ሕወሓት ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን አነሳ

Wednesday, 17 January 2018 13:19

ከጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመቐለ ከተማ 7ኛውን የድርጅቱን ኮንፈረንስ እያካሄደ የሚገኘው ህወሓት፤ ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማንሳቱ ታውቋል።

 

ሕወሓት ከካድሬዎቹ እና ከሕዝብ ጋር እያደረገ ባለው ሕዝባዊ ኮንፈረንስ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም እና ወ/ሮ አረጋሽ በየነን ማንሳቱን ተገልጿል።


ከተሳታፊዎች እና ከምክር ቤት አባላት ከኃላፊነት ስለሚነሱ ሰዎች ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም እና ወ/ሮ አረጋሽ በየነን ከኃላፊነታቸው ለምን እንደተነሱ ጥያቄ ቀርቦ፣ በኔትዎርክ የተያያዙ ናቸው የሚል በድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊ ምላሽ ተሰጥቷል።


ድርጅቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በክልሉ በሚታዩ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ችግሮች በመለየት እና ችግሮች ለመፍታት በሚያስችሉ አሰራሮች ላይ በጥልቀት እና በስፋት ውይይት መደረጉ እና አመራሩ ለታዩት ችግሮች መፈጠር ዋና ምክንያት መሆኑን መግባባት ላይ ደርሷል ከመባሉ ውጪ በግለሰብ ደረጃ የተወሰደ ኃላፊነትና ተጠያቂነት መኖሩን ድርጅቱ ይፋ አላደረግም። ሆኖም ግን ችግር ያለበት አካል ይዞ መዝለቅ ስለማይቻል ውሳኔ ማሳለፍ አስፈላጊ እንደሚሆን ገልጿል።


እስካሁን ባለው እርምጃ “ኔትዎርክ የዘረጉ” ወይም የእንቶኔ ኔትዎርክ ናቸው የተባሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ተመራጮች ከመነሳታቸው ውጪ ኔትዎርኩን የዘረጋው ማን፣ ለምን ዓላማ እንደዘረጋው ግልፅ አልተደረገም። ኔትዎርኩ የሚበጠሰው ማንን በማንሳት እንደሆነ በግልፅ ድርጅቱ ያስቀመጠው አቅጣጫ ባይኖርም፣ በመቐለ ከተማ የተለያዩ ግምት እየተሰጠ በመሆኑ የሚሰጠውን ውሣኔ ተጠባቂ አድርጎታል።


በሌላ ወገን ያነጋገርናቸው፣ አለ የሚሉትን ኔትዎርክ በጥሶ አዲስ ኔትዎርክ የመዘርጋት ሥራዎች በድርጅቱ ውስጥ እንዳይከሰትም ስጋቶች አሉን፣ የሚደረገው የስልጣን መተጋገል ለተሻለ ለውጥ ከሆነ ግን አንጠላውም ብለዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
785 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 930 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us