ባህርዳር ከተማ በ26 ቀበሌዎች እንደገና ተዋቀረች

Wednesday, 29 November 2017 12:41

ባህርዳር ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተስማሚ ትሆን ዘንድ በ6 ክፍለ ከተሞች እና በ26 ቀበሌዎች እንደገና መዋቀርዋ ተሰማ።

በተለይም ህዝቡ ቅሬታ የሚያነሳበት የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ በጽ/ቤቱ ብቻ ይሰጥ የነበሩ የተለያዩ ተግባራት ወደ ክፍለ ከተሞችና ቀበሌዎች በሂደትና ጽ/ቤት ደረጃ እንዲዋቀሩ መደረጉን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ክብረት መሀመድ  ለአማራ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት መዋቅር ተግባራዊ ለማድረግ አመራርን የመመደብ እና ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት የማዘጋጃ ቤቱን መዋቅር እየተሰራ ነው ብለዋል።

ይህም ወደፊት የከተማዋን ነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ከማሻሻል ባለፈ የከተማዋን ሁለንተናዊ ለውጥ ያመጣል ተብሏል።

በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ሊሰሩ ከሚገባቸው ተግባራት መካከል የከተማዋን አገልግሎት አሰጣጥ መዋቅራዊ አደረጃጀቱን መቀየር ቁልፍ ጉዳይ እንደነበር ተገልጾአል።¾

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
332 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 111 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us