የአዲስ አበባ ሕዝብ ለመልሶ ማልማት ስኬት ድጋፍ ተጠየቀ

Wednesday, 06 December 2017 12:51

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የተጎሳቆሉ የከተማዋን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት የከተማው ሕዝብ ትብብር እንዳይለየው ጠየቀ።

ኤጀንሲው በ2010 በጀት ዓመት አምስት አካባቢዎችን በፕሮጀክትና በተቀናጀ መንገድ ለማልማት የተግባር እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ብሏል። በዚሁ መሠረት በበጀት ዓመቱ ከቂርቆስ ክ/ከተማ ካዛንቺስ ቁጥር 3፣ ከአራዳ ክ/ከ አሜሪካን ግቢ ቁጥር 2 እና ገዳም ሠፈር፣ ከየካ ክ/ከተማ ሾላ መገናኛ፣ ከልደታ ክ/ከተማ ደግሞ ጌጃ ሠፈሮች እንዲለሙ ዕቅድ የተያዘላቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

  በመልሶ ማልማቱ የሚገኙት የአካባቢው ነዋሪዎች ኤጀንሲው በቅርቡ ስራ ሲጀምር አስፈላጊውን የተለመደ ልማታዊ ትብብር እንዲያደርጉ የጠየቀ ሲሆን ህብረተሰቡ የተዛባ መረጃ በሚሰጡ አካላት ወሬ እንዳይረበሽ መክሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የአዲስ አበባ መሀል ከተማ ለኑሮ የማይመቹና የተጎሣቆሉ አካባቢዎችን በጥናት እየለየ መልሠው እንዲለሙ ቀዳሚ ኃላፊነት ይዞ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል። ኤጀንሲው በልደታ፤ በሰንጋተራ በአፍሪካ ህብረት፣ በባሻ ወልዴና በሌሎችም አካባቢዎች ለዘመናት የቆዩና የደቀቁ ሠፈሮች በዘመናዊ መንገድ እንዲለሙ ማድረጉን አስታውሷል።

ኤጀንሲው መዲናዋ ከፌዴራል መንግስት ዋና መቀመጫነት አልፋ የአፍሪካ ህብረትና የበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መገኛ መሆኗንና የነዋሪዎችን የኢኮኖሚ ባለቤትነት ለማረጋገጥ በማሠብ በ2006 እና በ2008 በጀት ዓመት በርካታ አካባቢዎች መልሠው እንዲለሙ ዕቅድ ይዞ ስራውን በስፋት ጀምሮ የተወሠነ ርቀትን ተጉዟል። ይሁን አንጂ አሠራሩ ካለው ውስብስብነትና የተነሺዎችን የካሣ፤ የምትክ ቦታና ቤት አሠጣጥ ተመጣጣኝ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ልማቱን በዕቅዱ መሠረት ማከናወን አለመቻሉንም አልደበቀም።

ኤጀንሲው ካሁን በፊት የተጀመሩትንም ሆነ ቀጣይ የሚለሙትን አካባቢዎች በቦታው ላይ ማልማት የሚችልበትንና ማልማት ባይችል እንኳን  የተሻለና ተመጣጣኝ ካሣ ተከፍሎት መሠረተ ልማቱ በተሟላ አካባቢ መልሶ እንዲሠፍር የሚያስችል ቀልጣፋና ፍትሐዊ አሠራርን የሚያረጋግጥ አዲስ ስትራቴጂን ተግባር ላይ ማዋል ጀምሯል። በዚህ መሠረት ከዚህ በኋላ መልሶ ማልማቱ የተነሺዎችን ቅሬታ በሚያስወግድና በሚያዝለት ዕቅድ መጠናቀቅ በሚያስችል መልኩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራም በኦፍሻል ፌስቡክ ገጹ ላይ ጠቁሟል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
272 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1041 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us