የውጭ ሀገር ጉዲፈቻ በአዋጅ ተከለከለ

Friday, 12 January 2018 16:58

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የቤተሰብ ሕግ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ውስጥ የተካተተውን የውጭ ሀገር ጉድፈቻ የሚከለክለውን ሕግ በትላንትናው ዕለት አጸደቀ።

 

ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር ዕይታ የተመራላቸው የም/ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮምቴ፣ የሴቶችና የሕጻናት ጉዳዮች ቋሚ ኮምቴ እና የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮምቴ ረቂቅ አዋጁን መርምረው፣ ጉዳዩ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክረው የውሳኔ ሀሳባቸውን በትላንትውናው ዕለት ለምክርቤቱ ይዘው ቀርበዋል።


የቋሚ ኮምቴዎቹ አብዛኛው አባላት የተሻሻለው አዋጅ ላይ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ያጡ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሕጻናት በኢትዮጽያ ባህል፣ በተወለዱበት አካባቢ ወግ ልማድና ማህበረሰባዊ እሴት ታንጸው እንዲያድጉ በሀገር ውስጥ ባሉ አማራጮች የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና እንክብካቤ ማለትም በሀገር ውስጥ ጉድፈቻ፣ በአደራ ቤተሰብ እና በመልሶ ማቀላቀል ፕሮግራሞች ተደግፈው እንዲያድጉ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተስማምተዋል።


በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ 213/1992 አንቀጽ 193 እና 194 /3/ መ እና ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ እንደተመለከተው የውጭ ጉድፈቻ እንደ አንድ አማራጭ መቀመጡ በሕጻናት ላይ ለሚፈጸሙ የተለያዩ ወንጀሎች በር የሚከፍት መሆኑ ተመልክቷል። የውጭ ጉድፈቻ ማስቀረቱ በሕጻናት ላይ የሚደርሰውን የማንነትና የሥነልቦና ቀውስ ከማስቀረቱም በላይ በሕጻናቱ መልካም አስተዳደግና ስብዕና ግንባታ ላይ ለመስራት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርና ብሔራዊ የሕጻናት ፖሊሲውን በመተግበር ሕጻናቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ በአዋጁ ማብራሪያ ላይ ተመልክቷል።


በረቂቅ አዋጁ በቋሚ ኮምቴዎቹ በታየበት ወቅት በአነስተኛ ድምጽ አዋጁ መጽደቁን የተቃወሙ የም/ቤቱ አባላት የሚከተሉትን መከራከሪያዎች አቅርበዋል። «ነባሩ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ከብሔራዊ የህጻናት ፖሊሲ ጋር የማይጋጭ ሆኖ ሳለ ሕገወጥ የሕጻናት ዝውውርን በመከላከል ሰበብ የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን የውጭ ጉድፈቻ መዝጋት በከፍተኛ የጤና ችግር ውስጥ ያሉትንና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ሕጻናት ዕድል የሚዘጋ በመሆኑ ሕጉ የሚሻሻልበት አሳማኝ ምክንያት አላገኘንም» በማለት የማሻሻያ አዋጁን መጽደቅ ተቃውመዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
248 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1049 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us