“ወልድያ ላይ በጥምቀት በዓል ለተፈጠረው ግጭት ኢህአዴግ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን ይቅርታ ይጠይቅ”

Wednesday, 24 January 2018 14:13

“ወልድያ ላይ በጥምቀት በዓል ለተፈጠረው ግጭት ኢህአዴግ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን ይቅርታ ይጠይቅ” 

 

መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲዎች

በይርጋ አበበ

 

መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን የጥምቀትና የቅዱስ ሚካኤል ቃና ዘገሊላ በዓል ለማክበር በወጡ የወልድያ ከተማ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ለተፈፀመው ግድያ የእምነቱን ተከታዮች ኢህአዴግ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል።


ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው “ለተነሳው ግጭትና ለተወሰደው የግድያ እርምጃም የቀረበው ምክንያት መንግሥትን የሚቃወም ዜማ አሰማችሁ የሚል ነው። ይህ ደግሞ መብት መጣስ ነው” ያሉ ሲሆን “ይህን ችግር የተመለከተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ድርጊቱን አለማውገዟ ያስተዛዝበናል” ብለዋል።


ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አክለውም “የፀጥታ ሀይሎች ቅዱስ ታቦት ተሸክመው በቆሙ ቀሳውስት ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ሀይማኖቱን መድፈር በመሆኑ መንግሥት ድርጊቱን በማውገዝ በግልጽ በአደባባይ ይቅርታ ይጠይቅ። ለሟች ቤተሰቦች የደም ካሳ እንዲከፈል፣ ግድያው እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡም ሆነ ጉዳዩን በቸልተኝነት የተመለከቱ የዞኑ ባለሥልጣናት በህግ እንዲጠየቁ፤ ግድያውን የፈፀሙ የመንግሥት ታጣቂዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን” ሲሉ አቋማቸውን አስታውቀዋል።

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
393 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1031 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us