የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ-እንዳስላሴ በረራ ጀመረ

Wednesday, 08 November 2017 18:13

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሣምንት ለአራት ጊዜ ወደ ሽሬ-እንዳስላሴ የበረራ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ።

 

የአዲሱን በረራ ተግባራዊነት ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንደገለጹት፤ የኢትየጵያ አየር መንገድ የሐገሪቱን ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማሳለጥ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎትን በአራቱም ማዕዘን በማዳረስ ሐገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል። ወደ ሽሬ እንዳስላሴ የጀመረው በረራም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን 20 ያደርሰዋል።


አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመመደብና የሀገር ውስጥ አየር ማረፊያዎችን በማዘመን በአህጉሪቱ በሀገር ውስጥ በረራ ትስስር ግንባር ቀደምት ሆኖ ቀጥሏል። በሀገር ውስጥ እና በአከባቢው ሀገራት የሚሰጠው የበረራ አገልግሎት ለደንበኞች ምቹና ተስማሚ የሆኑትን የ Q400 እና የB737 አውሮፕላኖች በማሰማራት በሰዓት አክባሪነታቸው ከሚመረጡ የዓለማችን አየር መንገዶች ተርታ ለመሰለፍ መብቃቱን ገልጾ። የሀገር ውስጥ በረራ አገልግሎትን የማስፋፋት ጥረታችንን በማጠናከር የጎብኚዎች ፍሰት፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ተደራሽ እንዲሆኑ እናደርጋለን ብሏል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በክልል ያሉ የአውሮፕላን ማረፊዎችን የማሻሻል ስራ በመተግበር በአክሱምና ጎንደር ከተሞች የምሽት በረራ በቅርቡ መጀመሩ የሚታወስ ነው። 

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
338 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 913 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us