የባሕርዳር ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ተማሪዎችና ማኔጅመንቱ አልተግባቡም

Wednesday, 04 October 2017 12:24

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ተቋም በየአመቱ ለ4ኛ ዓመት የምህንድስና ተማሪዎች አጠቃላይ ፈተና (Holistic exam) አልፈተንም ያሉትን ተማሪዎች ጋር ከተፈጠረው አለመግባባት ጋር ተያይዞ ተማሪዎቹን አሰናበተ።

የተማሪዎቹ ዋና ጥያቄም ፈተናውን ብናልፍም ባናልፍም ዩኒቨርሲቲው ወደ ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች ተቋማት እንደሚልከን ካረጋገጠልን ብቻ ነው የምንፈተነው የሚል መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በድረገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጅ ተቋማት አንዱ የሆነው የኢትዩጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት /EiTeX/ ተማሪዎች የዚህን ዓመት አጠቃላይ ፈተና (Holistic exam)  በተለመደው ሁኔታ ተፈትነው ወደ ተግባር ልምምድ ለመሄድ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ የቴክኖሎጂ ተቋም (ፖሊ ግቢ) 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ግን አንፈተንም በማለታቸው ዩኒቨርሲቲው ህግና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ረጅም ጊዜ ወስዶ በማወያየት ለማስረዳት ቢሞክርም ፈቃደኛ ስላልሆኑ ግቢውን በሰላም ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተወስኗል ብሏል። በዩኒቨርሲቲው ውሣኔ መሠረት ተማሪዎቹ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ግቢውን ለቀው መውጣት መጀመራቸው ታውቋል።

 

የዩኒቨርሲቲው መግለጫ እንደሚከተለው ተስተናግዷል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ተቋም በየአመቱ ለ4ኛ ዓመት የምህንድስና ተማሪዎች አጠቃላይ ፈተና (Holistic exam) እንደሚሰጥ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለልምምድ ኢንዲወጡ ይደረጋል። ነገር ግን በዚህ ዓመት ተፈታኝ የነበሩ የ4ኛ ዓመት የምህንድስና  ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የተማሪዎቹ ዋና ጥያቄም ፈተናውን ብናልፍም ባናልፍም ዩኒቨርሲቲው ወደ ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች ተቋማት እንደሚልከን ካረጋገጠልን ብቻ ነው የምንፈተነው የሚል ነው። ነገር ግን ጥያቄው የፈተናን ዓላማ እና ትርጉም ግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ ዩኒቨርሲቲው አልተቀበለውም። አጠቃላይ ፈተናውን ማለፍ ያልቻለ ተማሪን ወደ ኢንዱስትሪዎች ሂዶ እንዲሰራ ማድረግ ዩኒቨርሲቲው ከያዘው ጥራት ያለው ትምህርት የመስጠት ዓላማ ጋር የሚጣረስ ሆኖ አግኝተነዋል። ይልቁንም ዩኒቨርሲቲው ምናልባት የሚሰጠውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ካሉ ክፍተታቸውን በሂደት በመሙላት ብቁ ሲሆኑ ለልምምድ መላክ እንዳለበት ግን በፅኑ ያምናል።

በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጅ ተቋማት አንዱ የሆነው የኢትዩጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት /EiTeX/ ተማሪዎች የዚህን ዓመት አጠቃላይ ፈተና (Holistic exam)  በተለመደው ሁኔታ ተፈትነው ወደ ተግባር ልምምድ ለመሄድ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ የቴክኖሎጂ ተቋም (ፖሊ ግቢ) 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ግን አንፈተንም በማለታቸው ዩኒቨርሲቲው ህግና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ረጅም ጊዜ ወስዶ በማወያየት ለማስረዳት ቢሞክርም ፈቃደኛ ስላልሆኑ ግቢውን በሰላም ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ኢንድሄዱ የወሰነ ሲሆን በቀጣይ የሚኖረው ሂደት በማስታወቂያ የሚገለፅ  ይሆናል።¾

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
643 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 883 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us