ህወሓት ሊቀመንበሩን ጨምሮ ነባር አመራሮቹን አነሳ

Wednesday, 29 November 2017 12:44

-  /ሮ አዜብ መስፍን ታገዱ

 

 

የህወሓት ሊቀመንበርና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አባይ ወልዱ እንዲሁም ሌላው የሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ በየነ ምክሩ ከሥራ አስፈጻሚነት ወደ ማዕከላዊ  ኮሚቴ አባልነት ዝቅ እንዲሉ የተደረገ ሲሆን ወ/ሮ አዜብ መስፍን ደግሞ ከሥራ አስፈጻሚና ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለጊዜው እንደታገዱ የህወሀት ማዕከላዊ ኮምቴ ወሰነ። በህወሀት ውሳኔ መሰረት ተሰናባቾቹ ከኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚነትም የሚነሱ ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባላት መካከል አቶ አለም ገብረዋህድና አምባሳደር ዶ/ር አዲሳሌም ባሌማ በማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ተደርጓል።

በነሐሴ ወር 2007 መጨረሻ ህወሀት የመረጣቸው ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባላት ማለትም አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ አቶ በየነ ምክሩ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ ኣለም ገ/ዋሀድ፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ነበሩ። ነገርግን በአሁኑ ሰዓት ዶ/ር ቴዎድሮስ የዓለም አቀፉ ጤና ጥበቃ ኃላፊ ሆነው በመሄዳቸውና ሶስት የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባላት በመነሳታቸው በጎደሉት ምትክ ምናልባትም በዛሬው ዕለት ምርጫ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ሕወሀት ትላንት ለሕትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ሊቀመንበሩ ጨምሮ ምርጫ ስለማካሄዱ የተነገረ ነገር ባይኖርም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለፓርቲው ሊቀመንበርነት ሊመረጡ ይችላሉ የሚል ጠንካራ ግምቶች እየተሰጡ ነው።¾

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
605 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 951 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us