ታክሲ ለማሽከርከር 10ኛ ክፍልን ማጠናቀቅን በአስገዳጅነት ያስቀመጠው አዋጅ ጸደቀ

Wednesday, 24 January 2018 14:15

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የታክሲ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት 10ኛ ክፍል ማጠናቀቅና ልዩ የሙያ ሥልጠና መውሰድን የሚያስገድደውን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ ፈቃድን ባልተለመደ ሁኔታ በከፍተኛ የተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ።

 

አዲሱ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ለምክርቤቱ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም የምክርቤቱ የድምጽ መሳሪያዎች ቴክኒካል ብልሽት ምክንያት ስብሰባውን ማካሄድ ባለመቻሉ ይህው ስብሰባ በትላንትናው እለት እንዲካሄድ ሆኗል።


ምክርቤቱ በትላንት ውሎው የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ ከ60 በላይ ተቃውሞ በማስከተል በአብላጫ ድምጽ ያጸደቀው ሲሆን አነስተኛው ድምጽ አዋጁ የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው በማለት እንዳይጸድቅ ተቃውመዋል።


ትላንት የጸደቀው አዋጅ እንዲህ ይላል። «ማንኛውም አሽከርካሪ በታክሲ አገልግሎት የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎችን ማሽከርከር የሚችለው 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ሆኖ የአውቶሞቢል ወይም የሕዝብ ምድብ ቋሚ አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያለው ከሆነ እና ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው የሥልጠና ይዘት መሠረት ከፈቃድ ሰጪ አካል ልዩ ሥልጠና በመውሰድ የታክሲ የአሽከርካሪ የምስክር ወረቀት የተሰጠው እንደሆነ ነው።»


አዲሱ አዋጅ፤ ሰፊ ክፍተቶች ነበሩበት የተባለውንና እስከ ትላንት ድረስ በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 600/2000 ሽሮታል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
351 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 149 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us