ምርጫ ቦርድ ከዘንድሮ ምርጫ ጋር በተያያዘ ከፓርቲዎች ጋር ሊወያይ ነው

Wednesday, 27 December 2017 12:16

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በያዝነው ዓመት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሚያካሂደው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም አስመልክቶ በተዘጋጀው ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፓርቲዎች ጋር ሊወያይ መሆኑን የሰንደቅ ምንጮች አረጋገጡ።

 

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና የአካባቢ ምርጫ ዘንድሮ ለማካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሰንደቅ ጋዜጣ ምንጮች ጠቅሰው፤ ቦርዱ ዝግጅቱን ጨርሶ ከፓርቲዎች ጋር የጊዜ ሰሌዳውን ለማፅደቅ እየጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል። ለወትሮ በሚያዚያ እና በግንቦት ወራት ምርጫዎች የሚካሄዱ ሲሆን የዘንድሮው ምርጫ መቼ እንደሚከናወን በጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳው ላይ በቀጣይ የሚታወቅ ይሆናል።


በዘንድሮ ምርጫ ላይ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ተሳትፎ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ጥያቄ አቅርበን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥላሁን እንዳሻው፤ ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ጥላሁን እንዳሉት “ፓርቲያችን በመሠረታዊ የምርጫ ስርዓትና አወቃቀር ላይ ለኢህአዴግ ያቀረብንለት ጥያቄ አለ። እስካሁን ጥያቄውን ያልመለሰልን ሲሆን ጥያቄያችን ከተመለሰ ውሳኔ እናስተላልፋለን” ብለዋል።


በዚህ ጉዳይ ላይ የፓርቲያቸውን አቋም እንዲነግሩን የጠየቅናቸው የመኢአዱ ም/ል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ፓርቲያቸው በዚህ ጉዳይ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ተናግረዋል። ፓርቲው ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ የጊዜ ሰሌዳው ከወጣ በኋላ እንደሚወስን ጨምረው ተናግረዋል።


ምርጫው በእስካሁን አካሄዱ ግንቦት ወር ላይ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን የዘንድሮ ምርጫ ግን መቼ እንደሚከናወንና እያደረጉ ስላሉት ዝግጅት ምርጫውን የሚመራው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ሆነ ፓርቲዎች እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በአገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች ቦርዱ ምርጫውን ለማካሄድ አስቸጋሪ ሳይሆንበት እንዳልቀረ የሰንደቅ ጋዜጣ ምንጮች ተናግረዋል።


የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም አባይ በበኩላቸው ቦርዱ ምርጫውን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
161 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1073 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us