በአዲስ አበባ በአራት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ተላላፊ ባልሆኑ ሕመሞች ከተያዙ ሰዎች ግማሽ ያህሉ ሞተዋል

Wednesday, 28 June 2017 11:20

በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በአራት ተከታታይ ዓመታት ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ከተያዙ ሰዎች መካከል 51 በመቶ ያህሉ ለህልፈት መዳረጋቸውን ጥናቶች አረጋገጡ። ይህ የተገለፀው ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት በካፒታል ሆቴል ባሰናዳው የምክክር አውደ-ጥናት ላይ ነው። በአውደ ጥናቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ተላላፊ ያልሆነ ህመም መንስኤዎችን ለመግታት የአገሪቷ ቀጣይ ተረካቢ በሆኑ 27 ሚሊዮን ወጣቶች ላይ መስራት እንደሚያስፈልግም የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ መስራችና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አስተባባሪ አቶ ወንዱ በቀለ ሲናገሩ ሰምተናል።

በአውደ-ጥናቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ በበኩላቸው፤ ወጣቶችና ታዳጊዎችን ለሱስ የሚጋብዙ ማስታወቂያዎች ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባ አመልክተዋል። አክለውም ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች የጤና ችግር ብቻ ሳይሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ የሚፈጥሩ ችግሮችም ናቸው ሲሉ አስታውቀዋል።

አብዛኛው ወጣትና ታዳጊ ክፍሉን የሚጎዳው ነው የተባለለት እንደጫት፣ አልኮል መጠጥና የጣፋጭ ምግቦች ማዘውተር ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች መዳረጋቸው አይቀርም የሚል ሃሳብ ከመድረኩ ተሰምቷል። እንደመፍትሄም ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ለመከላከል በአምስት ነጥቦች ዙሪያ በጥብቅ መስራት እንዳለበትም ተጠቁሟል። የአመጋገብ ስርዓታችንን በማስተካከል፤ አካላዊ እንቅስቃሴን አዘውትሮ ማከናወን፤ ተመጣጣኝ የተክለ ሰውነት (አቋም) እንዲኖረን መስራት፤ እንዲሁም ትምባሆ ባለማጨስና የአልኮል መጠጥን በመቀነስ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን አደጋ መከላከል እንደሚቻል ተጠቁሟል። ይህንን ማድረግ ከተቻለ በተለይም እንደስኳር፣ የልብ ህመምና የደም ግፊት የመሳሰሉ ህመሞችን 80 በመቶ መከላከል ሲቻል፤ ካንሰርን ደግሞ 40 በመቶ መከላከል ይቻላል ሲሉ አቶ ወንዱ በቀለ ይናገራሉ።

በማህፀንና የጡት ጫፍ ካንሰር፣ በህፃናት ካንሰር እና በትምባሆ ማገገሚያ ዘርፎች ላይ አተኩሮ የሚሰራው ማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ኢትዮጵያ፤ በአሁኑ ወቅት 90 ህጻናት እና 70 ሴቶች በመርዳት ላይ ይገኛል ተብሏል።

በዓመት እስከ 460 ሺህ ብር ለህፃናት የመድሐኒት ግዢ ወጪ ማድረጉ የአቅም ችግር እንደፈጠረባቸው በመግለፅ፤ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም መጠየቃቸውን ተናግረዋል። አሁን ላይ ከክልል ከተሞች የሚመጡትን የካንሰር ህሙማን ባሉበት ለመርዳት በተለያዩ ከተሞች የጤና ማዕከላትን የመገንባት ሃሳብ እንዳላቸውም ሰምተናል።    

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
300 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1081 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us