“የአመራሮቹ መታሰር ለኦፌኮ ጥንካሬ ሆኖታል”

Wednesday, 24 January 2018 14:17

“የአመራሮቹ መታሰር ለኦፌኮ ጥንካሬ ሆኖታል” 

ዶ/ር መረራ ጉዲና

 

በይርጋ አበበ

 

በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ በምህረት ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና “የእኛ መታሰር ለኦፌኮ ጥንካሬ ሆኖታል” አሉ።


ዶ/ር መረራ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ “የድርጅት መዋቅር እና ግለሰቦችን ስታነሳ ብዙ ችግሮችን ታያለህ። ከእስር ከወጣሁ በኋላ እያየሁ ያለሁት ግን ኦፌኮ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት በላይ የተሻለ የህዝብ ድጋፍ ያገኘ ይመስለኛል። የህዝብ ድጋፍ ካለ ደግሞ የግለሰቦች መታሰር እና መፈታት ብዙም ትርጉም የለውም” ሲሉ ተናግረዋል።


የኦፌኮ ሊቀመንበር አያይዘውም “ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የሚደረጉ ድጋፎችና የመገናኛ ብዙሃንን ሽፋን ስመለከት ለኦፌኮ ጭራሽ ማስታወቂያ ሆኖለታል። እኔ ባልታሰር ኖሮ ይህን ያህል እሰራለሁ ብዬ አላስብም” ያሉ ሲሆን ኦፌኮም ከዚህ በተሻለ ተጠናክሮ ይመጣል ብለዋል።


መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “የአማራ እና ኦሮሞ መገናኛ ብዙሃን እየተሻሻሉ ነው። የብሔራዊ ጣቢያው ግን ለውጥ አልባ ሆኗል” ብለዋል። ዶ/ር መረራ አክለውም “ኢህአዴግ የፖለቲካ እስረኛ የለም ማለቱ እንዲያው አጉል ድርቅና ካልሆነበት በቀር ማንም ሽንኩርት ሰርቆ የታሰረ የለም” ሲሉ መንግስት የፖለቲካ እስረኛ የለም የሚለውን ተቃውመዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ምሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ስፖርተኞች፣ አርቲስቶች እና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በመኖሪያ ቤታቸው በመሄድ እየጎበኟቸው ነው።


ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ፣ ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ ድምፃዊ አጫሉ ሁንዴሳ፣ ኮሜዲያን ልጅ ያሬድ እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዶ/ር መረራን ከጎበኙ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
780 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 109 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us