የመካን ሴቶች ህክምና በቅርቡ ይጀመራል

Wednesday, 24 January 2018 13:58

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ ልጅ መውለድ ያልቻሉ (የመካን) ሴቶች ህክምናን ከወራት በኋላ ሊጀመር መሆኑን አስታወቀ። የመጀመሪያ ዙር ባለሞያዎችም ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።

 

የጤናማ እናትነት ወርን አስመልክቶ ኮሌጁ በሰጠው መግለጫ ላይ እንደተገለፀው በማህፀን ቱቦ መደፈን ምክንያት ልጅ መውለድ ላልቻሉ ሴቶች ህክምና በማድረግ ልጅ እንዲወልዱ ለማገዝ ዝግጅት እየተደረገ ነው። በኮሌጁ የማህፀንና ጽንስ ስፔሻሊስትና የክፍሉ ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ኡርጌሳ እንደገለፁትም ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመውለድ ችግር ላለባቸው ሴቶች በአርቴፊሻል መንገድ ፅንስ እንዲፈጠር የማድረግ ህክምና ለመስጠት ኮሌጁ እየሰራ ይገኛል። ኮሌጁ ከመካንነት ችግር ጋር በተያያዘ በሰብ ስፔሻሊቲ ደረጃ ባለሞያዎችን እያሰለጠ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በመጪው ሚያዝያ ወይም ግንቦት ወር ላይ ለመጀመሪያዎቹ ሴቶች አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ህክምናው የሚሰጠው ለሴቶች ብቻ ሲሆን፣ ለህክምናው ብቁ የሆኑ ሴቶችም ከታካሚዎች ተመርጠው መዘጋጀታቸው ተገልጿል። ጤናማ የማህፀን ቱቦ ኖሯቸው እገዛ ተደርጎላቸው በተፈጥሯዊ መንገድ መወለድ የማይችሉት ብቻ ለዚህ ህክምና መመረጣቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።


የመካንነት ህክምና የተራቀቀ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ፣ የራሱ የሆነ ላብራቶሪ እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህ አገልግሎት የሚውል ቦታ ሀያ ሁለት አካባቢ በማደራጀት ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ላብራቶሪው በዝግጅት ላይ እንደሚገኝና በቅርቡ ተጠናቆ ዝግጁ እንደሚሆን የገለፁት ዳይሬክተሩ፣ ህክምና ረቀቅ ያለ ችሎታን የሚጠይቅ በመሆኑ የሰብ ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ተቀርፆ የመጀመሪያው ዙር ባለሞያዎች እየሰለጠኑ መሆናቸውን እና ከሌሎች ሀገራትም ልምድ እየተቀሰመ መሆኑን ዶክተር ታደሰ ተናግረዋል።


ህክምናው የሚሰጠው ከሚቺጋን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር መሆኑን የገለፁት በኮሌጁ የህክምና ዘርፍ ምክትል ፕሮቮስት ዶክተር ብርሐኔ ረዳኢ በበኩላቸው፤ ህክምናውን ለማስጀመር የሚያስፈልገው ገንዘብ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል። ለህክምናው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ተከላ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅም ዶክተር ብርሐኔ በተጨማሪ ተናግረዋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
228 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1037 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us