የሥንፈተ ወሲብ ሕክምና በኢትዮጵያ ውጤታማ እየሆነ ነው

Wednesday, 29 November 2017 12:36

በይርጋ አበበ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የስንፈተ ወሲብ ህክምና በወንዶች በኩል ውጤታማ መሆኑን ዶ/ር አንተነህ ሮባ የተባሉ የሙያው ሐኪም ተናገሩ።

ዶ/ር አንተነህ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት ከአሜሪካ በመጣ ዘመናዊ የህክምና ማሽን ህክምና እየሰጡ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በእስካሁኑ የህክምና ሥራቸውም በወንዶች በኩል ውጤት ማምጣታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ግን ሴቶች የችግሩ ሰለባ ቢሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች ህክምናውን እያገኙ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።

በሽታው አስጊ መሆን የሚጠረጠር ባይኖርም የህክምናው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ህክምናውን በቀላሉ እንዳያገኙ ያደርጋል። የህክምናው ወጭ እንዲቀንስ የሚደረግበት መንገድ የለም ወይ? ተብለው ከጋዜጠኞች የተጠየቁት ዶ/ር አንተነህ “የህክምናው ዋጋ ከፍተኛ የሆነው የመድሃኒቱ ዋጋ በዶላር ስለሚገዛ ነው እንጂ የህክምናው ወጭ እና ለማሽኑ የሚከፈለው ዋጋ አይደለም። መድሃኒቱ በዶላር ከመገዛቱም በላይ የቀረጥ ዋጋውም ከፍተኛ ስለሆነ ነው” ብለዋል።

ዶ/ር አንተነህ ሮባ አያይዘውም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ያለው የአመጋገብ እና የኑሮ ሁኔታ በመቀየሩ ስኳርና ደም ግፊትን የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መስፋፋታቸውን ተናግረዋል። በተለይ ስኳር በአፍሪካ ኢትዮጵያዊን በቀዳሚነት እያጠቃት መሆኑን ተናግረዋል።

ይምረጡ
(16 ሰዎች መርጠዋል)
1338 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1037 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us