በኦሮሚያ ክልል በሀዊ ጉዲና እና በዳሮ ለቡ ወረዳዎች በርካታ ዜጎች ሕይወታቸውን አጡ

Wednesday, 20 December 2017 13:07

· ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅምላ ጭፍጨፋ መደረጉን አምነዋል

 


ከታህሳስ 5/2010 ጀምሮ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሀዊ ጉዲና እና ዳሮ ለቡ ወረዳዎች በኦሮሚያ እና በሶማሌ ብሔረሰቦች መካከል በተደረጉ ግጭቶች የበርካታ ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል እንዲሁም በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡


በዞኑ ሀዊ ጉዲና እና የዳሮ ለቡ ወረዳዎች ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጋር እንደማይዋሰን ቢታወቅም፣ በርካታ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጆች በእነዚህ ወረዳዎች መንደሮችን መስርተዉ ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር በመኖር ላይ ቢገኙም ዘግናኝ ጭፍጨፋ በአካባቢው መፈጸሙን በርካታ ምንጮች ለሰንደቅ ገልጸዋል፡፡


ከታህሳስ 5 እስከ ትናንት አመሻሽ በተሰነዘሩት ጥቃቶችም በተጠቀሱት ቀበሌዎች 29 የኦሮሞ እና ከ30 በላይ የሶማሌ ተወላጆች መገደላቸው ታውቋል፡፡ ከ360 በላይ መኖሪያ ቤቶችም ከነሙሉ ንብረታችዉ ወድመዋል።


ለግጭቱ መነሻ ነው የተባለው አቶ ዚያድ በሃዊ የተባለ ግለሰብ ጉዲና ወረዳ በተፈጠረዉ ግጭት የወንድሙን ሞት ተከትሎ ግብረ አበሮቹን በማስተባባር ሃዊ ጉዲና ወረዳ ላይ ከተፈጠረዉ ግጭት ጋር ምንም ግንኙነት በሌላቸዉ በጋዱሎ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ ንፁሃን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጆች ላይ ዘግናኝ የግድያ እርምጃ ፈጽሟል፡፡ እስካሁን በደረሰን ሪፖርትም በጋዱሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የ32 የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ህወታችዉን አጥተዋል፡፡


በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሀዊ ጉዲና እና ዳሮ ለቡ ወረዳዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የደረሰዉ እልቂት ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ይፋ አድርገዋል፡፡


አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ የተገደሉት ዜጎች ቁጥር ከሚነገረው ሁለት እጥፍ በላይ መሆኑን ነው፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
373 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 150 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us