የዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመኖሪያ ቤት በሐራጅ ተሸጠ

Wednesday, 20 December 2017 13:05

በእነ ብርጋዴን ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው ሲታይ የነበረው የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የአንዳርጋቸው ጽጌ የመኖሪያ ቤት በሐራጅ እንዲሸጥ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሠረት ሁለቱም ቤቶች በ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ሰሞኑን ተሸጡ።

 

የፍርድ ባለእዳዎች በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 175740 ሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቤታቸው በሐራጅ ተሽጦ ለፍርድ ባለመብት ይከፈል በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት የፍርድ ባለዕዳዎች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ናቸው።


በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 11 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ በአዲስ መንደር የቤት ስራ አክሲዮን ማህበር ውስጥ የሚገኝ ሽንሻኖ በመባል የሚታወቅና በጅምር ላይ ያለ ግንባታው ያልተጠናቀቀ ሪል እስቴት የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሲሆን የቦታው ስፋትም 613 (ስድስት መቶ አስራ ሶስት) ካሬ ሜትር ነው።


መኖሪያ ቤቱ ለሐራጅ ጨረታ የቀረበበት መነሻ ዋጋም ብር 344 ሺ 949 (ሶስት መቶ አርባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ዘጠኝ ብር) ሲሆን ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደው ግልጽ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ 6,380,000 (ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ ሺህ) ብር ተሸጧል ሲል በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፍትሀብሄር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።


በሌላ በኩል ደግሞ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአቶ አንዳርጋቸወ ጽጌ የመኖሪያ ቤት ከላይ በተጠቀሰው የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ መሰረት የሐራጅ መነሻ ዋጋ 361 ሺ 999 ብር (ሶስት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር) ሲሆን 73 ካሬ ሜትር እንደሆነም ታውቋል። በተካሄደው የጨረታ ውድድርም በ1000,000 (በአንድ ሚሊዮን ብር) ተሸጧል።


በመሆኑም የሁለቱ የፍርድ ባለዕዳዎች የመኖሪያ ቤት 7,380,000 (ሰባት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር) በሐራጅ ተሽጧል ሲል የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የላከልን ዘገባ ያሳያል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
572 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1075 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us