የጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ጉብኝትን የተወሰኑ የግብፅ እንደራሴዎች ተቃወሙ

Wednesday, 06 December 2017 12:59

 

-         እስራኤል የአል ሲ ሲ መንግስት እንዳይወድቅ ያላትን ስጋት ገለፀች

 

ፕሬዝደንት አል ሲሲ በዲሴምበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ጋር በካይሮ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ በተመለከተ በተነሳው አለመግባባት ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸውን ተከትሎ፣ አስራ ስምንት የግብፅ እንደራሴዎች ያላቸውን ተቃውሞ ለአፈ ጉባኤያቸው ለአሊ አብደላህ ማቅረባቸውን አል መስሪ አል ዩም ዘግቧል።

በግብፅ እንደራሴ አብደል ሃሚድ ካማለ እና አስራ ስምንት ተጨማሪ አባላት የቀረበው ቅሬታ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በግብፅ ፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዳያደርጉ የሚጠይቅ ነው።

እንደራሴዎቹ ያቀረቡት ምክንያት፣ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው ግፊት ከሕግ ከፖለቲካ እና ከኢኮኖሚ አንፃር ውሸት ነው፤ ይኸውም፣ የእኛን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነው። የናይል ውሃ ከብሔራዊ ደህንነታችን ጋር የተቆራኘ መሆኑን እና ቀይ መስመር እንደሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በፊት ማሳወቅ አለብን የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ዘገባው ያመለክታል።

እንደራሴዎቹ ለአፈ ጉባኤው ካቀረቡት መጠይቅ በተጨማሪም፣ ከግብርና ሚኒስትር፣ ከመስኖ ሚኒስትር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች እና ከደህንነት ባለሙያዎች ጋር ስብሰባ እንዲጠራላቸው አስፍረዋል።

እንደሚታወቀው የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አህመድ አቡ ዛይድ ባሳለፍነው ሳምንት ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የግብፅ እና የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች በካይሮ ውይይት እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

በተያያዘ ዜናም ሚድል ኢስት ሞኒተር ድረገጽ፤ እስራኤል የፕሬዝደንት አል ሲሲ መንግስት በቀጣይ በግብፅ ብሔራዊ ምርጫ በተፎካካሪ ወገኖች ሽንፈት እንዳይገጥመው የአሜሪካ መንግስት ሊያግዘው ይገባል ስትል መጠየቋን አስነብቧል።

እንደዘገባው ከሆነ እስራኤል ፕሬዝደንት አል ሲ ሲ በግብፅ ሕዝብ የነበራቸው ተቀባይነት እየደበዘዘ እንዳሄድ እና በቀጣይ በግብፅ በሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ ጥላ እንዳያጠላባቸው ስጋት እንዳላት አስታውቃለች። የእስራኤል መንግስት ስጋት ውስጥ የወደቀው፣ ፕሬዝደንት አልሲሲ  ለግብፅ ሕዝብ አመጣዋለሁ ያሉትን አስተማማኝ ደህንነት እና ብልፅግናን በተፈለገው ደረጃ ማቅረብ አለመቻላቸውን ከግምት በመውሰድ እንደሆነ ዘገባው ጨምሮ ገልፃል። 

የግብፅ እንደራሴዎችም ተቃውሞ ከግብፅ ሀገር አቀፍ ምርጫ ቀጣይ ውጤት ጋር የተያያዘ እንደሆነ በባለድርሻ አካላት ተገምቷል።¾

ይምረጡ
(4 ሰዎች መርጠዋል)
475 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 917 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us