አሜሪካ በኤርትራ ላይ ሌላ ዙር ማዕቀብ ጣለች

Wednesday, 04 October 2017 12:22

የኤርትራ ዜጎችን ወደ አሜሪካ የመግባት እድል በሚያጠብ መልኩ የአሜሪካ መንግስት በኤርትራ ላይ ማዕቀብ የጣለ መሆኑን ከሰሞኑ አስታውቋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ከኋይት ሀውስ የተለቀቀው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ ኤርትራ የዚህ ማዕቀብ ሰለባ የሆነችው የሀገሪቱ መንግስት ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ተባባሪ አይደለም በሚል ነው።

 

አሜሪካ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሚሆኑ ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በሚል እ.ኤ.አ በ2000 “Trafficking Victims Protection Act” በሚል ያወጣችው ህግ ሀገራት በዚህ በኩል ተባባሪ እንዲሆኑ የሚጠይቅ ሲሆን በርካታ ዜጎቹ በመፍለስ ላይ የሚገኙት የኤርትራ መንግስት ግን በዚህ ጉዳይ ለመተባበር ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሀገሪቱን የማዕቀቡ ሰለባ እንደዳረጋት የአፍሪካን ኒውስ ዘገባ ያመለክታል። በዚህ ህግ መሰረት በአሜሪካ ተለይተው የሚፈረጁ ሀገራት፤ከንግድ ግንኙነትና ከሰብአዊ እገዛ ውጪ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ እገዛ ከአሜሪካ የሚያገኙበት ሁኔታ የማይኖር መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል።

 

ይሄንኑ የማዕቀብ ውሳኔ ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት እገዳው ተግባራዊ እንዲሆን በአስመራ ለአሜሪካ ኢምባሲ ቪዛ ክፍል ትዕዛዙን ማስተላለፉን ተከትሎ ኢምባሲው የተወሰኑ የቪዛ አይነቶች አገልግሎት እንዳይሰጥባቸው አድርጓል። እነዚህም የቪዛ አይነቶች ቢ-1፤ ቢ-2 እና ቢ1/ቢ2 በሚል ስያሜ የሚታወቁ ናቸው። አሜሪካ በዚሁ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ዙሪያ ተባባሪ አይደሉም እንደዚሁም በአሜሪካ የሚኖሩና በተለያየ ህገወጥ ድርጊት ውስጥ ተገኝተው የሚባረሩ ዜጎቻቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም ያለቻቸውን ሀገራት በመለየት የዚሁ ማዕቀብ ሰለባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኗን ስትገልፅ ቆይታ ነበር።

 

ይህ አሁን ክልከላ የተደረገበት የቪዛ አይነት ከኤርትራ መንግስት ይልቅ የበለጠ የሚጎዳው የኤርትራ ዜጎችን ነው የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
600 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 577 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us