ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ስለሼህ ሙሐመድ ኩባንያዎች ወቅታዊ ሁኔታ ለሠራተኞቹ ማብራሪያ ሰጠ

Wednesday, 15 November 2017 12:40

 

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በኩባንያው ሊቀመንበር የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በሳዑዲ ከገጠማቸው እስር ጋር በተገናኘ ከማኔጅመንት አባላትና ከሠራተኞቹ ጋር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተወያየ።


ከሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሲኢኦ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል የተገኘ መረጃ እንደጠቀሰው ከሳምንት በፊት ከወደ ሳዑዲ አረቢያ በተሰራጨው ዜና ቁጥራቸው ከ208 በላይ የሆኑ ልዑላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለሐብቶች (ሊቀመንበራችንን ጨምሮ) በታላቁ የሪትዝ ካርልተን (Ritz Carlton) ሆቴል እንዲቆዩ በመደረግ ምርምራ እየተደረገባቸው መሆኑንና ሰሞኑንም (እነማን እንደሆኑ ባይጠቀስም) ሰባት ያህሉ መለቀቃቸውን ተገልጷል ብሏል።


የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሠር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ከፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሠሮች፣ ከዋና ሥራ አስኪያጆች እና ከሠራተኞች ጋር ጉዳዩን አስመልክተው ከተወያዩ በኋላ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። በዚሁ ውይይት ላይ ዶ/ር አረጋ በአጠቃላይ ሁሉም ሠራተኞች ሥራቸውን እንደተለመደው እንዲያከናውኑ፣ ኩባንያዎቹ ሁሉ የራሳቸው ሕጋዊ አመሠራረት እና ሂደት ስላላቸው ባጋጠመው ጊዜያዊ ችግር ምክንያት ስለማይደናቀፍ ሥራቸውን በትጋት ማከናወን እንደሚገባቸው አብራርተዋል።


ከሳዑዲ አረቢያ በተጨማሪ በተገኘ ዜና መሠረት ታግዷል የተባለው ገንዘብ የባለሐብቶቹን የግል አካውንት የሚመለከት እንጂ ያቋቋሟቸውን ኩባንያዎች የማይነካ እንደሆነ በመግለጽ ሠራተኛው በተረጋጋ መንፈስ ሥራቸውን እያከናወኑ እንዲቀጥሉ መመሪያ ሰጥተዋል። በዚሁ መሠረት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች በተረጋጋ መንፈስ ሥራቸውን በማከናወን ከሊቀመንበራችን የተሰጠንን ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል ሲሉ ዶ/ር አረጋ አሳስበዋል።


በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በጽ/ቤታቸው ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሼህ ሙሐመድ እስርን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። «በሳዑዲ አረቢያ ያሉትን ሼህ ሙሐመድ አልአሙዲን በተመለከተ በሚድያዎች ከሰማን በኋላ በተለያየ ደረጃ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ መንግሥት ኃላፊዎች ጋር ጉዳዩ ምን እንደሆነ ለማጣራት ጥረት እያደረግን ነው። እንደሚታወቀው በሀገራችን የተሻለ ኢንቨስትመንት የሚያካሂዱና ለሀገር ትልቅ ፍቅር ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ፤በእናታቸውም ኢትዮጵያዊ ናቸው። ስለዚህ ጉዳዩ ወዴት እንደሚያመራ መንግሥት በቅርብ የሚከታተለው ይሆናል። የሳዑዲ መንግሥት ሉአላዊ መንግሥት በመሆኑ የሚወስዳቸውን ሂደቶች ተከትሎ የሚካሄድ ይሆናል። በዲፕሎማሲ መስክ ግን እኛ ለኢትዮጵያ ካላቸው ፍቅር እንደዚሁም በአገራችን ካላቸው ኢንቨስትመንትና ለዜጎችም ከሚያደርጉት አስተዋፅኦ አኳያ ይሄ ጉዳይ ምን እንደሆነ በየጊዜው እያጠናንና እያወቅን የምንሄድበት ሁኔታ ይኖራል» ብለዋል።


አያይዘውም በኢትዮጵያ የሚገኙት የሼህ ሙሐመድ ኢንቨስትመንቶች ሥራቸውን እንደሚቀጥሉና መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።


የዛሬ 17 ዓመት የተመሠረተውና በዶ/ር አረጋ ይርዳው ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰርነት የሚመራው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በሥሩ 25 ኩባንያዎችን በማቀፍ ከ9 ሺ 395 በላይ ሠራተኞችን የሚያስተዳድር መሆኑ ይታወቃል።

ይምረጡ
(6 ሰዎች መርጠዋል)
1028 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 114 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us