አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ ለ50 ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል እሰጣለሁ አለ

Wednesday, 03 January 2018 15:46
በ1996 ዓ.ም የተመሠረተው እና በአምስት ካምፓሶች ትምህርት እየሰጠ ያለው አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ50 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የትምህርት ዕድል መስጠቱን ገለፀ። ኮሌጁ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የነፃ ትምህርት እድል የሚያገኙ ተማሪዎች መማር የሚችሉት ከአምስቱ ካምፓሶች (አዲስ አበባ፣ ደብረዘይት፣ ድሬዳዋ እና ሐርጌሳ) በመረጡት ይሆናል። ምዝገባ የሚካሄደው ከጥር 1 ቀን እስከ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም መሆኑንም ጋዜጣዊ መግለጫው ጨምሮ አስታውቋል። በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን ከፍለው መከታተል ላልቻሉ ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጥ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የማድረግ አገራዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ የገለፀው አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ፤ ከምስረታው ጀምሮ ባሉት 14 ዓታት 10ሺህ ተማሪዎችን በነፃ ማስተማሩን አስታውቋል። ይህም በገንዘብ ሲሰላ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አቶ ሀብታሙ ጋቢሳ ተናግረዋል። የነፃ ትምህርት ዕድል የሚያገኙ ተማሪዎችን በተመለከተ ምን ያህል ተማሪ በዲግሪ ስንት በሁለተኛ ዲግሪ እንደሆነ መግለጫው ባይገልፅም በዕድ ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ኮሌጁ በነፃ ለማስተማር የሚጠይቀውን መስፈርቶች የትምህርት ሚኒስቴርን መስፈርት ጨምሮ አሟልተው እንዲመዘገቡ ጠይቋል።
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
147 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1040 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us