ዳሸን ባንክ ለተለያዩ ተቋማት የ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ለገሰ

Wednesday, 13 December 2017 12:11


- የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በ700 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ፣


- አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ አካሄደ፣

 

 

የዳሸን ባንክ አክስዮን ማህበር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ካለው ፍላጎት ጋር በተያያዘ ለተለያዩ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።


የባንኩ ባለአክሲዮኖች ሐሙስ፤ ኅዳር 21 ቀን 2010 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ በነበረው የእራት ግብዣ ላይ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ካለው ፅኑ ፍላጎት በመነሳት ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ ናቸው ያላቸውን ተግባራት ለመደገፍ የ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ልገሳ አድርጓል። በዚህም መሰረት በጣና ሀይቅ ህልውና ላይ አደጋ የጋረጠውን የእምቦጮ አረም ለማስወገድ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል። በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ፤ ለኢትየጵያ ካንሰር ማህበር እና ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ለእያንዳንዳቸው የብር 700 ሺህ ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት ባንኩ ላደረገላቸው እገዛ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ የመላው ማህበረሰብ ድጋፍ እንዳይለያቸው ጥሪ አቅርበዋል።


በተጨማሪም የባንኩ ባለአክስዮኖች በሸራተን ሆቴል ሰሞኑን ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል በ700 ሚሊዮን ብር ለማሳደግ ውሳኔ አሳልፈዋል። ይህ በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው የሆነ የካፒታል ጭማሪ የባንኩን የፋይናንስ አቅም ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ብሎም ለተያያዘው ቀጣይነት ያለው ዕድገት አጋዥ እንደሚሆን በጉባኤው ተገልጧል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ባንኩ በተመሳሳይ ቀን ባከናወነው ጉባኤ የሥራ ዘመናቸውን ባጠናቀቁት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ የዘጠኝ አዲስ አባላትን ምርጫ አከናውኗል። ብሔራዊ ባንክ የአዲሶቹን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ እንዳጸደቀ ሥራቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
213 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 145 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us