የቀድሞ ኢኖቫ ፓኬጂንግ ወደሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ተቀላቀለ

Wednesday, 26 July 2017 12:51

 

-    ፋብሪካው ጥገናና እድሳት ተደርጎለት ቅዳሜ ዕለት ተመርቋል

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አንድ አባል የሆነው የብሉናይል የፕሮፖሊንና ክራፍት ወረቀት ከረጢት ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሕንድ ባለሃብቶች እጅ የነበረውንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሐራጅ ጨረታ ያወጣበት በቀድሞ ስሙ ኢኖቫ ፓኬጂንግ በ99 ሚሊየን ብር በመግዛት አንድ ቅርንጫፍ በማድረግ ቅዳሜ ሐምሌ 15 ቀን 2009 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ። የቀድሞ ኢኖቫ ፓኬጂንግ፤ የብሉናይል የፕሮፖሊንና ክራፍት ወረቀት ከረጢት ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “ቁርቁራ” ቅርንጫፍ በሚል ተሰይሟል።

በቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኘውን ይኸንኑ ፋብሪካ ለማደስ ኩባንያው ተጨማሪ አራት ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉንም አቶ ኃይለማርያም ጉተኒ የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አስታውቀዋል። ብሉናይል የፕሮፖሊንና ክራፍት ወረቀት ከረጢት ማምረቻ ኃ/የተ/የግል ማህበር የዛሬ 25 ዓመት በቢሾፍቱ ከተማ ቃጅማ አካባቢ ተመስርቶ ሲሰራ ከቆየ በኋላ በመሥራች ባለአክስዮኖቹ ፍላጎት በሽያጭ ወደሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ እንዲዛወር መደረጉን አቶ ኃይለማርያም አስታውሰዋል። ፋብሪካው ከነበረበት ኪሳራም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲላቀቅ መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል።

የቀድሞ ኢኖቫ ፓኬጂንግ በሽያጭ ወደ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከተቀላቀለ በኋላ የብሉናይል የፕሮፖሊንና ክራፍት ወረቀት ከረጢት ማምረቻ ኃ/የተ/የግል ማህበር ቁርቁራ ቅርንጫፍ የቀድሞ ሠራተኞች የሥራ ዋስትናቸው ተረጋግጦ በሥራ ገበታቸው ላይ እንዲቀጥሉ መደረጉን ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር አስታውቀዋል። ፋብሪካውን ሥራ ለማስጀመር በተካሄደው ጥገና እና የማሻሻል ሥራ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች ባለሙያዎች ተከናውኖ መጠናቀቁም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። በኮንትራት ሲያገለግሉ የነበሩ የፋብሪካው 72 ያህል ሠራተኞችም በዕለቱ ቋሚ ሠራተኞች እንዲሆኑ መወሰኑን ይፋ አድርገዋል።

አቶ ጁላ ለማ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በሥነሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚገኙ ኩባንያዎች በቢሾፍቱ ከተማ ብዙ ባለሃብቶች በሌሉበት ወቅት በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩ ለከተማው ባለውለታ መሆናቸውን በማስታወስ ምሥጋና አቅርበዋል። በቀጣይም አስተዳደሩ ከሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ጋር ይበልጥ ተባብሮ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ፋብሪካውን በማደስና በመጠገን ተግባራት የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትና የፋብሪካው ሠራተኞች ከዕለቱ የክብር እንግዶች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

 የብሉናይል የፕሮፖሊንና ክራፍት ወረቀት ከረጢት ማምረቻ ኃ/የተ/የግል ማህበር ቁርቁራ ቅርንጫፍ የማዳበሪያ ከረጢቶችን፣ የሄሺያን ብትን ጆንያዎችን፣ የዕቃ ማሸጊያ ላስቲኮችን ያመርታል።

በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 25 ኩባንያዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል ሰባት ያህሉ በቢሾፍቱና አካባቢው በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ከዶ/ር አረጋ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
528 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 140 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us