ለ23 ወራት እስር ላይ የቆየው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ይግባኙ ተቀባይነት አገኘ

Wednesday, 29 November 2017 12:41

በይርጋ አበበ

የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቷል።

የፌዴራሉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ከትናንት በስቲያ ሰኞ በዋለው ችሎት ከወራት በፊት የፌዴራሉ የስር ፍርድ ቤት አቶ ዮናታንን “በፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ አንቀፅ ስድስት ላይ የተቀመጠውን ተላልፏል” ሲል የስድስት ዓመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት አሳልፏል።

የአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ዮናታን በፌስ ቡክ አድራሻው ያስተላለፈው ፅሁፍ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ ሕገ መንግሥታዊ መብቱን ተጠቅሞ ያደረገው እንጂ ወንጀል አይደለም የሚል ነበር ያቀረብነው ይግባኝ። ይህን እንዲከላከልም በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀጽ ስድስት ተጠቅሶ እንዲከላከል ነበር የተቀጠረው። ዮናታን በግል አድራሻ ያደረገው የሃሳብ ልውውጥ ፈጽም ወንጀል ስላልሆነ በነፃ ይሰናበት የሚል እና በአማራጭነትም የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን ተላልፏል የሚል አንዳችም ነገር የለም። ሽብርተኛ እና ሽብርተኝነት በሌለበት ሽብርተኝነትን አበረታቷል መባሉ አግባብ አይደለም። ስለዚህ ተመጣጣኝ ቅጣት ነው ሊሰጠው የሚገባ የሚል ነበር” ብለዋል። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱም የመጀመሪያውን አማራጭ ሳይቀበለው ቀርቶ ሽብርተኛ እና የሽብርተኛ ተግባር ሳይኖር አበረታቷል የሚለው የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ አድርጎታል። ነገር ግን አቶ ዮናታን በግል አድራሻው “የሰው ህይወት ከሚጠፋ የትኛውም ንብረት ቢወድም ይሻላል ሲል የፃፈው በመደበኛው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 257 ስር ጥፋተኛ ያደርገዋል ብሎ የሶስት ዓመት ከስድስት ወር ቅጣት አሳልፏል” ሲሉ ጠበቃው ተናግረዋል።

አቶ ሽብሩ ስለ ደንበኛቸው የጤንነት እና የእስር ቤት አያያዝ በተመለከተ ላቀረብንላቸው ጥያቄ “ከወራት በፊት በነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ከታሰረበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት በቪዲዮ ኮል ቀርቦ አይቸዋለሁ። ያኔ ደህና ነበር። በአሁኑ ቀጠሮ ግን አላየሁትም” ብለዋል።

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ታህሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም በሽብርተኝነት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
307 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 958 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us