላዊ እሴቶች ላይ የሚያተኩሩ ሁለት መፅሀፍት እንደሚመረቁ ተጠቁሟል።

ለአንድ ሳምንት በሚከበር የባህል ሳምንት ብቻ መሠረታዊ ለውጥ አይመጣም ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተሯ፤ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣና ከባህል ወረራ እንድንጠበቅ የሚያደርጉ ጥናቶችን ለውይይት እናቀርባለን ብለዋል። በየአመቱ በሚከበረው የባህል ሳምንት የባህል ማዕከላት የልምድ ልውውጥ መኖሩን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ማዕከላቱ ከህንጻ ግንባታነት በዘለለ አመለካከት ላይ ለውጥ የሚያመጡበት አሰራር እንዲኖራቸው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።  

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
379 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 851 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us