ሰማያዊ ፓርቲ ችግሩን በውስጥ አሰራር እንዲፈታ በሽማግሌዎች ተመከረ

Wednesday, 20 December 2017 12:57

በይርጋ አበበ

 

በሰማያዊ ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል ሲያሸማግሉ የነበሩ የአገር ሽማግላች ሁለቱን ወገኖች በማስማማት ስራቸውን መጨረሳቸውን ገለፁ።


ላለፉት አምስት ወራት ሁለቱን ወገኖች ሲያሸማግሉ መቆየታቸውን የገለፁት የሽማግሌዎቹ ተወካይ አቶ ተማም አባቡላጉ፤ “ሁለቱም ወገኖች የቅሬታቸውን ማስረጃ እንዲያመጡ ካደረግንና እሱን ከተመለከትን በኋላ ሌሎች ህጎችን በመመርመር ሁለቱም ወገኖች ችግራቸውን በውስጥ አሰራራቸው እንዲፈቱ ውሳኔ አስተላልፈናል” ብለዋል።


በእነ አቶ ይልቃል ጌትነት እና አቶ የሺዋስ አሰፋ በሚመሩት አዲሱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ለሁለት ዓመታት ቆይቷል። ይህንን ውዝግብ ለመፍታትም አምስት አባላት ያሉት የሽምግልና ኮሚቴ እንደተዋቀረ የገለፁት አቶ ተማም፤ አደራዳሪ ሽማግሌዎችን ማንነት ሲገልጹም “ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም፣ አቶ ይልማ ይፍሩ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ አቶ ተማም አባቡልጉ እና አንጋፋው የህግ ባለሙያና ጠበቃው አቶ ብርሃኔ ሞገሴ ናቸው” ብለዋል። ሽማግሌዎቹ ባስተላለፉት ውሳኔ ሁለቱም ወገኖች መስማማታቸውንም አቶ ተማም ጨምረው ገልፀዋል።


በሌላ ዜና በምዕራብ ዞን በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ህዝቦች የተፈጠረውን ግጭትና የደረሰው ሰብዓዊ እልቂት እንዳሳሰበው ሰማያዊ ፓርቲ ገልጿል።


ፓርቲው ትናንት ረፋዱ ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “ችግሩን የፈጠሩ አካላት ተጣርቶ አጥፊዎቹ ለህግ እንዲቀርቡ” ሲል ያስታወቀ ሲሆን “ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እመኛለሁ” ብሏል።


ፓርቲው በመግለጫው አክሎም “በአገሪቱ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁነኛ መፍትሄው ግልፅና ሁሉን አቀፍ ውይይት ማካሄድ ነው” ሲል አስታውቋል። ለዚህም በየሳምንቱ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን ያስታወቀው ሰማያዊ ፓርቲ፤ “በየሳምንቱ እሁድ ለምናካሂደው የውይይት መድረክ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የነበሩ የፓርቲያችን አባላት ለእስር ተዳርገውብን የቆዩ ሲሆን በጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ታስረው የነበሩ አባሎቻችን በ15ሺህ ብር ዋስ መለቀቃቸው አግባብነት የለውም” ሲል ቅሬታውን ገልጿል።


በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ታስረው የነበሩ የፓርቲው አባላት ግን ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ አሳይተው ከእስር መለቀቃቸውን የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ባልቻ ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
184 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 926 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us