ኤርትራ ማዕቀቡን በመተላለፍ የጦር መሳሪያ ግዢ እያከናወነች ነው

Wednesday, 15 November 2017 12:36

ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት የተጣለባትን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመተላለፍ የጦር መሳሪያ ሸመታን እያካሄደች መሆኑን የመንግስታቱን ድርጅት አጣሪ ምርመራን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ሰሞኑን ብሉምበርግ ባሰራጨው ዘገባ አመልክቷል፡፡ ሀገሪቱ ከመሳሪያ ሸመታ ባሻገር የተለያዩ ወታደራዊ ስልጠና የሚያገኙ ዜጎቿንም ወደተለያዩ ሀገራት በመላክ ወታደራዊ ሙያን እንዲቀስሙ እያደረገች መሆኗን ይሄው ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል፡፡

 

እንደ ዘገባው ከሆነ ሀገሪቱ እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2015  ዓ.ም ባሉተረ ጊዜያት ሀገሪቱ 13 የባህር ኃይልንና የአየር ኃይል ሰልጣኝ ካዴቶችን ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬት በመላክ ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠናን እንዲያገኙ አድርጋለች፡፡ ሌሎች ሰባት የሚሆኑ ደግሞ  በዚያው በተባሩት ኤሜሬት ወታደራዊ ኮሌጅ ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ሳይንስ ትምህርትን እንዲቀስሙ የተደረገ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት አጣሪ ቡድንን ሪፖርት ጠቅሶ ይሄው ዘገባው አመልክቷል፡፡

 

አጣሪ ቡድኑ ማዕቀቡን በመተላለፍ ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገራት ጋር በወታራዊ ሥልጠና እና በመሳሪያ ግዢ ግንኙነት ውስጥ መግባቷን ካረጋገጠባቸው መንገዶች መካከል አንደኛው ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ የኤርትራን መንግስት በዚያው በመክዳት ሌላ ሀገር ከሄዱ ኤርትራዊያን ነው፡፡

 

ኤርትራ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬት ካላት ልዩ ወታደራዊ ግንኙነት ጋር በተያያዘም ሰፊ የሆነ ወታደራዊ እርዳታ እያገኘች መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል፡፡ ሁኔታውን ውስብስብ ያደረገው ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤሜሬት በኤርትራ የጦር ሰፈር የመገንባቷ ጉዳይ መሆኑን ዘገባው ያመልክታል፡፡ ኤርትራ አሸባሪ ቡድኖችን ትረዳለች እንደዚሁም በጎረቤት ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ትገባለች በሚል የተባበሩት መንግስታት በሀገሪቱ ላይ ማዕቀብ እ.ኤ.አ በ2009 ሲጥል ሀገሪቱን ለማዕቀቡ እንድትገዛ የሚያደርግባቸው አሰራሮችን ያልዘረጋ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኤርትራ መንግስት ማዕቀቡን በመተላለፍ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬት፣ ከሩስያ፣ ከጣሊያንና ከቼክ ጦር መሳሪያ አቅራቢ ኩባንያዎች በተደጋጋሚ የጦር መሳሪያ ግዢ ያከናወነ መሆኑን ሪፖርቱን ዋቢ በማድረግ የብሉምበርግ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
446 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 893 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us