የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ በመጻፍ ያታለለው ግለሰብ ተቀጣ

Wednesday, 15 November 2017 12:38

ተከሳሽ ዮሴፍ አከበረኝ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በተቀማጭ ሂሳቡ የሚያዝበት ብር ሳይኖረዉ ቼክ በመፃፍ በሰራዉ የማታለል ወንጀል በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጉለሌ ምድብ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ሶስት ክስ መስርቶበታል።

 

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳዉ በ1ኛ ክስ ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 629 /1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው የማይገባዉን ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ የካቲት 1 ቀን 2009 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ክልል ልዩ ቦታው መቀጠያ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ የግል ተበዳይ ለሆነችው ወ/ሮ እታገኝ ምስጋናው ለተበደረው ብር ክፍያ የሚሆን በቼክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ የሚመነዘር የ121‚000 /መቶ ሃያ አንድ ሺህ ብር/ ቼክ ፅፎና ፈርሞ የሰጠ ሲሆን ሰኔ 05 ቀን 09 ዓ.ም የግል ተበዳይዋ ስትጠይቅ ባንኩ በተከሳሹ ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ ስለሌለው በቅርንጫፍ የተዘጋ መሆኑን ገልፃል።


በ2ኛ ክስ ተከሳሹ በተመሳሳይ ወንጀል መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም በግምት ከቀኑ10፡00 ሰዓት ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ክልል ልዩ ቦታው ቀጨኔ አደባባይ ኤልሳ ባርና ሬስቶራንት ውስጥ የግል ተበዳይ ለሆነው ለአቶ ነጋ አያሌው ለተበደረው ብር ክፍያ የሚሆን በቼክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ የሚመነዘር የ65‚000 ሺህ ብር / ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ ፅፎና ፈርሞ የሰጠ ሲሆን የግል ተበዳይ ሲጠይቅ ባንኩ በተከሳሹ ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ ስለሌለው በቅርንጫፍ የተዘጋ መሆኑን የገለፀ በመሆኑ በፈፀመው የሚመነዘር ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ ማውጣት ወንጀል ሲከሰስ እንዲሁም በ3ኛ ክስ ተከሳሹ በ2ኛ ክስ በተጠቀሰዉ ቦታ የግል ተበዳይ ለሆነው ለአቶ ፍርድአወቅ ስናፍቀው ለተበደረው ብር ክፍያ የሚሆን በቼክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ የሚመነዘር የ300‚000 ሺህ ብር/ ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ ፅፎና ፈርሞ የሰጠ ሲሆን የግል ተበዳይዋ ሲጠይቅ ባንኩ በተከሳሹ ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ ስለሌለው በቅርንጫፍ የተዘጋ መሆኑን የገለፀ በመሆኑ በፈፀመው የሚመነዘር ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ ማውጣት ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል::


ወንጀሉን የመረመረው የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተከሳሹ ከላይ በዐቃቤ ህግ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክሶች የተመሰረተበትን የቼክ ማጭበርበር ወንጀል ተነቦለት ስለ አድራጎቱ ሲጠየቅ “ወንጀሉን ፈፀሜያለሁ፣ ጥፋተኛ ነኝ፣ ቼኩም የራሴ ነው” በማለት አምኖ ቃሉን የሰጠ ሲሆን ዐቃቤ ህግ በሌሎቹ ክሶች ላይ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ ተከሳሽን ጥፋተኛ እንዲባል ፍርድ ቤትን ጠይቋል።


ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተከሳሹን መቃወሚያ ካለው እንዲያቀርብ ሲጠይቅ ተከሳሹም ጥፋተኛ ከተባለ የእምነት ክህደት ቃሌን መቀየር እፈልጋለሁ ያለ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የእምነት ክህደት ቃሉን መቀየር አልተቀበለውም::


የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርብ የተጠየቀዉ የፌዴራል ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመዉ በተደጋጋሚ በመሆኑ ተከሳሽን ሊያርም ሌሎችን ሊያስጠነቅቅ የሚችል የቅጣት ዉሳኔ እንዲወሰን በማለት ያመለከተ ሲሆን ተከሳሽ በበኩሉ ሪከርድ የሌለበት እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን በመግለጽ በቅጣት ማቅለያ እንዲያዝለት አቅርቧል።


የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት 5 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና በ3000 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በላከልን ዜና ዘግቧል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
474 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 941 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us