ለዘመናዊ ቄራ ግንባታ 70 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ተገኘ

Wednesday, 06 December 2017 12:50

ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ቦታ ማዛወርያ እና ማዘመኛ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ከፈረንሳይ ልማት ድርጅት 70 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ተገኘ። የብድር ስምምነት ሰነዱን ለማጽደቅ የተረቀቀው አዋጅ ትላንት ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቧል።

በረቂቅ አዋጁ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የብድሩ የወለድ መጠን አንድ ነጥብ 72 በመቶ ሲሆን የመመለሻ ጊዜው ሰባት ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ25 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው።

ሰነዱ እንደሚያብራራው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከተቋቋመ 60 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን፤ ቄራው የሚገኝበት ቦታ እና ሁኔታ ቄራውን ዘመናዊ አድርጎ ለማደስና ለማስፋፋት አመቺ አይደለም።  ቄራው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማይጠቀም በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ የእርድ አገልግሎት በመስጠት የሥጋና ተረፈ ምርቶችን በሚፈለገው መጠን ለአገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ለማቅረብ የማይችል ከመሆኑም በላይ አካባቢውን ከብክለት ለመከላከል የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ ባለመሆኑ ከባባዊ ብክለትን እያስከተለ ይገኛል። በመሆኑም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ የሚገኘውን ፍላጎት የሚያስተናግድ፣ ጤናማ፣ ንፁህ እና ጥራቱ የተጠበቀ ዘመናዊ የእርድ አገልግሎት የሚሰጥ እንዲሁም ከአከባቢ ብክለት ነፃ የሆነ ከፍተኛ አቅም ያለው ቄራ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሁን በሥራ ላይ ያለውን ቄራ በማንሳት ትልቅ አቅም ያለው ዘመናዊ የቄራ ኮምፕሌክስ በፉሪ ሃና ኢንዱስትሪ ዞን ለመገንባት ፕሮጀክት ቀርጿል።

ቄራው የኤክስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የሚገነባ ሲሆን፤ አምስት ዘመናዊ የእርድ መስመሮች እያንዳንዳቸው 100 ከብት በሰዓት የሚያርዱ፣ ሦስት ዘመናዊ የእርድ መስመሮች እያንዳንዳቸው 450 በግና ፍየል በሰዓት የሚያርዱ፣ እንዲሁም ዘመናዊና ዝግ ለእርድ እንስሳት እንክብካቤ (Animal Welfare) አገልግሎት የሚውል ትልቅ አቅም ያለው በረት ይኖረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የእርድ አቅሙን ታሳቢ ያደረገ የተቀናጀ የተረፈ ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከቄራው ጋር ተያይዞ የሚገነባ ሲሆን፤ ፋብሪካው ለኤክስፖርት አገልግሎት የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን ለማቀነባበርና ለማዘጋጀት ይውላል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ዘመናዊ የእርድ አገልግሎት በመስጠት ጤናማ፣ ንፁህ እና ጥራቱ የተጠበቀ የኤክስፖርት ደረጃውን የሚያሟላ የስጋ አቅርቦትና ተረፈ ምርት ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ በማስቻል የሀገራችንን የውጪ ንግድ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በብድር የተገኘው ገንዘብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትን ሙሉ በሙሉ በማዘመን ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ጥራቱን የጠበቀ ሥጋ እና ተረፈ ምርቶችን ለማቅረብ የሚያበረክተው አስተዋፅዖ የጎላ መሆኑን በረቂቅ አዋጁ ሰነድ ላይ ተመልክቷል። ፓርላማው፤ ረቂቅ አዋጁን ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
175 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 895 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us