ፍ/ቤት ለዶክተር መረራ ጉዲና 67ሺ ብር ካሳ እንዲከፈል ወሰነ

Wednesday, 03 January 2018 16:06

በዶክተር መረራ ጉዲና እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መካከል በነበረው አለመግባባት ክስ ለመስረት ኃላፊነት የወሰዱ ጠበቃ በወቅቱ ክስ ባለመመስረታቸው 67ሺ ብር ለዶክተር መረራ ጉዲና ካሳ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡

የዶክተር መረራ ጉዲና የግል ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፣ “ዶክተር መረራ ጉዲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላይ ክስ ለመመስረት ለጠበቃ ደርበው ተመስገን ውል ሰጥተዋቸው ነበር፡፡ ጠበቃ ደርበው ግን ውሉን ተቀብለው አንድ ዓመት ድረስ በመያዝ ክስ መመስረት የሚያስችላቸው ጊዜ በማለቁ ክሱ በይርጋ ታግዷል፡፡ በዚህ መነሻ ለጠበቆች ዲሲፕሊን ኮሚቴ ክስ መስርተን ጉዳዩን የተመለከተው ኮሚቴ በአቶ ደርበው ላይ የስድስት ወር ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡ ይህንን የኮሚቴውን ውሳኔ ይዘን በአንደኛ ደረጃ ችሎት ክስ መስርተን ለተፈጸመው ስህተት ጠበቃ ደርበው ለዶክተር መረራ ጉዲና 67ሺ ብር ካሳ እንዲከፍሉ በይኖባቸዋል” ብለዋል፡፡

በተያያዘም በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ ዓቃቢ ሕግ ክስ መስርቶ ሕዳር 22 ቀን 2010 ዓ.ም ምስክር አሰምቶ መጨረሱን ከገለጸ በኋላ፣ ከክሱ ጋር አብሮ ያልቀረበ 10 ሲዲ ይታይልኝ ሲል በድጋሚ ላቀረበው ጥያቄ፣ ፍርድ ቤት መፍቀዱን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

ጠበቃው አቶ ወንድሙ እንደሚሉት፣ ከክስ መዝገቡ ጋ ያልቀረበ ማስረጃ ይታይልኝ ማለቱ ተገቢ አለመሆኑን እና የሥነሥርዓት ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርገው ብጠይቅም፣ አልተቀበለኝም ብለዋል፡፡

ዓቃቤ ሕጉ ትላንት በዋለው ችሎት የሲዲውን አንድ ኮፒ ብቻ ይዞ በመቅረቡ ለነገ ጠዋት እንዲያስረክብ ትዕዛዝ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
723 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1079 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us