ሳዑዲ አረቢያ በክፍያ እስረኞችን እየለቀቀች ነው

Wednesday, 27 December 2017 12:09

በሳዑዲ ከንጉሳዊያን የሥልጣን ሽኩቻ ጋር ተያይዞ በጥቅምት ወር የመጨረሻ ሳምንት ከታሰሩት ባለሥልጣናትና ባለሃብቶች መካከል የቀድሞዉን የገንዘብ ሚኒስትር አብርሃም አብዱልአዚዝ አል አሳፍን የክፍያ ገንዘብ ተደራዳራ ከእስር ሰሞኑን ለቃለች።

 

ትውልደ ኢትዮጵያዊውን የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ጨምሮ ሳዑዲ በዕውቁ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁም እስር ላይ ካዋለቻቸው ግለሰቦች መካከል የአገሪቱ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሳኡድ አል ዳዋሽም በተመሳሳይ ሁኔታ በገንዘብ ድርድር ከቁም እስሩ መለቀቃቸዉን የሃገሪቱ መንግስት ልሳን የሆነዉ እለታዊ አካዝ ጋዜጣ ዘግቧል።


ሁለቱ ግለሰቦች ከእስር የተለቀቁት በሃገር ዉስጥና በሌሎች ሃገሮች ያላቸዉን ንብረቶቻቸዉን፣ የግል አዉሮፕላኖቻቸዉን፣ የመዝናኛ ጀልባዎቻቸዉንና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦቻቸዉን ለመንግስት እንደመደለያ በመስጠት ነዉ ሲል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈልገ ታማኝ ምንጭ መግለፁን ዘገባዎች አመልክተዋል።


የሳውዲ መንግስት በሪትዝ ሆቴል በቁም እስር ያቆያቸውን ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላል ለመልቀቅ የ6 ቢልዮን ዶላር ክፍያ እየተጠየቀነዉ በሚል ዎል ስትሪት ጆርናል ወቀሳ እያሰማ መሆኑ ይታወቃል።


ልዑል አልዋሊድ ከአለማችን ባለፀጋ ግለሰቦች በ57ኛ ደረጃ የሚጠቀሱና 18 ሚሊዩን ዶላር የሚገመት አዱኛ ባለቤት መሆናቸው ይታወቃል።


የሳዑዲ መንግስት ሼህ አልሙዲንን ጨምሮ በርካታ ተዋቂ ግለሰቦችን ያሰርኩት ሙስናን ለመዋጋት ነዉ ቢልም የፖለቲካ ተንታኞች ግን ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ።


አዲሱ የሳዑዲ መንግስት ስልጣን ለማጠናከርና ከግለሰቦቹ ሀብት የተወሰነ ጥሪት ለመቃረም እስሩን እንደፈፅመ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ተደጋጋሚ ትችትና አስተያየት ሰጡበት ጉዳይ ነው።


በሪያድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው ሲሉም የሰብዓዊ መብት ተቃዋሚዎች ቅሬታ ማስማት መጀመራቸዉ የድሬ ቲዩብ ዘገባ ያስረዳል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
270 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1042 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us