የዳሸን ባንክ ዘመናዊ ህንፃ በፕሬዝደንት ሙላቱ ተመረቀ

Wednesday, 08 November 2017 18:36

 

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም ዳሸን ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት ያስገነባውን ባለ 21 ወለል ዘመናዊና ግዙፍ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ በኢፌዴሪ ፕሬዝደነት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተመርቆ ወደ ሥራ ገብቷል።


የዳሸን ባንክ ፕሬዝደነት አቶ አስፋው አለሙ ዳሸን በ14 ሚሊዮን ብር የመነሻ ካፒታል እንደነበረው አስታውሰው፣ አሁን የ30 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል እዳለው አስታውቀዋል። አይዘውም ዳሽን ወደ ተወዳዳሪነት እና የዘመናዊ የባንክ ቴክሎጂ ባለቤት ለሚያደርገው ጉዞ “በ3ሺ 485 ካሬ ሜትር ቅጥር ግቢ ውስጥ በ2ሺ 690 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈና በ35ሺ145 ካሬ ሜትር የወለል ስፋት ያለው ባለ 21 ወለል ህንጻ መገንባቱ እና ማስመረቁ እንደ አንድ ትልቅ ማሳያ አድርገው” አቅርበዋል።


እንዲሁም የዳሸን ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተካ አስፋው “ባንኩ የቁጣባ ባህልን በማዳበር ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚልቁ ደንበኞችን አፍርቷል። ከእነዚህም ደንበኞቹ ከ30 ቢሊዮን ብር የሚልቅ ተቀማጭ ገንዘብ ሰብስቧል” ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ተካ አያይዘው እንዳስረዱት፤ ባንኩ ለ7ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል። የአጭርና የረጅም ጊዜ ብድር በመስጠትም በአገሪቱ የንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ማገዙን ጠቅሰዋል።


ለባንኩ የሥራ መመሪያ እንዲሰጡ ወደ መድረክ የተጋበዙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እንዳሉት የግል ባንኮች የቁጠባ ባህልን ከማዳበራቸው ባሻገር ሀብት በማሰባሰብና ለንግድ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት የሚሆን ብድር በማቅረብ ከፍተኛ ሚናን እየተጫወቱ የሚገኙ መሆኑን ገልፀዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራና አዳዲስ አሰራሮችን እንዲሁም ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ረገድም ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ጨምረው አመልክተዋል። “ይህ ደግሞ የእነርሱም አቅም እዲጎለብት ያደርገዋል። ባንኮቹ በተለያየ ደረጃ አቅማቸውን እያሳደጉ መምጣታቸው ደግሞ የፋይናንስ ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመንና አሳታፊ፣ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ” ይኖረዋል ብለዋል። ፕሬዝደንቱ አይዘውም፤ ለኢንዱስትሪው ተገቢውን ድጋፍ በማድረግም የኢኮኖሚ ሽግግሩ እንዲሳካ፣ የአገር ውስጥ የውጭ ምንዛሪ እንዲያድግና የወጣቶች የሥራ ባህል እንዲጐለብት ባንኰች በልዩ ትኩረት መንቀሳቀስ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አሳስበዋል።


ፕሬዝደንቱ ባስተላለፍት ማሳሰቢያቸው፣ ቁጥሩ ቀላል የማይሆን ማህበረሰብ አሁንም ድረስ ለፋይናንስ ሥርዓቱ ገና ተደራሽ ስላልሆነም በአማራጭ ቴክኖሎጂ ታግዘው አሰራሮችን በማጎልበትና በማስፋፋት መስራቱ ለነገ የሚባል አይደለምና የጋራ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ማሳደግ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል። ያለ ጠንካራና ዘመናዊ ፋይናንስ ዘርፉ ግቡን ሊመታ ስለማይችል አደረጃጀቱንና አሰራሩን ማዘመን፣ የሰው ኃይሉን አቅም ማጎልበት እንዲሁም የዘርፉን ምርጥ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመቀመር ውጤታማ ማድረግም የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል። ስለሆነም ዳሽን ባንክም በዚህ ስኬት ሳይዘናጋ ከዚህ ይበልጥ መስራት እንደሚኖርበትም ገልፀዋል።


የባንኩ ህንጻ አምስት መደበኛ፣ ሁለት የቪአይፒ፣ አንድ የጭነት፤ በጠቅላላው ስምንት አሳንሰሮች ያሉት ሲሆን፤ ሁለት የስብሰባ አዳራሽ የሠራተኞች መመገቢያ፣ ክሊኒክ፣ የጨቅላ ህጻናት ማቆያ፣ ጅምናዚየም፣ የባንኩ ታሪክ መዘክርና ከ170 በላይ መኪኖች ማቆም የሚያስችል ስፍራን ያካተተ ተደርጎ እንደተገነባ ታውቋል።


ዳሸን ባንክ ድፍን ምዕተ አመት ባስቆጠረው የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ታሪክ ውስጥ የአዲስ ዘመን ጅማሮ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለውን የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ካርድ በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ ነው።


ባንኩ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በማቅረብ፣ ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ በመስጠት፣ የፕሮጀክት እና ሥራ ማስኬጃ የአጭር የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ብድር በማቅረብ በሀገራችን ኢንቨስትመንት እና ንግድ እንዲስፋፋ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ነው።


ሀገራችን ከወጪ ንግድ፤ ከዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንትና ድጋፍ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ሀዋላ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግም የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ የሚገኝ መሆኑ ተመልክቷል። 

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
484 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 933 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us