“የታተመው ዜና የተሳሳተ ነው”

Friday, 12 January 2018 16:54

የታተመው ዜና የተሳሳተ ነው

ለሰንደቅ ጋዜጣ

በአራተኛው ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ የትምህርትና ቅስቀሳ ዘመቻ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አፈፃፀም እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ለመወያየት ሁሉንም የመንግሥትና የግል የኮሙዩኒኬሽንና የሚዲያ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያሳተፈ መድረክ ታህሳስ 21 ቀን 2010 . በቢሾፍቱ ከተማ ፒራሚድ ሆቴል መካሄዱ ይታወሳል። በዚህ መድረክ ከተጋበዙት ሕትመት ሚዲያዎች መካከል ሰንደቅ ጋዜጣ አንዱ ሲሆን፤ በዕለቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን /ቤት እና የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ስለ ቆጠራው ቀጣይ ሂደት ላይ የሰጡት ምላሽ፡-

 

1.ቆጠራ ኮሚሽን /ቤቱ አጠቃላይ የቴክኒክ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን እንዳጠናቀቀ፣

2.ለትምህርትና ቅስቀሳ ዘመቻው የተመደበ በጀት በቂ አይደለም በሚል ለተነሳው ጥያቄ ሕብረተሰቡን የመቀስቀስ ሥራ ክልሎች በባለቤትነት ከሚያከናውኑት ተግባራት አንዱ መሆኑን ገልፀው ለዝህ ተግባር የሚመደብላቸው በጀት በቁጠባ በመጠቀም እንዲሁም ሌሎች ለዚህ ሥራ የሚያግዙ አማራጮችን ጭምር በመጠቀም የትምህርትና ቅስቀሳ ዘመቻውን ወደ ኅብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መሥራት እንዳለባቸው፣

3.አሁን በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ የድንበር ግጭት ምክንያት የተፈጠረው የሠላም መታጣትና አለመረጋጋት በቆጠራው ሥራ ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ በሚመለከት ያላቸውን ግምገማ እንዲያስረዱ ለተነሳው ጥያቄ ያላቸውን ግምገማ ሲያስረዱ፡-

 

·    ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሚያ እና ኢትዮ ሶማሌ ክልሎች በድንበር አካባቢ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከሁለቱም ክልሎች በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው በመፈናቀላቸው በነዚህ ቦታዎች ቀደም ሲል የተሰራውን የቆጠራ ቦታ ካርታዎች በመጠቀም ደረጃውንና መርሆውን የጠበቀ የሕዝብ ቆጠራ ማካሄድ ተፅዕኖ እንደሚኖረው፤

·   በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲታዩ የነበሩ የፀጥታ መደፍረስና ያለመረጋጋት ለቆጠራው ሥራ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ምቹ እንዳልነበሩ፤ በዚህም ምክንያት በቆጠራው የሚሰማሩትን ሠራተኞች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት መመልመል፣ የስልጠና ቦታዎችን በበቂ ሁኔታ ያለማዘጋጀት፤

·   ወረዳዎቹ ለፀጥታና ሰላምን የማረጋጋት ስራ ቅድሚያ ከመስጠታቸው የተነሳ ለቆጠራ ሥራው በቂ ዝግጅት ያለማድረግና በቀበሌ ደረጃ ሁኔታዎችን ያለማመቻቸት፤ በየአካባቢው የተደረጉት ግምገማዎች እንደሚያሳዩት፣ በዚህም መነሻ በህዝብና ቤት ቆጠራ መርሆዎች መሠረት የተሳካና ተኣማኒነት ያለው ቆጠራ ለማካሄድ የሚመረጠው ጊዜ በሰው ሰራሽም ሆነ በሌሎች የተፈጥሮ ምክንያቶች ህዝቡ ከመደበኛ መኖሪያው የማይፈናቀልበትና ተረጋግቶ በአካባቢው የሚኖርበት ወቅት መሆን ያለበት መሆኑ ግልጽ እንደሆነ አስረድተው ከላይ በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት የቆጠራው ሥራ በተቀመጠለት ጊዜ ይካሄድ፣ አይካሄድ የሚለው ጉዳይ ለህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ቀርቦ ውሣኔ እንደሚሰጥበት በአጽንኦት ለተሳታፊዎቹ የገለጹት ሀሳብ ሆኖ እያለ በጋዜጣችሁ 13 ዓመት ቁጥር 613 የታህሳስ 25 ቀን 2010 . ረቡዕ ዕትምለህዝብና ቤት ቆጠራ የተመደበው በጀት በቂ አይደለምበሚል ርዕስ ስር በዚህ ምክንያት ቆጠራ የሚካሄድበት ጊዜ ሊራዘም ይችላል ብላችሁ ያወጣችሁት ጽሑፍ በወቅቱ ዋና ዳይሬክተሩ በጉዳዩ ላይ የሰጡትን ገለጻ መሠረት ያላደረገ የተሳሳተ መረጃ እንደሆነ፤ የአራተኛው ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ ከበጀት ጋር በተያያዘ የቆጠራው ጊዜ ሊራዘም እንደሚችል የተሰጠ መረጃ እንደሌለ እያሳወቅን በቀጣይም በሕትመታችሁ ስለ ቆጠራው የምታወጡት መረጃ ከቆጠራ ኮሚሽን /ቤት በኩል የሚሰጡትን መረጃ መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት እየገለጽን ጋዜጣችሁ ላይ በተጠቀሰው ቀንና የሕትመት ቁጥር ያወጣችሁት የተሳሳተ መረጃ በዚህ ደብዳቤ ላይ ስለ ጉዳዩ የተዘረዘሩትን ሀሳቦች መነሻ በማድረግ በቀጣይ ዕትማትሁ ለሕብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ የሚያስተላልፍ የዕርምት ጽሁፍ እንድታወጡ በጥብቅ እናሳስባለን።

ከሠላምታ ጋር

ሳፊ ገመዲ

የሕዝብ ግንኙነትና መረጃ ስርጭት

ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ማህተም እና ፊርማ አለው

አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ በተመለከተ ታህሳስ 21 ቀን 2010 . በቢሾፍቱ ከተማ ለመንግስትና የግል የሚዲያ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተሰጠውን ግንዛቤ ማስጨበጫ ተከታትለን የሰራነውን ዜና በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ መሆኑ በህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ፅህፈት እና የማዕከላዊ ስታትቲክስ ኤጀንሲ አማካኝነት ተገልፆልናል። ዜናውለህዝብና ቤት ቆጠራ የተመደበው በጀት በቂ አይደለምየሚል ርዕስ ያለው ሲሆን እኛም የተላከልንን ማስተባበያ ተቀብለን እንደሚከተለው ያስተናገድን አስተናግደናል።

  አንባቢያን የተሰራውን ዜና ባያገኙ እንኳን በኤጀንሲው የተላከውን ማስተባቢያና ዋና ዳይሬክተሩ በወቅቱ የተናገሩትን ንግግር አስተያይተው የራሳቸውን የህሊና ፍርድ መስጠት ይችሉ ዘንድ ከዚሁ ጎን ለጎን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በዚያው መድረክ የተናገሩትን ሀሳብ ከመቅረፀ ድምፃችን ቃል በቃል በመገልበጥ ለአንባቢያን አቅርበናል

አቶ ቢራቱ ይገዙ በዕለቱ በመድረኩ ላይ የተናገሩት፤

ወጪን በሚመለከት የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ለዚህ ሥራ ይበቃል ብሎ የመደበው ወደ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ነው። ከቆጠራው መጀመሪያ ውጤቱ ይፋ እስኪደረግ ድረስ። ይህ በጀት ይበቃል? ሁሉንም ሥራዎች ከሰራን አይበቃም። ስለዚህ የፌደራል መንግስት የሚመድበው ውስን በጀት ይሆናል። መረጃው ደግሞ የፌደራል ብቻ ሳይሆን የክልልም ስለሆነ፤ ክልልም የራሱን ድርሻ ስለሆነ በየሁሉም መድቦ ካልሰራ በስተቀር በቂ ስለማይሆን ይሄንን ሁላችንም በጋራ እየተረዳዳን የምንሰራው ሆኖ ቢወሰድ። ነገር ግን በእኛ በኩል ያለችውን በጀት ወይንም ለቆጠራ የተመደበውን በጀት ግን  እስከታች ድረስ ምደባውን (Allocation) ሰርተን ለሁሉም እንዲደርስ ይደረጋል። ግን በቂ አይደለም በሚል ነው እኛ የወሰድነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
201 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1033 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us