በኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በላይ በእስር የቆዩ ሁለት ኤርትራውያን ጋዜጠኞች ተፈቱ

Wednesday, 04 October 2017 12:12

በኢትዮጵያ ከአስር ዓመታት በላይ በእስር የቆዩ ሁለት ኤርትራውያን የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች መለቀቃቸውን የአሜሪካ ድምጽ ቤተሰቦቻቸውን እና የኤርትራ ፕሬስ ፍሪደም ተሟጋቾችን ጠቅሶ ዘገበ  ተስፋልደት ኪዳኔ እና ሳለህ ጋማ በሳምንቱ መጨረሻ የተለቀቁ ጋዜጠኞች መሆናቸውን ቪኦኤ በዘገባው አስታውቆ፤ ሳሊህ ጋማ ወደኤርትራ የገባ ሲሆን፤ ተስፋልደት ግን አሁን ድረስ በኢትዮጵያ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች በመሆን የሚታወቀው ሲ.ፒ.ጂ እንደገለፀው በኤርትራ ቴሌቭዥን በፕሮግራም አቅራቢነት የሚሰራው ሳህሊ ጋማ እና ካሜራ ማኑ ተስፋልደት ኪዳኔ በቁጥጥር ስር የዋሉት፤ በታህሳስ ወር በ2006 (እ.ኤ.አ) የኢትዮጵያ ጦር በኬኒያ ሶማሊያ ድንበር አካባቢ ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት እንደነበር አስታውሷል አክሎም በሚያዚያ 2007 (እ.ኤ.አ) የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒትር ጋዜጠኞች በመንግስታዊው ቴሌቭዥን ጣቢያ አቅርቦ እንዳሳያቸው አስታውሶ፤ አብረዋቸው 41 ሰዎች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ቢቀርቡም ኤርትራውያኑ ጋዜጠኞች ግን ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትባቸው ቆይቷል ብሏል

አሁን ድረስ የሁለቱን ጋዜጠኞች መለቀቅ አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ ከሁለቱም አገር መንግስታት አለመውጣቱን ያስታወቀው ዘገባው፤ ሀገራቱ በፕሬስ ነፃነት አያያዝ ከዓለም የመጨረሻው ተርታ እንደሚገኙ ሲ.ፒ.ጄን ጠቅሶ አስታውሷል

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
359 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 774 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us