በአዲስ አበባ በዘጠኝ ወራት 338 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞቱ

Wednesday, 26 July 2017 12:42

 

-    ብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ኮንፍረንስ ይካሄዳል

 

በአዲስ አበባ ብቻ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 338 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ፤ 2 ሺህ 268 ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከ20 ሺህ 27 በላይ መሆኑንም ተጠቁሟል። ይህ የተነገረው በመንገድና ከመንገድ ጋር በተያያዙ መስኮች የሚሰሩ የተለያዩ አካላት የሚሳተፉበት “የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ኮንፍረንስ” ነሐሴ 18 እና 19 ቀን 2009 ዓ.ም በአፍሪካ ኮሚሽን አዳራሽ እንደሚካሄድ በተገለፀበት ወቅት ሲሆን፤ መረጃውን ይፋ ያደረጉት ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ናቸው። የኮንፈረንሱ አዘጋጆች ሉሲ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ጅማ ዩኒቨርስቲ መሆናቸው ባሳለፍነው አርብ (ሐምሌ 14 ቀን 2009 ዓ.ም) በሀርመኒ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል። ይህ ኮንፈረንስ በየዓመቱ በብሔራዊ ደረጃ እንደሚካሄድ ያስታወቁት አሰናጆቹ፤ ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ ዓለም አቀፍ ይዘት ኖሮት እንዲተገበር ማሰባቸውን ገልጸዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ በርካታ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ዓላማውም በአገራችን በመንገድ ትራፊክ አደጋ የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት እየተቀጠፈ፤ ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ እና ከፍተኛ ንብረትም እየወደመ ከምጣቱ ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገራችንን ገጽታ አሉታዊ መልክ እያላበሰ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ አደጋውን እንዴት መቀነስና የተሻለ የመንገድ አጠቃቀም መፍጠር ይቻላል? በሚሉና መሰል ጥናታዊ ሃሳቦች ዙሪያ መፍትሄ ጠቋሚ ጥናቶችን ማንሸራሸር ነው ተብሏል። ከጉባኤው የሚገኙት የጥናት ሃሳቦች ለፖሊሲ አርቃቂዎች እንደግብዓት ሆነው ከመቅረብም ባሻገር በማህበረሰብ ግንዛቤ ላይ የተሻለ ለውጥን ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጫ ወቅት ተወስቷል።

በጉባኤው ላይ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዙሪያ በርካታ ጥናት የሰሩ ባለሙያዎች፣ ህግ አውጪዎች፣ የትራፊክ ባለሙያዎችና አሽከርካሪዎች ይታደማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በመረጃና በማስረጃ ለሚዘረዘሩ ችግሮች ጥናታዊ መፍትሄም ይሰጣል ተብሏል። በተለይም ጅማ ዩኒቨርስቲ ከመንገድ ደህንነት ጋር በተቀናጀ ቀጣይነት ያለው ጥናት ያደርጋልም ተብሏል። ይህም በአገሪቱ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን መዝግቦ የሚያጠና ማዕከል እስከማቋቋም ታስቧል ብለዋል። በተያያዘም በትራፊክ አደጋ ወቅት የሚያጋጥም የድንገተኛ ህክምናን በተመለከተ የጅማ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ራሱን የቻለ የማገገሚያ ማዕከል ያቋቁማል ተብሎም እንደሚጠበቅ ሰምተናል።

የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ኮንፈረንስን አስመልክቶ በተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ዋነኛ ባለድርሻ አካል የነበረው መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በቦታው አለመገኘቱ ቅሬታ ፈጥሯል። በአንፃሩ ግን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ በኩል የኮንፈረንሱ አጋር መሆኑን አስመስክሯል። ይህ ሁሉ አደጋ ሲደርስ በአገራችን ከ500 ሺህ የማይበልጡ መኪናዎች ብቻ መኖራቸው አስገራሚ መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል።  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
277 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 148 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us