ኢትዮጵያ እና አርጀንቲና የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ

Wednesday, 20 December 2017 12:46

በይርጋ አበበ

ኢትዮጵያ ከአርጀንቲና ጋር የአየር ስምምነት መፈራረሟን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ ኮምዩኒኬሽን እና የማስተዋወቅ ሥራ አስኪያጅ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ሁለቱ አገራት የደረሱበት አዲስ ስምምነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራዚል ሁለት ከተሞች ያደርገው የነበረውን በረራ ቁጥር ይጨምርለታል በዚህ መሠረትም አየር መንገዱ ወደ ብራዚል ከሚያደርገው በራራ በተጨማሪ በምዕራብ አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ ከተሞች ጋር የሚያስተሳስር እንደሚሆን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቅርቡ ከሌላዋ ላቲን አሜሪካዊት አገር ቺሊ ጋር የስምምነት ፊርማ ለማካሄድ እቅድ መያዙን አቶ አንሙት ጨምረው ገልፀዋል።

ከአዳዲስ ስምምነቶች በተጨማሪ ከግሪክ እና ታይላንድ ጋር የበሩ ስምምነቶች መታደሳቸውን የገለፁት የአቪየሽን ባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ፤በተለይ ከታይላንድ ጋር የተፈረመው ስምምነት በመንገደኛ እና በጭነት አገልግሎት በሳምንት እስከ 14 የበረራ ምልልሶችን ለማካሄድ ያስችላል። በረራዎቹ የሚከናወኑት እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጫ ቀጥታ የሚፈቅድ ስምምነት የተደረገ ነውያሉት አቶ አንሙት፤ ስምምነቱም ከተደራራቢ ግብር እና ታክስ ነፃ የመሆን (Avoidance of Double Taxation) ከሌላ አየር መንገዶች ጋር በትብብር (Code Share) የመስራት መብቶችን ያካተተ እንደሆነ ገልፀዋል።¾   

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
93 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1070 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us