የመከላከያ ምስክር ውድቅ የተደረገባቸው እነ አቶ በቀለ ገርባ በቀጣይ ሰኞ ለውሳኔ ይቀርባሉ

Wednesday, 31 January 2018 12:46

 

በይርጋ አበበ

 

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ችሎት በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ የተከሰሱት የኦፌኮ አባላትና አመራሮች የፊታችን ሰኞ ለውሳኔ ችሎት ይቀርባሉ።


አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ስምንቱ የኦፌኮ አመራሮችና አባላት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ባለሥልጣናትን ለመከላከያ ምስክሮች ያቀረቧቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም ነበር። ይህን ተከትሎም ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ለውሳኔ ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ይሆናል።


በእነ አቶ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ብዛት 22 የነበረ ሲሆን ዘጠኙ ተከሳሾች በቅርቡ መንግስት ባሳለፈው ምህረት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈተዋል። አምስቱ ደግሞ ቀደም ብሎ ከተከሰሱበት ወንጀል ነጻ ተብለው የተለቀቁ ናቸው።


በእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ አስተያየታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ “አባሎቻችንና አመራሮቻችን የታሰሩት በፖለቲካ እንጂ ወንጄል ፈጽመው ስላልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተናሩት መሰረት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ እንጠይቃለን” ብለዋል።


የፊታችን ሰኞ ለውሳኔ ችሎት ከሚቀርቡት ስምንቱ የኦፌኮ አመራሮችና አባላት መካከል አቶ በቀለ ገርባ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሲሆኑ፤ አቶ ደጀኔ ጣፋ ምክትል ፀሐፊ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ የወጣቶች ክፍል ኃላፊ እና አቶ ጉርሜሳ አያኖ አባል መሆናቸውን የፓርቲው ምክትል ሊመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
686 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 100 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us