የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

Wednesday, 08 November 2017 18:17

 

የቀድሞው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራርና አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላለቀላቸውን የሰማዊ ፓርቲ አመራሮች በትላንትናው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

 

በመኢአድ ፅህፈት ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ሰማያዊ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረጉት የጋራ ምክክር ሰማያዊ ፓርቲን በአባልነት ለመቀላቀል መወሰናቸውን አስታውቀዋል።


እንደ ኃላፊዎቹ ገለፃ ከሆነ አባላቱ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ናቸው። በዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ፓርቲውን መቀላቀላቸው የተነገረው የቀድሞው የአንድነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት መካከል ያልተገኙ ሲሆን እኛም በስልክ ደውለን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት የቀድሞው የአንድነት ለዲሞክራና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክርቤቱ ሴክሬተሪና በአዲስ አበባ አስተዳደር የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ነብዩ ባዘዘው የቀድመው የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰማያዊ ፓርቲን በይፋ ለመቀላለቀል የወሰኑ መሆኑን ገልፀውልናል። የቀድሞው የፓርቲው አባላት ሰማያዊ ፓርቲን ለመቀላለቀል ውሳኔ ማሳለፋቸውን እንጂ ገና ያልተቀላቀሉ መሆናቸውን ገልፀውልናል።


የቀድሞው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ውስጥ በተነሳው ውዝግብ ፓርቲው በሌሎች አመራራሮች መያዙን ተከትሎ ጉዳዩን በምርጫ ቦርድ ተይዞ በመጨረሻ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ካመራ በኋላ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የፀና መሆኑን ያመለከቱት አቶ ነብዩ፤ ከዚያ በኋላም አበላቱ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ መሆኑን አስታውሰዋል። ይሁንና የቀድሞውን የፓርቲው አባላት በመጥራት ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኋላ በስተመጨረሻ አዲስ ፓርቲ ከማቋቋም ይልቅ ሀገር ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ጋር በመቀላቀል ትግሉን መቀጠል ተመራጭ ተደርጎ የታየ መሆኑን አቶ ነብዩ አመልክተዋል።


ወደዚህ ውሳኔም ለመድረስ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መኢአድ ፅህፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ሰፊ ውይይት የተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።


በዚህም ስብሰባ ላይ የቀድሞው አንድነት የብሄራዊ ምክርቤት አባላት፣የስራ አስፈፃሚ አባላት የነበሩ፣ በክልልና በዞን ደረጃ የነበሩ የፓርቲው አባላትም በቀረበላቸው ጥሪ የተገኙ መሆኑ ታውቋል። ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በግንባርና በውህደት አብሮ ለመስራት ያመቸው ዘንድ ፕሮግራምንና ደንብን አሻስሽሎ ለመስራት ብዙም ችግር የሌለበት መሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አመልክተዋል።


በውጪ ያሉ የቀድሞው የአንደነት ፓርቲ ደጋፊዎችም የፓርቲው የቀድሞው አባላትና ደጋፊዎች ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቅለው እንዲሰሩ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል። በውጪ ያሉ እነዚሁ ደጋፊዎች የዚህ ውሳኔ አካል መሆናቸውን አመራሮቹ ጨምረው አመልክተዋል። 

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
405 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 991 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us