የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጠ/ሚ ኃይለማርያም እና ከዶ/ር ወርቅነህ ጋር ተወያዩ

Wednesday, 27 December 2017 12:18

በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በትናንትናው ዕለት ከጠ/ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ / ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ሚኒስትሩን ትናንት ተቀብለው ባነጋገሩበት ሥነ ሥርዓት ላይ ከግብፁ ፕሬዚደንት አልሲሲ የተላከላቸውን መልዕክት ተቀብለዋል።

 

የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የመከሩ መሆኑን የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ዘገባ የጠቆመ ሲሆን፤ ግድቡን በተመለከተ በመርህ ደረጃ በተደረሰው ስምምነት ላይ ተወያይተዋል ብሏል።

 

የግድቡ ጉዳይ ዝርዝር ውይይት የሚደረገው በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን ሱዳንን ጨምሮ የሦስትዮሽ መሆኑ በጋራ ውይይታቸው ላይ ተነስቷል።

 

በግድቡ ዙሪያ ዓለም አቀፍ የጥናት ቡድን ባለፈው ጥቅምት 2017 ባቀረበው ሪፖርት ላይ ሦስቱ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ግብፅ) ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻላቸው በተለይ በግብፅ መገናኛ ብዙሃንና አንዳንድ ባለሥልጣናት በኩል አዲስ የፕሮፓጋንዳ ውጥረትን ፈጥሮ ከርሟል።

 

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከግብፁ ፕሬዝደንት በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት በቅርቡ በግብፅ ይፋዊ የሥራ ጉብኝትን ጨምሮ ለፓርላማው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።¾

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
248 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 148 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us