የመኢአድ ዋና ፀሐፊ ፓርቲያቸውንና ደጋፊዎቻቸውን ይቅርታ ጠየቁ

Wednesday, 20 December 2017 12:35

-   በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የተጣለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና በየተቋማቱ የገባው የፀጥታ ኃይል በአስቸኳይ እንዲነሳ መኢአድ ጠየቀ

በይርጋ አበበ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ራሳቸውን ከፓርቲ አመራር አባልነት ማግለላቸውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ ፓርቲውን፣ የፓርቲውን አመራሮችና ደጋፊዎች ይቅርታ ጠይቀዋል።

አቶ አዳነ ለሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት ከመጀመሪያው ውሳኔ ላይ የደረሱት ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እያካሄዱት ያለውን ድርድር ስለሚያምኑበት ነው። ይህን አቋማቸውንም በፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባዎች ላይ ደጋግመው ቢገልፁም፤ ተቀባይነት ሊያገኝ አለመቻሉ ራሳቸውን ከፓርቲው አመራርነትና አባልነት ለማግለል እንዳበቃቸው ተናግረዋል።

ሆኖምበተናጠል የሚካሄድ ትግል ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ፓርቲዬን ይቅርታ ጠይቄ ወደ ቀድሞ ሥራዬ ልመለስ ጥያቄ አቅርቢያለሁሲሉ ተናግረዋል። አቶ አዳነ አክለውም፤ከዚህ ቀደም ስምምነት ላይ ባልደረስንባቸው ነጥቦች ላይ መተማመን እስከምንችል ድረስ አጀንዳ ማቅረብ እንደምችል ዝግ አለመሆኑን በማየት እና ከፓርቲያችን ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር ባደረግነው ውይይት ውሳኔዬን እንድከልስ ሆኛለሁብለዋል። በዚህ የተነሳም በፓርቲ አባልነታቸውና የኃላፊነት መደብ ሥራቸው ለመመለስ በፅሁፍ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

በተያያ ዜና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግቢ ውስጥ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና በየተቋማቱ የተሰማራው የፀጥታ ኃይል በአስቸኳይ እንዲነሳ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ አቀረበ።

ፓርቲው ታህሳስ 9 ቀን 2010 . ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እና በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀሰቀሱ ግጭቶች ያስከተሉት ሰብአዊ እልቂት ከዚህም በላይ ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር መንግሥት ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ ጠይቋል።

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፃፈውና የጠቅላይ / /ቤት ሠራተኛ ፈርመው በተቀበሉት የመኢአድ ደብዳቤ፤ከዚህ ቀደም የመኢአድ አመራር የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ምሁራንና ህዝቦችን ይህ አይነት ችግር እንደሚመጣ በመጠቆም የኢህአዴግ መንግሥት የአመራር ማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ፣ ለህዝቦች ጥያቄም ተገቢውን መልስ እንዲሰጥ ሲመክሩ እና ሲዘክሩ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግሥት ለእነዚህ ጥያቄዎች ጆሮ ሊሰጥ ባለመቻሉ የአገር አንድነት እና ጥቅም በከፋ ሁኔታ ሊሸረሸሩ የሚችሉ ድርጊቶች በመፈፀም ላይ ይገኛሉይላል።

የመኢአድ ደብዳቤ አያይዞም፤በዜጎች መካከል የተፈጠረው መለያየትና ግጭት የዜጎችን ህይወት ቀጥፏል። የአገራችንን አንድነትም አደጋ ላይ ጥሏልሲል የገለፀ ሲሆን፤ ይህን ችግር ለማስተካከልም አቶ ኃይለማርያም እና ካቢኔያቸው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ መኢአድ ጠይቋል።

በዚህም መሠረት የኢህአዴግ አመራሮች እስከታችኛው እርከን ድረስ ወርደው ከህዝብ ጋር እንዲወያዩ፣ በተለያዩ ክልሎች የተፈጠሩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ አስቸኳይ ውይይትና ምክክር እንዲደረግ፣ የአገር ጉዳይ ያገባኛል ከሚሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር የውይይት መድረክ መክፈት እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጣለው የግቢ ውስጥ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የፀጥታ ኃይል ከግቢው እንዲወጣ ሲል መኢአድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላከው ደብዳቤ አስታውቋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
125 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 943 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us