የሚለቀቁ ታራሚዎች ቁጥር 6ሺ 376 ደረሰ

Wednesday, 31 January 2018 12:48

- እስካሁን ከክልሎች አማራ 2ሺ 905፣ ኦሮሚያ 2ሺ 345፣ ደቡብ 413 ታራሚዎችን ለቀዋል

 

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአማራ ክልላዊ መንግሥት በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከቀረበባቸውና ጉዳያቸው በፌዴራል ደረጃ ከሚታዩ መካከል የ598 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑን ይፋ ካደረገ በኋላ የአማራ ክልል መንግሥት ለተጨማሪ 2 ሺ 905 ታራሚዎች ምህረት ማድረጉን ትናንት ይፋ አደረገ።


በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ክሳቸው የተቋረጠላቸውና ከቀናት የተሀድሶ ስልጠና በኋላ ይለቀቃሉ የተባሉት ተጠርጣሪዎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ሰሜን ጎንደር 224፣ ከአዊ ዞን 176፣ ከምዕራብ ጎጃም ዞን 107፣ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ከሌሎች ዞኖች የተያዙ ናቸው።


የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ከሚቴ ግምገማ በኋላ የተሻለ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሲባል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች እንዲፈቱ በወሰነው መሠረት በመጀመሪያው ዙር ከተፈቱት 528 እስረኞች መካከል 413 ያህሉ ከደቡብ ክልል ሲሆኑ የተቀሩት 115 ያህሉ ከፌዴራል ናቸው።


በተመሳሳይ ሁኔታ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ትላንት 2 ሺ 905 ታራሚዎችን በምህረት የለቀቀ ሲሆን ከሳምንት በፊት ደግሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 2 ሺ 345 ታራሚዎችን በምህረት መልቀቁ አይዘነጋም።


በኢህአዴግ ውሳኔ መሠረት እስከትላንት ድረስ የተለቀቁ ታራሚዎች ጠቅላላ ቁጥር 6ሺ 376 ደርሷል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
713 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 98 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us