የአፈጉባዔ አባዱላ የሥራ መልቀቂያ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

Wednesday, 11 October 2017 12:44

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ብዙም ባልተለመደ መልኩ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውና እሱንም ተከትሎ በቀጣይ ስለሁኔታው ለሕዝብ ለመናገር ቃል መግባታቸው እያነጋገረ ይገኛል፡፡

የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አባዱላ ገመዳ በመገናኛ ብዙሃን የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ከተነገረና የሕዝብ መወያያ አጀንዳ ከሆነ በኋላ ለመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ወሬው እውነት መሆኑን አረጋግጠው መልቀቂያቸው በመንግሥት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ስለሁኔታው በዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል፡፡ ይህ የአፈጉባዔው አባባል ምን ሚስጢር ይኖር ይሆን በሚል አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ ከርሟል፡፡ አፈጉባዔው ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸው የፖለቲካ ልዩነት ይሁን ወይንም የሥልጣን ሽኩቻ ወይንም ሌላ ምክንያት ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም፡፡

አቶ አባዱላ ገመዳ አሁን ካሉበት የአፈጉባዔነት ሃላፊነት በፊት በኢፊዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በሜጄር ጄኔራልነት ማዕረግ ያገለገሉ ሲሆን ወደሲቪል ከተመለሱ በኋላ የኦሮምያ ክልል በፕሬዚደንትን አገልግለዋል፡፡

አቶ አባዱላ ሰኞ ዕለት የሁለቱ ምክርቤቶች የጋራ የዓመቱ መክፈቻ ስብሰባ በመደበኛ ሥራቸው ላይ  የታዩ ሰሆን ትላንት ማክሰኞ የምክርቤቱ ስብሰባ በም/አፈጉባዔዋ ተመርቶአል፡፡

በተያያዘ ዜና የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዮት አንዱ አካል ተደርጎ በሚወሰደው፤ ኬኛ የመጠጥ አክሲዮን ማሕበርን በመወከል ትላንት ማክሰኞ በሸራተን አዲስ ሆቴል ከእንግሊዙ ካፒታል 54 ተብሎ ከሚጠራ ኩባንያ በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡

የአባዱላ አዲሱ እንቅስቃሴ ወደ ክልላቸው በመመለስ ክልሉን ለማገልገል ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ተወስዷል፡፡

ኬኛ ቤቬሬጅስ የተሰኘ ግዙፍ አክሲዮን ማህበር በግል ባለሀብቶች፣ በህዝብና በመንግስት ጥምረት ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነው የተመሰረተው።

ኬኛ ቤቬሬጅ የክልሉ መንግስት፣ ህዝብና ባለሃብቱን አስተባብሮ የሚመራው የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት አካል ነው።

ይምረጡ
(21 ሰዎች መርጠዋል)
2045 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 43 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us