የኢንተለክችዋል ስኩል ተማሪዎች፣ የአሜሪካው የሕዋ ምርምር ጣቢያ ባዘጋጀው የፈጠራ ውድድር ተሳታፊ ሆኑ

Wednesday, 20 December 2017 12:54

የአሜሪካው የሕዋ ምርምር ጣቢያ (NASA) በ2017 ባዘጋጀው የኢንጂነሪንግ የፈጠራ ውድድር ላይ የኢንተለክችዋል ስኩል የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

ወርቃማ አበቦች (Team Golden Tulip) በሚል የተሰየመው የኢንተለክችዋል ስኩል ተማሪዎች ቡድን በሕዋ ምርምር ጣቢያው ውስጥ በሚገኘው የጀት ማስወንጨፊያ ላብራቶሪ ባዘጋጀው "Wiffle Ball Loft Contest" ውድድር ላይ ተካፍሏል። ውድድሩ፣ ተማሪዎቹ በፈጠሩት የማስወንጨፊያ መሣሪያ በመታገዝ በቁጥር አስር የሚሆኑ ትንንሽ ኳስ የሚመስሉ ክብ ነገሮችን፣ አስራ ዘጠኝ ፊት ርቀት ላይ ወደሚገኘው የፕላስቲክ ገንዳ ማወናጨፍ ነው። በአንድ ደቂቃ ውስጥ ስድስት ሜትር ርቀት ማወናጨፍ ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ሂድት የሚገጥማቸው ተግዳሮቶች፣ ከሚዋዥቀው ነፋስ በጣም ጥሩ የሆነ አንግል መወስድና ማወናጨፍ ይጠበቅባቸዋል፤ ኳሳንም እንዳትሰበር መከላከል ይጠበቅባቸዋል። እነዚህን ማከናወን ያልቻለ ከውድድሩ ውጪ እንደሚሆን ከአዘጋጆቹ መረዳት ይቻላል።


ወርቃማውን የአበቦች ቡድን ይዞ የተጓዘው መምህር ያሲን ጊራይ እንተናገረው፣ “በአፍሪካ ተማሪዎች ያላቸውን እምቅ ችሎታ ለማውጣት በተለይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያስችላቸው እድል ብዙም የላቸውም” ብሏል። አያይዞም፣ “በጉዟችን ብዙ ችግሮች ገጥመውናል። ለውድድሩ የሚሆን “wiffle balls” በኢትዮጵያ ገበያ የለም። ይህም በመሆኑ ለውድድሩ እንዲያግዘን ልምምድ ያደረግነው ከተለያዩ ፕላስቲኮች ባዘጋጀነው ኳስ ነው። ውድድሩን ግን እንደመልካም እድል እንደምንወስደው እናውቃለን።” ሲል መምህር ያሲን ተናግሯል።


ይህንን ከጀት የማስወንጨፍ ሥራዎች ጋር ተያያዥ ውድድሮችን በፈጠራ መልክ ተማሪዎች እንዲያዘጋጁት ሃሳቡን ያመነጨው በናሳ የጀት ማስወንጨፊያ ላብላቶሪ ውስጥ መካኒካል ኢንጅነር የሆነው፣ ፖል ማክኔል ነው። ውድድሩ ሥራ ላይ ከዋለ ሃያ ዓመታት አስቆጥሯል። የፖል ዓላማም፣ ተማሪዎችን ለኢንጅነሪንግ ዘርፍ ትምህርት ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ግፊት ማድረግ ነው። ውድድሩም ቀለል ያለና አዝናኝ እንዲሆንም ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። ከዚህ በፊት በዚህ ውድድር የተሳተፉ ተማሪዎችም በአካባቢያቸው ሲመለሱ በተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል።


በዚህ ውድድር ላይ ከአሜሪካ ከተለያዩ ግዛቶች የመጡ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። ከኢትዮጵያ ከመቀሌ ቅርንጫፍ ኢንተለክችዋል ስኩል (intellectual school) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሳተፉት ተማሪዎች ሳብሪና ዳዊት፣ ነይና ገ/ስላሴ፣ ሔርሜላ ኪሮስ፣ ሊዲያ ዘሩ፣ ሳሮን ገ/ስላሴ እና ሔርሜላ ብርሃኔ የተባሉ ታዳጊዎች ናቸው። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
139 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 146 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us