“ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ወደ ቀደመ ቦታቸው አለመመለስ አደጋ አለው”

Friday, 12 January 2018 16:49

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ወደ ቀደመ ቦታቸው አለመመለስ አደጋ አለው

ኦፌኮ

በይርጋ አበበ

በቅርቡ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች በተነሳ ግጭት የተፈናቀለ-የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በአስቸኳይ ወደነበሩበት መመለስ አለባቸው ሲሉ የኢፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡

አቶ ሙላቱ እንደተናገሩት፤አሁን የተያዘው በተለያዩ ቦታ እናሰፍራለንም ማለት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ጠንቅ የሆነ ሌላ መርዝ ወይም ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ መትከል ነውብለዋል፡፡ አቶ ሙላቱ አክለውም፤ሶማሌ ክልልም ሆነ ኦሮሚያ ክልል በአንድ አገር እና አንድ መንግሥት ሥር የሚተዳደሩ ሆነው ሳለ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን ዜጎች በሌላ ቦታ ቢያሰፍሩት ነገ ደግሞ ሌላው ክልል የአንዱን ብሔር ህዝብ ያፈናቅልና ተመሳሳይ ችግር ይፈጠራል፡፡ ይህን ለማስቀረት ግን ከአሁኑ ጥንቃቄ ቢደረግበት ይበጃልሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኦፌኮ /ሊቀመንበር አያይዘውም፤ይህ የዜጎች መፈናቀል ዝም ብሎ ዜጎች ተፈናቀሉ ተብሎ የሚተው ጉዳይ ሳይሆን፤ ለሕግ የበላይነትና የሰዎችን መብት ለማስከበር ሲባል ይህን ጉዳት ያደረሱ ሰዎች ለሕግ ሊቀርቡ እና ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባልብለዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች መካከል የተነሳውን ግጭት ያጣራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቋቋመው የሱፐርቪዥን ቡድን በበኩሉ ታህሳስ 26 ቀን 2010 . ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አቅርቦ ነበር፡፡ በሪፖርቱ  ላይም  ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ያሉበት ኮሚቴ በማቋቋም ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል። ተሰርቷል ካሉት መካከል በግጭት አካባቢዎች ከማንኛውም የክልል ታጣቂ ሀይል ነጻ ማድረግ ተችሏል፣ በዚህም እርምጃ አንጻራዊ ሠላም እየመጣ ነው ብለዋል። የሠላም ኮንፈረንሱ ባለመሳካቱ ክልሎች በተመረጡ አካባቢዎች በጊዜያዊነት ተፈናቃዮችን እንዲያሰፍሩ ወስነው እየተሰራበት መሆኑን ገልጿል፡፡

የተወካዮች /ቤት አባላት በበኩላቸው፤ እነዚህ ወንጀለኞች እነማን ናቸው፣ ለምንድነው ለፍርድ የማይቀርቡት? የፌደራል መንግሥት ስለምን ዝምታን መረጠ? በማለት አጥብቀው ጠይቀዋል።መሸፋፈን ይቅር' ያሉ አባላት በወንጀሉ እጃቸው ያለበት ከፍተኛ አመራሮች ጭምር ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
137 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1021 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us