ከ374.8 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ሽያጭ አሜሪካ የ57.9 በመቶ ድርሻውን ይዛለች

Wednesday, 13 December 2017 12:22

የስቶክሆልም ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም (ሲፕሪ) ዘገባ እንደሚለው በ2016፣ የዓለማችን 100 ትላልቅ የጦር መሣሪያ አምራች ኩባንያዎች ከጦር መሣሪያ፣ ከጦር መሣሪያ መለዋወጫ እና ከወታደራዊ አገልግሎት ቁሳቁሶች ሽያጭ 374.8 ቢሊዮን ዶላር አግኝተዋል።

 

መቀመጫውን ስቶክሆልም ስዊድን ያደረገው ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም በምህፃሩ SIPRI ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው የንግዱ ዋነኛ ተጠቃሚዎች በዩናይትድ ስቴትስ እና በምዕራብ አውሮፓ የሚገኙ የጦር መሣሪያ አምራች ኩባንያዎች ናቸው።


እንደ ሲፕሪ ዘገባ ከሆነ በዓመቱ የአሜሪካን ኩባንያዎች ሽያጭ በአራት ከመቶ ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 217.2 ቢሊዮን ዶላር አድጓል።


የአውሮፓ ሀገራት ሁለተኛውን ቦታ ሲይዙ ሩስያ ደግሞ በ7.1 በመቶ ሦስተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከአውሮፓ የኢጣልያ እና የፈረንሳይ ኩባንያዎች የጦር መሣሪያ ንግድ ዝቅተኛ ሲሆን ብሪታንያ እና ጀርመን ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።


ከ5 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ. 2016 የጥይቶች፣ ታንኮች እና ሰው አልባ የጦር አይሮፕላኖች በአጠቃላይ የጦር እና ለወታደራዊ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ መሣሪያዎች ንግድ ማደጉን ያስታወሰው ሲፕሪ፣ አያይዞም የጦር መሳሪያ ንግዱ ከቀደመው ከ2015 የ1.9 በመቶ ከ2002 ጋር ሲነጻፀር ደግሞ የ38 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስፍሯል። በአሜሪካን ወታደሮች የውጭ ስምሪት ምክንያት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሀገራትም ብዙ የጦር መሣሪያ አገልግሎት ቁሳቁሶችን በመሸመታቸው ነው እንደ ጥናቱ ያሳያል።


የዓለማችን ትልቁ የጦር መሣሪያ አምራች የዩናይትድ ስቴትሱ ኩባንያ «ሎክሂድ ማርቲን» F-35 የተባሉትን የጦር አውሮፕላኖቹን እንደ ብሪታንያ ጣልያን ወይም ኖርዌይ ለመሳሰሉ ሀገራት በመሸጥ ብዙ ገንዘብ አፍሷል። የኩባንያው ዋነኛ ደምበኛው ግን የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል ሲሆን፤ የሲፕሪ ጥናት በግልጽ እንደሚያሳየው ከአጠቃላዩ የዓለም የጦር መሣሪያ ንግድ 57.9 በመቶው በአሜሪካን ኩባንያዎች የተከናወነ ነው።


የሲፕሪ ተመራማሪዎች ቻይናም ከዓለም ዋነኛ የጦር መሣሪያ አምራቾች አንድዋ ልትሆን ትችላለች የሚል እምነት አላቸው። ሆኖም ቻይናን በተመለከተ አስተማማኝ መረጃ ስላላገኙ አሀዛዊ መዘርዝሩ ውስጥ አላካተቷትም።


በሌላ በኩል የሲፕሪ ዘገባ እንዳሳየው፣ የጦር መሣሪያ በመሸመት የሚታወቁት በርካታ የአፍሪካ እና የደቡብ አሜሪካ ሀገራት በነዳጅ ዘይት ዋጋ መቀነስ ሰበብ ገንዘብ ስላነሳቸው በ2016 ብዙ የጦር መሣሪያ መግዛት አልቻሉም። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
172 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 967 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us