ኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል በየዓመቱ ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ታገኛለች

Wednesday, 27 December 2017 12:14

ኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል በየዓመቱ 964 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪን ታገኛለች። የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን አወዳድሮ ሽልማት  ለመስጠት ያለውን ሂደት አስመልክቶ ባሳለፍነው ሰኞ ታህሳስ 16 ቀን 2010 . ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሸሻ ሸዋረጋ፤ ይህም የውጭ ምንዛሪ የገቢ መጠን ሀገሪቱ ቡናን እንደዚሁም ቆዳና ሌጦን የመሳሰሉ ምርቶችን ወደ ውጪ በመላክ ከምታገኘው ገቢ በላይ ነው።

ገንዘቡ በቀጥታ በካሽ መልኩ እንጂ በአይነት የሚገለፅ እንዳልሆነ ዶክተር መሸሻ አመልክተዋል። ይህም በውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያኖች በግል ከሚላከው የውጭ ምንዛሪ ገቢ (remittance) በተጨማሪ በብሄራዊ ባንክ ሪፖርት ውስጥ ከውጭ በቀጥታ የሚላክ ገቢ (remittance) ተደርጎ የሚመዘገብ መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል። ገንዘቡ የልማት ሥራን በሚያከናውኑ የልማት ድርጅቶች ባንክ አካውንት በቀጥታ በውጭ ምንዛሪ ካሽ መልኩ የሚለቀቅ መሆኑ ታውቋል።  

 

ይህንን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ለልማት አጋሮቻቸው በቀጥታ የሚልኩ በርካታ ድርጅቶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ድርጅቶች መካከልም ለምግባረ ሰናይ አላማ የተቋቋሙ ፋውኔዴሽኖች በተለይም ፓካርድ ፋውንዴሽን እንደዚሁም ሚሊንዳና ጌትስ ፋውንዴሽኖች እንደዚሁም ዩሴኤአይዲ፣ ኦክስፋም፣ ፕላን ኢንተርናሽናል፣ ወርልድ ቪዥንና የመሳሰሉት ድርጅቶች በዚህ በኩል ሰፊ ገንዘብን በመልቀቅ የሚጠቀሱ መሆናቸውን ኃላፊው ጨምረው አመልክተዋል።

 

ይህም የሚለቀቀው ገንዘብ መጠን ከመንግስት የልማት ፕሮግራም ጋር በተጣጣመ መልኩ ለልማት ሥራ የሚውልበት አሰራር መኖሩ ተመልክቷል። ይህ የገንዘብ መጠን ሀገሪቱ ለምግብና ለዕለት ደራሽ ድጋፎች መልክ የምታገኘውን አይጨምርም ተብሏል። 

 

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ሕብረት በስሩ 4 መቶ አባል ድርጅቶችን አቅፎ የያዘ ህብረት ነው። ይህ የገንዘብ መጠን ከተጨመረ ባለፉት ዓምስት ዓመታት በየዓመቱ ወደ ሀገሪቱ እየገባ ያለው የገንዘብ መጠን ከአንድ ቢሊዮን 22 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።

 

የኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ ሲሆን የመንግስት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከውጭ ሀገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በሚልኩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደዚሁም በቱሪዝሙ ዘርፍ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህ ረገድ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩልም የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለመንግስት የልማት ሥራዎችና የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፍተኛ ገቢን በማስገኘት ላይ ይገኛል።

 

ሆኖም የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ የወጣው አዋጅ ድርጅቶቹ በሚገባ ሥራቸውን እንዳያከናውኑ አድርጓቸዋል የሚል ቅሬታን ሲያሰተናግድ በመቆየቱ ጉዳዩ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ቀርቦ በመንግስት በኩል በመታየት ላይ መሆኑ ታውቋል። በዚህም ዙሪያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የአንድ መድረክ ውይይት አድርገዋል። ህጉ የኢትዮጵያ መንግስት ከምዕራብያዊያን ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻክር አድርጓል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
146 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1082 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us