የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስል ጀኔራሎችና ለዳይሬክተር ጄኔራሎች ሹመት ሰጠ

Wednesday, 06 December 2017 12:57

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ሀገሮች ለሚሰሩ ቆንስል ጀኔራሎችና በውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ለሚሰሩ ለዳይሬክተር ጄኔራሎች ሹመት መስጠቱ ታውቋል፡፡

በተሰጠው ሹመት መሰረት፣ አምባሳደር ዋህደ በላይ በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር ማዕረግ በሊባኖስ የቤይሩት የኢፌዴሪ ቆንስል ጄኔራል፤ አቶ ደመቀ አጥናፉ በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር ማዕረግ በህንድ ሙምባይ የኢፌዴሪ ቆንስል ጄኔራል ሆነው እንዲገለግሉ ተሹመዋል።

እንዲሁም አቶ ተፈሪ መለሰ በባለ ሙሉ ስልጣን ሚኒስትር ማዕረግ በቻይና ጓንዡ የኢፌዴሪ ቆንስል ጄኔራል እና ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማሪያም በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር ማዕረግ በተባበሩት አረብ ኤምሬት የዱባይ የኢፌዴሪ ቆንስል ጄኔራል ሆነው እንዲያገለግሉ ተሸመዋል፡፡

በተያያዘም በዋና መስሪያ ቤት በዳይሬክተር ጄኔራልነት የተሾሙት፤ አምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር- የጎረቤት አገራትና ኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አምባሳደር ነጋ ጸጋዬ- የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አምባሳደር አባዲ ዘሞ  የጎረቤት አገራትና የኢጋድ ጉዳዮች የሚኒስትሩ አማካሪ፤ ዶ/ር አምባሳደር መሃመድ ሃሰን የፖሊሲ ምርምርና ትንተና ዲፓርትመንት ዋና አማካሪ፤ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ መላኩ ለገሰ የእቅድና በጀት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ አዛናው ታደሰ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ ብርሃኔ ፍስሃ -የሰንዓ ፎረም እና የኤርትራውያን ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ ኤፍሬም ብዙአየሁ የአለም አቀፍ ህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ ሽብሩ ማሞ የፋይናንስና የግዥ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ ዘላለም ብርሃን የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል፤ አቶ አየለ ሊሬ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል እና አቶ በሪሁን ደጉ የኢንስፔክተር ጄኔራል ጽ/ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
328 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 104 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us